Monday, April 15, 2024
Homeስፖንሰር የተደረጉየአየርላንድ እና የኢትዮጵያ የ30 ዓመታት ግንኙነት ስናከብር

የአየርላንድ እና የኢትዮጵያ የ30 ዓመታት ግንኙነት ስናከብር

Published on

- Advertisment -

ዘንድሮ አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት የጀመረችበት 30ኛ ዓመት ቢሆንም ግንኙነቱ ግን ከዚያም በበለጠ ወደኋላ ይመለሳል። እ.ኤ.አ. በ1936 አየርላንድ ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ጎን በመቆም አገራቸው ላይ የተፈጸመውን ወረራ በመቃወም ለዓለም መንግስታት ማህበር (ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ) አቤቱታቸውን ካቀረቡት ሁለት አገሮች አንዷ ነበረች። ይህ እውነታም በአዲስ አበባ ከተማ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከሚገኙት ሃይማኖታዊ ሥዕሎች መካከል እንደ አንዱ ሆኖ እስከ ዛሬ ድረስ ይታያል።

አየርላንድ ራሷ ያሳለፈችውን የመከራ እና የረሃብ ጉዞ በማስታወስ የአየርላንድ መንግስት እ.ኤ.አ. በ1974 ዓ.ም. ዓለምአቀፍ የልማት ፖሊሲ እና መርሃ ግብር (ፕሮግራም) አቋቁሟል። ከዚህ ጊዜ ጀምሮም አየርላንድ ለበርካታ አገራት የልማትና የሰብዓዊ ድጋፎችን በማቅረብ ላይ የምትገኝ ሲሆን ኢትዮጵያም ትልቋ የአየርላንድ የሁለትዮሽ ድጋፍ ተቀባይ ሆናለች። ይህ አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ግንኙነት የሰጠችውን ከፍተኛ ዋጋ አመላካች ብቻ ሳይሆን የአየር ንብረት ለውጥ፣ የምግብ ዋስትና እጦት እና ግጭትን ተከትሎ ለሚመጡ ተግዳሮቶች አየርላንድ የምትሰጠውን እውቅና ማሳያም ነው።

እ.ኤ.አ. በ 1994 የአየርላንድ ኤምባሲ በአዲስ አበባ መከፈቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ከጤና፣ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ የአኗኗር ዘዴን ከመፍጠር ከማህበራዊ ጥበቃ ጋር በተያያዘ የሁለትዮሽ ተሳትፎ እና ልማት ትብብር በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር ሁኔታዎችን አመቻችታቷል። በቀጣዮቹ ዓመታትም አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት ከመዳበሩም ባሻገር በአሁኑ ወቅትም በተለይ የጾታ እኩልነትና የሰብዓዊ ተግባራት ላይ በማተኮር ግንኙነቱ ሰፊ የሆነ ዲፕሎማሲያዊ፣ የልማት ትብብር፣ የባህልና ንግድ ግንኙነቶችን በስፋት የሚሸፍን ሆኗል።

አየርላንድ ባለፉት 5 ዓመታት ውስጥ ብቻ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ዜጎችን ተጠቃሚ ለሚያደርግ የሁለትዮሽ የልማት ትብብር ከ200 ሚሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ንዋይ አፍሳለች። ለሰላም እና ለእርቅ አላማ ከሚሰጡ ድጋፎች ጋር ተዳምሮም በሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥ፣ በጤና እና በጾታ እኩልነት ላይ የሚደረገው ትብብር ለአየርላንድ−ኢትዮጵያ ግንኙነት ማዕከል ሆኖ ለወደፊቱም ይቀጥላል። እ.ኤ.አ. በ1970ዎቹ ግጭቶችን እና ብጥብጦችን እንዳሳለፈች አንድ አገር ይህ ድጋፍ በማህበረሰቦች ላይ የሚኖረውን ተፅእኖ አየርላንድ ጠንቅቃ ታውቃለች፤ ለዘለቄታውም ጠላትነት የማቆም ስምምነት ተግባራዊነት ድጋፏን ትቀጥላለች።

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶቻና ትስስር ዘላቂ ትስስሮች በአየርላንድ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም አማካኝነት በአየርላንድ በተማሩ ከ200 በላይ በሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ለመገንባት ተችሏል። እነዚህ ተማሪዎች ጥልቅ ወዳጅነት እና ዘላቂ የአካዳሚክ ግንኙነቶችን የገነቡ ከመሆናቸውም ባሻገር በኢትዮጵያ እድገትና ልማት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ ይገኛሉ። አየርላንድ በመስከረም 2017 ተጨማሪ አስራ ሁለት ተማሪዎችን ለመቀበል በጉጉት ትጠብቃለች።

በ2008 (እ.ኤ.አ. 2016) የቀድሞ የአየርላንድ ፕሬዝዳንት ሜሪ ሮቢንሰንን፣ በ2011 (እ.ኤ.አ. 2019)፣ ጠቅላይ ሚ/ር ሊኦ ቫርዳካርን፣ እንዲሁም በዚህ ወር የግብርና፣ የምግብ እና የባህር ጉዳዮች ሚኒስትር ቻርሊ ማኮናሎግ ቲዲን ጨምሮ በርካታ ጎብኚዎች አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በጥልቀት እንዲዳብር አድርገዋል። በአሁኑ ወቅት የአየር ንብረት ለውጥ እያሳደረ ከመጣው ከባድ ተግዳሮቶች አኳያ፣ የሚኒስትር ማኮናሎግ ጉብኝት ለዘላቂ የምግብ ስርዓት፣ ኢነርጂ እና ንግድ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ለማጠናከር ጥሩ ዕድል አስገኝቷል። እንዲህ ያለው የጋራ ቁርጠኝነት ለሚቀጥሉት ሰላሳ ዓመታትም የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ልዩ መለያ ምልክት እንደሚሆን እንጠብቃለን።

የቅርብ ጊዜ መጣጥፎች

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም በቶነር አሴምብሊንግ ስራ የተሰማራ ድርጅት...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት መኖር የመማር ማስተማር አንዱ ውጤት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣ ከሰብዓዊ ፍጡራንም አልፎ እንስሳትና አዕዋፋት፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ በሌሎች ዘርፎች እንደታየው በወርቃማ ዘመንነት...

ተመሳሳይ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም በቶነር አሴምብሊንግ ስራ የተሰማራ ድርጅት...

ኦርቶፔዲክስ

በጡንቻ መገጣጠሚያ እና የአጥንት ህመሞች ላይ የላቀ ጥበብ፡- የአጥንት ጉዳትን ችግር ከመመርመርም ያለፈ የአጥንትና መገጣጠሚያ...

የአየርላንድ ብሔራዊ ቀን – የቅዱስ ፓትሪክ ቀን – 2016 (እ.ኤ.አ. 2024)

“የቅዱስ ፓትሪክ ቀን ላይ ሆነን መጪውን ጊዜ ስንቃኝ” በእያንዳንዱ የቅዱስ ፓትሪክ ቀን በአለም ዙሪያ ያሉ...