Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኦቲዝም ተጠቂዎች እንክብካቤ ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶች መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ  

በኦቲዝም ተጠቂዎች እንክብካቤ ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶች መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ  

ቀን:

በአዲስ አበባ የሚገኙ አምስት በኦቲዝም ዘርፍ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ ኦቲዝምና ተዛማጅ የአዕምሮ ዕድገት ችግር የገጠማቸውን ሕፃናትና አፍላ ወጣቶች ለመርዳት እየተቸገሩ በመሆኑ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቀረቡ፡፡

የኦቲዝም ተጠቂዎችንና ቤተሰቦቻቸውን ከጤና፣ ከማኅበራዊ፣ ከሥነ ልቦናዊና ከኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች ለመታደግ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ አላላውስ ያሏቸው ችግሮች መኖራቸውንም አመልክተዋል፡፡

‹‹ፍረጃ ይቁም›› በሚል መሪ ቃል በመጋቢትና በሚያዝያ ወር በዓለምና በአገር አቀፍ ደረጃ ተከብሮ የሚውለውን የዳውን ሲንድሮም እና የኦቲዝምን ቀን አስመልክቶ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ድርጅቶቹ፣ ከተጋረጡባቸው ችግሮች መካከል ዋነኛው የቤት ኪራይ ውድነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እንደ ምንም ብለው የሰበሰቡትን ጥሪት ሁሉ ለቤት ኪራይ እንዲያወሉ መገደዳቸውን፣ በመሆኑም አገልግሎታቸውን ለማስፋትና የያዟቸውን ሕፃናት፣ አፍላ ወጣቶችና ቤተሰቦቻቸውን ለመታደግ እየተሳናቸው እንደመጣ አመልክተዋል፡፡

ፍቅር የኢትዮጵያ አዕምሮ ዕድገት ውስንነት ብሔራዊ ማኅበር፣ ነህምያ የኦቲዝም ማዕከል፣ ብሩህ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ማስተማሪያና ማሠልጠኛ፣ ኒያ ፋውንዴሽንና ጆይ ኦቲዝም ማዕከላትና ቤተ ምሕረት ሁሉን አቀፍ የልማት ድርጅት በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባና በየክልሎች ችግሩ ደርሶባቸው በየቤታቸው የዋሉ ሕፃናትን፣ አፍላ ወጣቶችንና ቤተሰቦችን በአቅም ማነስ ምክንያትም ለመድረስ እንደተሳናቸው አሳውቀዋል፡፡

በአንፃሩ ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ሕፃናት ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም፣ በመንግሥት በኩል የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ መሆኑ እንዳሳዘናቸው አስረድተዋል፡፡

ለእንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው ልዩ ልዩ የመገልገያ መሣሪያዎች ዋጋ ውድነትና ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ምክንያት፣ ፕሮጀክቶቻቸውንና ዕቅዶቻቸውን መሬት ላይ ለማውረድ እንደተሳናቸው፣ በመንገዳገድ ላይ እንደሆኑና ለዚህም ‹‹አይዟችሁ!›› ሊባሉና ሊደገፉ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ ከአዕምሮ ዕድገት ውስንነት መንስዔዎች አንዱ የዘር ውርስ/ሐረግ ነው፡፡ ይህም ማለት የዘር ውርስ/ሐረግ ተሸካሚዎች መዛባት፣ ጉድለት፣ ማፈንገጥ ያልተለመደ የክሮሞዞሞች ዕድገት፣ የሰውነት ንጥረ ነገሮች ሒደት መቃወስና በዘር ውርስ የሚፈጠሩ የአንጎልና የነርቭ ሕመሞች ይገኙባቸዋል፡፡

በዚህ ዓይነት ከሚከሰቱት መካከልም አንዱ ዳውን ሲንድሮም ነው፡፡ ዳውን ሲንድሮም ለአዕምሮ ዕድገት ውስንነት መንስዔ ከሚሆኑት ዋና ዋና ሁኔታዎች አንዱ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...