Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዛሬ የሚካሄደውና 21ኛ ዓመቱ ላይ የደረሰው የሴቶች ታላቁ ሩጫ

ዛሬ የሚካሄደውና 21ኛ ዓመቱ ላይ የደረሰው የሴቶች ታላቁ ሩጫ

ቀን:

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚያዘጋጀውና ሴቶች ብቻ የሚወዳደሩበት የ5 ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር ዛሬ እሑድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል፡፡

የ2016 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የሚል መጠሪያ ባለው የ5 ኪ.ሜ ሩጫ 16 ሺሕ ተሳታፊዎች እንደሚሳተፉበት ታውቋል፡፡

ታላቁ ሩጫ እንዳስታወቀው ‹‹የሴቶችን አቅም እንደግፍ፤ ለውጥን እናፋጥን›› በሚል መሪ ቃል የሚደረገው የዘንድሮው ውድድር የተሳታፊ ቁጥር በሁለት አሠርታት ውስጥ ትልቁ ሲሆን፣ ለተሳትፎ ከሚሮጡት ባሻገር በአምስት ዘርፎች የሚወዳደሩ ተካተዋል፡፡

እንደ ወትሮው ውድድር በክለብ የታቀፉና በግል የሚወዳደሩ አትሌቶችም የውድድሩ ድምቀት ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከአገር ውስጥ በተጨማሪ ከተለያዩ አገሮች የሚመጡ አርባ ሰዎችም በውድድሩ ይሳተፋሉ፡፡ የኢትዮጵያና አየርላንድ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረበት 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከአገራቸው የመጡ 35 አየርላንዳውያን እንደሚሳተፉ፣ በአጋጣሚውም በቅርቡ ያከበሩትን የቅዱስ ፓትሪክ ዓመታዊ በዓልን የሚያንፀባርቁበት ትርዒት ያሳዩበታል ተብሏል፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የዘንድሮውን የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ምዝገባ መክፈቻና የ21ኛ ዓመት ምሥረታ በዓልን አስመልክቶ ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ሰጥቶት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያና አጋሮቹ በሴቶች ዙሪያ ለሚከናወኑ ተግባራት እያደረጉት ላለው ድጋፍ  ማመስገናቸው አይዘነጋም።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዳግማዊት አማረ ባለፉት 21 ዓመታት የሴቶችን ስኬት ለማክበር፣ ሴቶችን ለማብቃትና ማኅበራዊ መልዕክቶች ለማስተላለፍ፣ እርስ በእርስ ልምድ ለመለዋወጥ እንዲሁም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሴቶችንና በጎ አድራጎት ተቋማትን ለመደገፍ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ የውድድሩ ተሳታፊዎች ቁጥርም ከ4500 አሁን ላይ 16 ሺሕ መድረሱም ትልቅ ስኬት መሆኑም ሳይጠቁሙ አላለፉም።

ከዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ጋር በማስተሳሰር ‹‹የሴቶችን አቅም እንደግፍ፣ ለውጥን እናፋጥን በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ውድድሩ፣ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የፌስቡክ ገጽና በኢቢሲ መዝናኛ ከጧቱ 1፡30 ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት እንደሚተላለፍ አዘጋጁ አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...