Monday, April 15, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኅብረት ባንክ የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ባለድርሻ የሚያደርገውን የ50 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ድርሻ ገዛ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኅብረት ባንክ በቅርቡ ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ በሚጠበቀው የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ አክሲዮን ማኅበር ላይ 50 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ አክሲዮኖችን በመግዛት የኩባንያው ባለድርሻ ሆነ።

በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ አክሲዮን ማኅበርና በኅብረት ባንክ መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት ኅብረት ባንክ የገዛው የ50 ሚሊዮን ብር አክሲዮን በኩባንያው ውስጥ የአምስት በመቶ ባለድርሻ የሚያደርው መሆኑም ታውቋል፡፡

ይህ ስምምነት ከኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ አክሲዮን ማኅበር ላይ አክሲዮኖችን የገዙ ባንኮችን ቁጥር ከፍ ያደረገው ሲሆን፣ እስካሁን አክሲዮን መግዛታቸውን በይፋ ያሳወቁት ዘመን ባንክ፣ ስንቄ ባንክ፣ አዋሽ ባንክና ግሎባል ባንክ ሲሆኑ፣ ሌሎች ባንኮችም መጠኑ አነስተኛ ይሁን እንጂ አክሲዮኖችን ከኩባንያው ገዝተዋል፡፡ 

ከኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ አክሲዮን ማኅበር አክሲዮን መግዛታቸውን ያሳወቁት አራቱ ባንኮች አዋሽ፣ ኅብረት፣ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የ220 ሚሊዮን ብር አክሲዮን መግዛታቸውን ያመላክታል፡፡

ከመዋዕለ ንዋይ ገበያ አክሲዮን ማኅበር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ እስካሁን ካከሄደው የአክሲዮን ሽያጭ ማሰባሰብ የቻለው ካፒታል መጠን ከዕቅዱ በላይ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ 

አጠቃላይ የአክሲዮን ሽያጩን ለማካሄድ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ማርች 30 ቀን የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ በቀረበው ሁለት ሳምንታት ተጨማሪ አዲስ ኩባንያዎች ይንቀሳቀሳሉ ተብሎ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡ 

በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ መፈጠርን ተከትሎ የሚቋቋመው ይህ ኩባንያ፣ ለተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የኢንቨስትመንት ፈንድ ለማሰባሰብና ሌሎች ዘመናዊ የግብይቶችን ለማካሄድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ተብሎ የሚታመንበት ነው፡፡ ኩባንያ መፈጠር በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ ተጨማሪ የቢዝነስ እንቅስቃሴዎች እንደሚካሄዱ ያስችላል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ አክሲዮን ማኅበርን በኅብረት ባንክ መካከል የተፈጸመውን የአክሲዮን ግዥ ኅብረት ባንክን በመወከል የፈረሙት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ መላኩ ከበደ ናቸው፡፡ 

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ በኩል ደግም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን እስማኤል (ዶ/ር) ናቸው፡፡ ኅብረት ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ የቆየ የግል ባንክ ነው፡፡ የ2015 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ አጠቃላይ የሀብት መጠኑ ከ82.5 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡ በዚሁ የሒሳብ ዓመት አጠቃላይ የካፒታል መጠኑ 9.4 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ከታክስ በፊት 3.06 ቢሊዮን ብር ማትረፉ መገለጹ አይዘነጋም፡፡ 

የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑም 64.5 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ በዚሁ በ2015 የሒሳብ ዓመት መጨረሻ ላይ የብድር ክምችት መጠኑ 60.1 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች