Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለታላቁ አፍሪካ ሩጫ ተወዳዳሪዎች የአውቶሞቢል ሽልማት ተዘጋጀ

ለታላቁ አፍሪካ ሩጫ ተወዳዳሪዎች የአውቶሞቢል ሽልማት ተዘጋጀ

ቀን:

መቀመጫውን በሀገረ አሜሪካ ያደረገው የታላቁ አፍሪካ ሩጫ የሚል ትርጉም ያለው የግራንድ አፍሪካ ረን፣ እ.ኤ.አ. በ2024 በሚያደርገው ውድድር ለሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች አሌክሳንደሪያ ቶዮታ የመኪና ሽልማት ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

የዝግጅቱ ተሳታፊዎች አንደኛም ሆነ መጨረሻ ቢወጡ መኪናውን የማሸነፍ እኩል ዕድል እንደሚኖራቸው በዋሽንግተን ዲሲ ሰሞኑን በሰጠው መግለጫው ሲገልጽ፣ የመኪናው አሸናፊ የሚለየው በሩጫው ማጠቃለያ ላይ የሎተሪ ዕጣ በማውጣት እንደሆነ ጠቁሟል፡፡

አሌክሳንድሪያ ቶዮታ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት የግራንድ አፍሪካ ረን እና ኢምፓክት አዋርድን ለመጪዎቹ አራት ዓመታት የመጠሪያ ስፖንሰር በመሆን ለዳያስፖራው ማኅበረሰብ ያለውን አጋርነት በቅርቡ ማሳወቁ ይታወቃል። 

አሌክሳንድሪያ ቶዮታ ‹‹ቅድሚያ ለማኅበረሰብ›› የሚል መርሕን አንግቦ የሚንቀሳቀስ እንደሆነ ተገልጾ፣ ለረጅም ዓመታት ታማኝ ደንበኞቹ ሆነው ለቆዩት የዳያስፖራው ማኅበረሰብ አባላት ይህንን ዕድል በማቅረቡ የላቀ ደስታ እንደሚሰማው በመግለጫው ላይ ተጠቁሟል::

 ግራንድ አፍሪካ ረን በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ በሁለተኛው ቅዳሜ በዋሽንግተን ዲሲ የሚካሄድ ብዙኃኑን የሚያሳትፍ ዓመታዊ የ5 ኪሜ የጎዳና ላይ የመዝናኛ ሩጫ ነው። ‘አብሮነት መሻል ነው’ በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ ዝግጅት፤ የዘንድሮው ሩጫ ለ6ኛ ጊዜ የሚዘጋጅ ይሆናል።

ዝግጅቱ በሰሜን አሜሪካ ተወዳጅ ባህል እየሆነ የመጣ ሲሆን፣ የዳያስፖራው ማህበረሰብን ማሰባሰብ፣ የመጀመሪያው ትውልድ ልጆችን ከባህላቸው ጋር የበለጠ ማቀራረብ፣ እና ለተለያዩ በጎ አድራጎቶች ገቢ ማሰባሰብን ዓላማው አድርጎ የሚከናወን ነው።

በሺዎች የሚቆጠሩ የዳያስፖራው ማኅበረሰብ አባላት የሚሳተፉበት ይህ ዝግጅት የዘንድሮን ምዝገባ በግንቦት መጨረሻ አንደሚጀመር አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

ባለፉት አምስት የግራንድ አፍሪካ ረን ዝግጅቶች፣ ብርቅዬ አትሌቶች ደራርቱ ቱሉ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ገንዘቤ ዲባባ፣ ስለሺ ስህን፣ ሚሊዮን ወልዴ፣ በላይነህ ዴንሳሞ፣ ፋጡማ ሮባ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ ቁጥሬ ዱለቻ እና ሌሎችም በክብር እንግድነት ተገኝተውበታል። በዚህም ዓመት ተመሳሳይ ደረጃ ያላቸው አትሌቶች በዝግጅቱ ላይ እንደሚገኙ በመግለጫው ላይ ተነስቷል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...