Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኢትዮጵያ አርታኢያን ማኅበር በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን መከታተል የሚያስችለውን ድረ ገጽ ይፋ...

የኢትዮጵያ አርታኢያን ማኅበር በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን መከታተል የሚያስችለውን ድረ ገጽ ይፋ አደረገ

ቀን:

የኢትዮጵያ አርታኢያን ማኅበር (ኢአማ) በመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከታተልና ለመመዝገብ የሚያስችል ድረ ገጽ ወይም ‹‹ፖርታል›› አዘጋጅቶ በሥራ ላይ ማዋሉን አስታወቀ፡፡

ማኅበሩ በአገር አቀፍ ደረጃ በመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በመከታተልና በመመዝገብ በየሦስት ወራት ለሚመለከታቸው ተቋማት ሪፖርት ለማቅረብ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን፣ ሐሙስ መጋቢት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

በድረ ገጹ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት ሳይንስና ባህል ድርጅት (UNESCO) ድጋፍ፣ በኢትዮጵያ አርታኢያን ማኅበር ተዘጋጅቶ በሥራ ላይ መዋሉ ተገልጿል፡፡

የማኅበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ጋዜጠኛ ፍሬው አበበ በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ላይ የሚደርሱ ማስፈራሪያዎች፣ እስራትና እንግልቶችን ለማስቀረት የተዘጋጀ ፖርታል ነው ብሏል፡፡

በማኅበሩ ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ የዋለው  ፖርታል በመጀመሪያ ምዕራፍ በሦስት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ በኦሮሚኛና በእንግሊዝኛ መዘጋጀቱን አስረድቷል፡፡

በማኅበራዊ ሚዲያና በሌሎች መንገዶች የሚደረጉ ማንቋሸሽ፣ ዘለፋ፣ ስም ማጥፋትና መሰል ጉዳዮችን በመመዝገብ፣ በማጣራትና ለቀጣይ ውትወታ ሥራዎች ግብዓት በመሰብሰብ መገናኛ ብዙኃን ነፃነታቸው ተጠብቆ እንዲንቀሳቀሱ ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥር መሆኑን ተናግሯል፡፡

በተለይም የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ሥራቸውን በሚሠሩበት ወቅት የሚደርስባቸውን ማስፈራሪያና የመሳሰሉ ክስተቶች ሲያጋጥሙ ከመከታተልና ከመመዝገብ በተጨማሪ፣ ሴት ጋዜጠኞች በሥራ ቦታቸውም ሆነ በጋዜጠኝነት ጉዟቸው ላይ የሚደርሱባቸውን ፆታዊ ጥቃቶችን ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ መንገድ የሚመዘግብና መፍትሔ ለመፈለግ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የሚያመቻችበት ማዕቀፍ ነው ተብሏል፡፡

‹‹በመንግሥትም ሆነ በተደራጁ ቡድኖች በመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የሚደርሱ ጥቃቶች መኖራቸው የሚታወቅ ነው፤›› ያለው የቦርድ ሰብሳቢው፣ እነዚህን ጥቃቶች ለማስቀረትና ለችግሩ መፍትሔ ለመስጠት የተዘጋጀው ውጥን ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብሏል፡፡  

‹‹የኢትዮጵያ ኢርታኢያን ማኅበር ያዘጋጀው ፓርታል የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ብቻ የሚጠቀሙበት ነው፤›› ያሉት ደግሞ የማኅበሩ የጠቅላላ ጉባዔ ሰብሳቢ አቶ ፍትሕአወቅ የወንድወሰን ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ አብዛኛውን ጊዜ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ሲታሰሩም ሆነ የተለያዩ በደል እንደደረሰባቸው ሪፖርት የሚያደርጉት ዓለም አቀፍ ተቋማት መሆናቸውን አስታውሰዋል፡፡

የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የሚደርስባቸውን በደልና እንግልት ሪፖርቶችን ለማጠናከር ፖርታሉ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸው፣ በድረ ገጹ ላይ ጋዜጠኞች እንዲህ ዓይነት በደል ደርሶብኛል በሚሉበት ወቅት የደረሰባቸውን በደል የሚከታተል ኮሚቴ መዋቀሩን አብራርተዋል፡፡

በዚህ መሠረት ማኅበሩ በጣም አስቸኳይ የሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙት በፍጥነት ሪፖርት የሚያደረግ መሆኑን የገለጹት አቶ ፍትሕአወቅ፣ በቀጣይ የተሻሉ ነገሮችን ለመሥራት ማኅበሩ ሰፊ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ አስረድተዋል፡፡

በመንግሥትም ሆነ በቡድን የሚደርሱ በደሎችን በግልጽ ሪፖርት በማድረግና በደሎችን በመዘርዘር ለሕግ አካላትና ለሚመለከታቸው ተቋማት ማኅበሩ ሪፖርቱን እንደሚያቀርብ ተናግረዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...