Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየመልቲሞዳል ፈቃድ ለግል ድርጅቶች ቢሰጥም ለኢባትሎአድ የሚደረገው ልዩ ድጋፍ እንደሚቀጥል ተገለጸ

የመልቲሞዳል ፈቃድ ለግል ድርጅቶች ቢሰጥም ለኢባትሎአድ የሚደረገው ልዩ ድጋፍ እንደሚቀጥል ተገለጸ

ቀን:

የመልቲሞዳል ትራንስፖርት ለግሉ ዘርፍ ክፍት ከተደረገ በኋላ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሦስት አገር በቀል ድርጅቶች ፈቃድ ቢሰጥም፣ በዘርፉ በብቸኝነት እያገለገለ ላለው ለኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት (ኢባትሎአድ) የሚጠው የፖሊሲ ድጋፍ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያን የመልቲሞዳል ሎጂስቲክስ አገልግሎት ጠቅልሎ በብቸኝነት እያገለገለ የነበረው ኢባትሎአድ የገበያ ተቀናቃኞች የመጡበት ቢሆንም፣ ብቸኛ አገልግሎት ሰጪ እያለ ያገኛቸው የነበሩ አንዳንድ የፖሊሲ ከለላዎች ሳይነሱበት የሚቀጥሉ ነው መሆናቸው ታውቋል፡፡

የሎጂስቲክስ ዘርፉን ሙሉ በሙሉ ለተወዳዳሪ ክፍት የማድረግ ውሳኔ በፖሊሲ ከተወሰነና ይህንን ውሳኔ ማስፈጸሚያ መመርያውም በ2013 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ፀድቆ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ፣ በርካታ ድርጅቶች ፍላጎት እያሳዩ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ላለፉት ሁለት ዓመታትም በኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን በወጡት ማስታወቂያዎችም መሠረት በርካታ ድርጅቶች የሚጠይቀውን መሥፈርት በማሟላት የመወዳደር ፍላጎት ሲያሳዩ ነበር፡፡ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የመጀመሪያው ውድድር ማንም ድርጅት ሳይመረጥ ቀርቶ በተያዘው ዓመት በተደረገው ውድድር ሦስት ድርጅቶች ተመርጠዋል፡፡

ከስምንት ተወዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛውን ነጥብ በማምጣት የተመረጡ ሦስቱ ድርጅቶች፣ ፓንአፍሪክ ግሎባል ሎጅስቲክስ፣ ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት፣ እንዲሁም ኮስሞስ መልቲሞዳል ሎጂስቲክስ የተባሉ ድርጅቶች ናቸው፡፡ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና ምክትላቸው አቶ ዳንጌ ቦሩ፣ እንዲሁም የማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አብዱልበር ሸምሱ (ኢንጂነር) በተገኙበት የሦስቱ ተቋማት ኃላፊዎች ባለፈው ረቡዕ መጋቢት 4 ቀን 2016 ዓ.ም. በሸራተን ሆቴል በተካሄደው መርሐ ግብር ፈቃዳቸውን ወስደዋል፡፡

የፈቃድ አሰጣጡ ሥነ ሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ የማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አብዱልበር (ኢንጂነር) እንደገለጹት፣ የመልቲሞዳል ፈቃዱን ለተጨማሪ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ተሰጠ ማለት ሙሉ ለሙሉ ሁሉም መዳረሻዎች ላይ እነዚህ ድርጅቶች ይሠራሉ ማለት እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡

‹‹አሁን ላይ በተወሰነ መስመር ላይ ነው የሚሠሩት፣ ሌላ መስመሮችን ከድርጅቶቹ ጋር ተነጋግረን ነው የምንሰጣቸው፤›› ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ‹‹በሒደት እያየን ነው እየለቀቅን የምንሄደው፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

እንደ ቻይና፣ ህንድና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ዓይነት የተለያዩ የሚታወቁና ትራፊክ የሚበዛባቸው የንግድ መስመሮች መኖራቸውን ያስታወሱት አብዱልበር (ኢንጂነር)፣ ከእነዚህና ተጨማሪ መስመሮች በመምረጥ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚያደርግና አቅማቸው እያደገ ሲሄድ ደግሞ በጊዜ ሒደት ሙሉ ለሙሉ ክፍት እንደሚረግላቸው ነው ያስረዱት፡፡ ‹‹እስከዚያ ድረስ ግን የፖሊሲ ከለላው ለኢባትሎአድ የሚቀጥል ይሆናል፤›› ብለዋል፡፡

ፈቃድ የተሰጣቸው ሦስቱ ድርጅቶች በስድስት ወራት ውስጥ ሥራ እንደሚጀምሩ እንደሚጠብቁ፣ እንደዚያ ካላደረጉ ግን ፈቃዳቸውን እስከመንጠቅ ድረስ አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንደሚወሰድባቸው ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹት፡፡

ፈቃድ ከተሰጣቸው ድርጅቶች አንደኛው የሆነው የፓንአፍሪክ ግሎባል ዋና ሥራ አስፈጻሚና የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ዘርፍ ማኅበር ፕሬዚዳንት የሆኑት ወ/ሮ ኤልሳቤት ጌታሁን ለሪፖርተር እንዳስረዱት፣ ቀሪዎቹን የዝግጅት ሥራዎች በማጠናቀቅ ሥራ ለመጀመር ስድስት ወራት ሙሉ ሊወስድባቸው እንደማይችል ነው፡፡

ወ/ሮ ኤልሳቤጥ አሁን ተቀናቃኝ የሚሆኑትን ኢባትሎአድ መንግሥት በፖሊሲ መደገፍ መቀጠሉን በሚመለከት ሲናገሩ፣ ‹‹ኢባትሎአድ በፖሊሲ የሚደገፍ ከሆነ እኛንም የሚጠቅም ይሆናል ብዬ ነው የማምነው፤›› ያሉ ሲሆን፣ ይህ የማይሆን ከሆነም ደግሞ ‹‹ዓይተን ችግሩን ለመንግሥት የምናቀርብ ነው የሚሆነው ይህ ትልቅ ዕድል ነው፡፡ ከችግሩ ዕድሉ ነው የሚታየኝ፤› ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...