Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአክሱም ኤርፖርት ጥገና ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተካሄደ መሆኑ ተነገረ

የአክሱም ኤርፖርት ጥገና ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተካሄደ መሆኑ ተነገረ

ቀን:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት የአውሮፕላን ማኮብኮቢያ ሥፍራውን ጨምሮ ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰበት የተነገረውን የአክሱም ኤርፖርት፣ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እያስጠገነ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ ‹‹ጨረታ ስናወጣ በአካባቢው የደኅንነት ጉዳይ አሳስቧቸው ስለነበር ብዙ ሥራ ተቋራጮች ፈቃደኛ ሆነው አልመጡልንም ነበር። ከአንዴም ሁለት ጊዜ ጨረታ አውጥተን መጨረሻ ላይ ተቋራጩን መርጠን ይፋ ካደረግን ወደ አምስት ወራት ይሆነናል። በአሁኑ ወቅት ግን ጥገናው ተጀምሯል፤›› ሲሉ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2016 ዓ.ም. የድርጅቱን ወቅታዊ ሁኔታና የሥራ አፈጻጸም አስመልክቶ በዋና መሥሪያ ቤቱ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ የአክሱም ኤርፖርት ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. በፊት ዕድሳቱ ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚጀምር ገልጸዋል። 

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አቶ መስፍን፣ ‹‹የአክሱም ኤርፖርት ጥገና ተጀምሯል፡፡ የአውሮፕላን ማኮብኮቢያ ሥፍራው ተበላሽቶ ነበር። ለረዥም ጊዜ ዘግይቷል፣ በጣም ይቅርታ እንጠይቃለን፤›› ብለዋል። 

አየር መንገዱ በተለይ ለቱሪስት ፍሰቱ መቀጠል ሲባል ጥገናውን በፍጥነት አጠናቆ በረራውን እንደገና መጀመር እንደሚፈልግም ገልጸዋል። 

ዋና ሥራ አስፈጻሚው የአገር ውስጥ በረራዎችን በድጋሚ ከማስጀመር ጋር በተያያዘ በቅርቡ ወደ ደምቢዶሎ በረራ መጀመሩን፣ እስካሁን በረራዎች በሰላም መቀጠላቸውንና በሌላ በኩል የነቀምት ኤርፖርት ግንባታ መዘግየቱን ጠቁመዋል። 

‹‹እስካሁን ወደኋላ የቀረብን የነበረው የነቀምት ኤርፖርት ነበር። የነቀምት ኤርፖርት ግንባታ ያላለቀው ትንሽ ነገር ስለቀረን ነበር፡፡ አሁን ግንባታው ከ90 በመቶ በላይ ተጠናቋል። እሱ እንዳለቀልን ወደ ነቀምት በረራ እንጀምራለን፤›› ብለዋል። 

የኢትዮጵያ  አየር መንገድ እ.ኤ.አ በ2023 የመንገደኞች ቁጥር 13.88 ሚሊዮን መድረሱን፣ ይህም ከተቀዳሚው ዓመት 8.6 ሚሊዮን መንገደኞች ቁጥር ጋር ሲተያይ አምስት ሚሊዮን ያህል ጭማሪ ማስተናገዱን መረጃው ያሳያል። 

የመንገደኞች ቁጥር መጨመርን አስመልክቶ አቶ መስፍን በሰጡት ማብራሪያ፣ የአገር ውስጥ መንገደኞች ብቻ የሚስተናገዱበት ተርሚናል ላለፉት ሁለት ዓመታት የማዘመንና ማስፋፋት ሥራ ሲከናወን ቆይቶ ከሁለት ወራት በፊት ሥራ መጀመሩን አስታውሰዋል። 

‹‹ይህ ተርሚናል አገልግሎቱን በከፍተኛ ደረጃ የመንገደኞችን አገልግሎት ለማሻሻል ከማስቻሉም በላይ፣ መቀበል የሚችለውን ደንበኞች ብዛት ከእጥፍ በላይ አሳድጎታል፤›› ብለዋል። 

በሁለት ዓመት የዕድሳት ወቅት የአገር ውስጥ መንገደኞች በተርሚናል ሁለት ወይም ዓለም አቀፍ መንገደኞች በሚስተናገዱበት አገልግሎት ሲሰጣቸው መቆየቱንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል። በዚህ የአሠራር ሒደት ስላጋጠሙ ችግሮች ሲያስረዱም፣ ‹‹ያኔ ብዙ እሮሮ ነበር፡፡ የመንገደኞች መጨናነቅ፣ መገፋፋት፣ ግራ መጋባት፣ አንዳንድ ሰዎች ግልጽ መረጃ ባለማግኘት ምክንያት በረራቸው የሚያመልጣቸው አጋጣሚዎች ነበሩ። ያንን በማየታችንና የቦታ ጥበት በመኖሩ ነው ማስፋፊያ አድርገን እንደ አዲስ ሥራ የጀመርነው፤›› ብለዋል። 

በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፍ በረራውንም ለማካሄድ ተርሚናል ሁለት የአቅም ውስንነት እንዳጋጠመው ገልጸዋል። ‹‹የመንገደኛ ቁጥራችን በጣም በማደጉ ምክንያት ተርሚናል ሁለት በቅርብ ጊዜ የተስፋፋ ቢሆንም፣ ዛሬም መጨናነቅ አለው፤›› በማለት አስረድተዋል።

‹‹በተለይ በአዲስ አበባ በኩል አልፈው ወደ ሌሎች አገሮች ለሚተላለፉ (Transit) መንገደኞች አሁንም መጨናነቅ አለ። እሱን ለመፍታት ስንል በተርሚናል ሁለት በምሥራቅ በኩል ተጨማሪ የማስፋፊያ ሥራዎች እየሠራን ነው ያለነው፤›› ብለዋል፡፡ በአየር መንገዱ ዕቅድ መሠረት የማስፋፊያ ግንባታ በሰኔ መጨረሻ እንዲያልቅ ይጠበቃል። 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...