Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊተማሪዎች የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለዓለም ገበያ ማቅረብ የሚችሉበት ስምምነት ተደረገ

ተማሪዎች የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለዓለም ገበያ ማቅረብ የሚችሉበት ስምምነት ተደረገ

ቀን:

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለዓለም ገበያ የሚያወጡበትና አዳዲስ የምርምር ሥራዎችን የሚያደርጉበት ስምምነት ማድረጉን፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ስምምነቱን ያደረገው ፋሪስ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ከተሰኘ ተቋም ጋር መሆኑን፣ ማክሰኞ መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአምስት ዓመቱን ስትራቴጂ ለማሳካት ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል፣ ተማሪዎች የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ከግል ዘርፍ ጋር በጋራ መሥራት አንዱ መሆኑን፣ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የተለያዩ ዕውቀትና ክህሎት እንዳላቸው የገለጹት ተጣባባቂ ፕሬዚዳንቱ፣ ክህሎታቸውን ለማበልፀግና ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ስምምነቱ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

ተማሪዎች የፈጠራ ሥራቸውን ወደ ሀብት እንዲቀይሩ፣ እንዲሁም ያላቸውን ክህሎት እንዲያሳድጉ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ፕሮግራሞችን ቀርፆ እየሠራ መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊት ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የምርምና የፈጠራ ሥራዎችን በመቀበል መሬት አውርዶ በመሥራት ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት መቻሉን፣ የፋሪስ ቴክኖሎጂ ግሩፕ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤልያስ ይርዳው ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፈጠራ ሥራ ውጤቶችን ለዓለም ገበያ በማስተዋወቅ፣ ተማሪዎቹ ተወዳዳሪ የሚሆኑበትን ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተለይ በተለያዩ አገሮች የምርምር ሥራዎች ላይ ከተሳተፉ ተቋማት ጋር ቅንጅት በመፍጠር፣ አዳዲስ ምርምር ሥራዎችን ማከናወን የሚያስችል ስምምነት መደረጉን አብራርተዋል፡፡

ወጣቶች የፈጠራ ሥራቸውን ወደ ቢዝነስ እንዲቀይሩ ድጋፎችን ማድረግና ማበረታታት ድርጅቱ ከያዛቸው አጀንዳዎች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸው፣  ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተደረገው ስምምነት ለተማሪዎች መልካም ዕድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...