Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

አይ ይቺ ዓለም!

ትኩስ ፅሁፎች

ሦስት ሰዎች ነበሩ፡፡ አንደኛው ራሰ በራ ነበር፡፡ ሁለተኛው ከመቆሸሹ የተነሳ እከክ ይዞት ነበር፡፡ ሦስተኛውም ንፍጣም ነበር፡፡

እነዚህም ሰዎች ልዩ ባህሪያት እንዳላቸው ተስማምተው ‹‹ስለዚህ አብረን እንሂድ፡፡›› ተባባሉ፡፡ አብረውም እየሄዱ ሳለ ንፍጣሙ ሰውዬ ‹‹አውሮፕላን ሲያልፍ ‘ሁሁሁ…’ ይላል፤›› ብሎ የአውሮፕላኑን አስተላለፍ ያሳየ በመምሰል አፍንጫውን ይጠርጋል፡፡

እከካሙም ሰው እጆቹን በማቆላለፍ ‹‹ኧረ አንድ ቀን ሁለት ፍየሎች እንደዚህ እያደረጉ ሲጣሉ አየሁ፤›› ብሎ የፍየሎቹን ፀብ ያሳየ መስሎ ቁስሉን ያካል፡፡

ራሰ በራውም ‹‹ምን ዓይነት ውሸታሞች ናችሁ!›› ብሎ የተገረመ በመምሰል መላጣውን በእጆቹ ሸፈነ ይባላል፡፡

  • የወግ ገበታ
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች