Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልትናንትን ለዛሬ በኅብራዊ ኪነ ጥበብ

ትናንትን ለዛሬ በኅብራዊ ኪነ ጥበብ

ቀን:

በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ዘርፍን ለማሳደግና ቀደምት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ለመዘከር ከሚንቀሳቀሱ የሙያ ማኅበራት መካከል አንዱ የኅብር ግኝት የኪነ ጥበብ ማኅበር ነው፡፡

የኅብር ግኝት የኪነ ጥበብ ማኅበር ሥራ አስኪያጅ የሆነችው አርቲስት ልዩ ወርቅ ተፈራ እንደገለጸችው፣ ማኅበሩ በኪነ ጥበብ ዘርፍ ለአገራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱና የተዘነጉ ባለሙያዎችን ለማስታወስ ዓላማ አድርጎ በ2011 ዓ.ም. የተመሠረተ ነው፡፡

ትናንትን ለዛሬ በኅብራዊ ኪነ ጥበብ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የኅብር ግኝት የኪነ ጥበብ ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አርቲስት ልዩ ወርቅ ተፈራ

ማኅበሩ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ዐፀድ የሚገኘውን፣ የአርቲስት ሙናዬ መንበሩን ሐውልት በማደስና አርቲስቷን በመዘከር ሥራ የጀመረ ሲሆን፣ በቀጣይም አርቲስት ሜሪ አርምዴን ለማስታወስና ከፍ ለማድረግ የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ሥራ አስኪያጇ እንደምትናገረው፣ ማኅበሩ በሕይወት የሌሉትን አርቲስቶች ከማንገሥ ባሻገር በሕይወት እያሉ የተረሱትን፣ አስታዋሽ ያጡትና ያልተዘመረላቸውን የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ከተደበቁበት በማውጣት የሚገባቸውን ክብር እንዲያገኙ በመሥራት ላይ ነው፡፡

በተለያዩ ቴአትር ቤቶች ይሠሩ በነበሩ ባለሙያዎች የተመሠረተው ይህ ማኅበር በአሁኑ ወቅት 30 አባላት ያሉት ሲሆን፣ መገናኛቸውና መሰባሰቢያቸው የሆነው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት እንደ ጥላ እያገለገላቸው ይገኛል፡፡

ማኅበሩ በቀጣይ በኪነ ጥበብ ዘርፍ ለመሥራት ያቀዳቸው በርካታ ተግባራት መኖራቸውን የምትናገረው ልዩ ወርቅ፣ በሕይወት ያሉትንም ሆነ የሌሉትን ባለሙያዎች ስማቸውንና ሥራቸውን ከመቃብር በላይ ለማድረግ አልባሳታቸውንና ሌሎች በሕይወት ዘመናቸው ይጠቀሙባቸው የነበሩትን ቁሳቁሶች በመሰብሰብ ሙዚየም ለመክፈት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ሁለገብ ከያኒያን የነበሩት ሙናዬ መንበሩና ሜሪ አርምዴ በሕይወት እያሉ ሲጠቀሙባቸው የነበሩ አልባሳትና ቁሳቁሶችን ማሰባሰብ መጀመራቸውን የሌሎችንም አርቲስቶች እንዲሁ ማሰባሰቡን አጠናክረው የሚቀጥሉበት መሆኑን ትገልጻለች፡፡

የኅብር ግኝት የኪነ ጥበብ ማኅበር ምክትል ሥራ አስኪያጅ አርቲስት መቅደስ ተሾመ እንደምትናገረው፣ ማኅበሩ የተለያዩ የኪነ ጥበብ ምሽቶችን በወር አንድ ጊዜ ያደርጋል፡፡ ፊልሞችንም ይሠራል፣ መጻሕፍትም ለማሳተም በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ በአገር የኪነ ጥበብ ዘርፍ የራሱን አሻራ አስቀምጦ ለማለፍ እየተጋ የሚገኝ ማኅበር ነው፡፡

ሠላሳ ከሚሆኑ የማኅበሩ አባላት ውስጥ ጋዜጠኞች፣ ተዋንያን፣ ጸሐፊያንና ኮሜዲያን የሚገኙበት ሲሆን፣ ማኅበሩ ‹‹ኅብር›› የተባለበትም ምክንያት ከተለያዩ ሙያዎች የተሰባሰቡ አባላት በመኖራቸው ነው፡፡

ማኅበሩ እንደነ ብርሃኑ በርታ (የማስታወቂያና የቴአትር ባለሙያ)፣ ኪነ ጠቢባኑን ዮሐንስ አፈወርቅ፣ መነን ሙላቱ፣ ኮከብ ተስፋዬ፣ ኮሜዲያን ሀብታሙና ሌሎችንም ታዋቂ ባለሙያዎችን ያቀፈ መሆኑን የምትናገረው አርቲስቷ፣ ማኅበሩ በርካታ የኪነ ጥበብ ሥራዎችን ከተለያዩ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያዎች ጋር በትብብር እየሠራ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የሙናዬ መንበሩን 20ኛ ዓመት በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ያከበረ ሲሆን፣ ለደራሲ ኃይለ መለኮት መዋዕል ‹የምስጋና መስጠት› ፕሮግራምም አዘጋጅቷል፡፡ 

የኅብር ግኝት የኪነ ጥበብ ማኅበር ፕሮዳክሽን ማናጀር አርቲስት ዘበናይ ማኅተመ በበኩሏ፣ ማኅበሩ ከኪነ ጥበቡ ባሻገር በማኅበረሰብ አቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ የድርሻውን እየተወጣ ነው፡፡ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ከኅብረተሰቡ በማሰባሰብ ቦረና ለሚገኙና በድርቅ ለተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎች አበርክቷል፡፡

ማኅበሩ በአሁኑ ወቅት ‹‹ኅብር›› የተሰኘና የማኅበሩ አባላት የተሳተፉበት የግጥም መድበል ለማሳተም በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ የማኅበሩ አባል በሆነችው አርቲስት ኮከብ ተስፋዬ የተጻፈና የተዘጋጀ ‹‹ባለን እናመስግን›› የሚል ተውኔት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመዘዋወር ለማሳየት በእንቅስቃሴ ላይ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...