Monday, July 22, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከ6 ሺሕ በላይ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የተለመው ኦቪድ ግሩፕ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ በአሁኑ ወቅት በርከት ባሉ ኢንቨስትመንቶች የተሰማራው ኦቪድ ግሩፕ በእህት ኩባንያ ኦቪድ በሪል ስቴት በኩል ከ60 ሺሕ በላይ የመኖሪያ ቤቶችን እየገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኦቪድ ግሩፕ እህት ኩባንያ የሆነው ኦቪድ ሪል ስቴት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገነባቸወን አራት የዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ልማት ፕሮጀክቶችን ይፋ ባደረገበት ፕሮግራም ላይ እንደተገለጸው፣ በአሁኑ ወቅት 62 ሺሕ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታዎች በእጁ እንዳሉ አስታውቋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑትን ግንባታዎች በማካሄድ ላይ ነው፡፡

መጋቢት 1 ቀን 2016 ዓ.ም. የአራቱን የመኖሪያ ቤት ፕሮጀክቶች የማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ እንደተገለጸው፣ እነዚህ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ፕሮጀክቶች በአራት ምድብና ሳይት የተካተቱ ሲሆኑ፣ በዕለቱ ለሕዝብ ለሽያጭ የቀረበው ጫካ መኖሪያ ቤት ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ጫካ ፕሮጀክት ውስጥ በግንባታ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ 1,900 ቤቶችን የያዘ ነው፡፡ እነዚህ ቤቶች ባለ አንድ፣ ባለ ሁለትና ባለ ሦስት መኝታ አፓርትመንቶችን ይይዛሉ፡፡ ይህ ፕሮጀክት ዘጠኝ ሔክታር በሚሸፍን ሰፊ የከተማው አረንጓዴ መስክ ላይ የሚለማ መሆኑ ታውቋል፡፡

ኩባንያው የሚገነባው ሌላው የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ሐረር ሆራይዘን ፕሮጀክት የሚል መጠሪያ ያለው ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ ከተማ ስምንት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና ባለ ሁለትና ባለ ሦስት መኝታ ቤት ዘመናዊ አፓርትመንቶችን የሚይዙ ናቸው፡፡

ኪንግስ ታወር የሚል መጠሪያ ያለው ሌላው የኦቪድ ሪል ስቴት ፕሮጀክት ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ግንባታዎችን የያዘ ሲሆን፣ ከሌሎች ፕሮጀክቶቹ ለየት ብሎ የሚሠራ ነው፡፡ ኪንግስ ታወር 1,740 ሰፋፊ መኖሪያዎች ባለ አንድ፣ ባለሁለት፣ ባለሦስትና ባለ አራት መኝታ አፓርትመንቶችን የያዙ ናቸው፡፡

አራተኛው አፍሪካን ሃይትስ የሚል መጠሪያ ያለው ፕሮጀክቱ፣ በአዲስ አበባ ውስጥ እጅግ ያሸበረቀና ሁለገብ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ባለአንድ፣ ባለሁለት፣ ባለሦስትና ባለአራት መኝታ ቤት አፓርትመንት ጨምሮ 324 ቤቶችን የያዘ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

እነዚህ ሁሉን አቀፍና ዘመናዊ የቤት ልማት ፕሮጀክቶች የአዲስ አበባን ልዩ ባህልና ውበት ለመጠበቅና ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው የሚያመለክተው የኩባንያው መረጃ፣ ኦቪድ በእነዚህ ፕሮጀክቶቹ ለቤት ልማት ኢንዱስትሪው ዕድገትና ልህቀት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚደረገውን ጥረት ማሳያም እንደሚሆን አክሏል፡፡

የኦቪድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ ታደሰ የኦቪድ ግሩፕ እህት ኩባንያዎች ዋና ዓላማ ኢትዮጵያን ማልማት ነው፤›› ብለዋል፡፡

ግሩፑ 64 ሺሕ ቤቶች እያለማ መሆኑን በመግለጽ እስካሁንም 90 በመቶ የሚሆኑት በመንግሥትና በግል አጋርነት የሚለሙ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ኩባንያው እነዚህን ሥራዎች ትውልድ ኩባንያዎቹንና የውጭ ኩባንያዎችን በማሳተፍ ጭምር የሚሠራው ነውም ተብሏል፡፡  

በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙ የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ግርማ ሰይፉ፣ ኦቪስ ከተማውን የቤት ችግር ለማቃለልና ሥራዎችን በቶሎ ሠርቶ በማስረከብ በምሳሌነት የሚጠቀስ በመሆኑ፣ እዚህንም ፕሮጀክቶች በወቅቱ ያስረክባል የሚል እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

ለግንባታው ዘርፍ አርዓያ መሆን መቻሉን ጭምር የገለጹት አቶ ግርማ ኦቪድ በ90 ቀናት ባለአሥራ አንድ ወለል ሕንፃ በማስረከብ አርዓያ መሆን የቻለ ነው ብለዋል፡፡ ይህንኑ ተግባር መደጋገማቸውን አቶ ግርማ ገልጸዋል፡፡፡ ሌሎችም ተቋማት ይህንን አርዓያነት እንዲከተሉም ጥሪ አድርገዋል፡፡

ኦቪድ ሪልስቴት በይፋዊ ሥራ ማስጀመሪያው ዕለት ለአንድ ቀን ብቻ የሚቆይ ልዩ የቤቶች ሽያጭ እስከ አራት በመቶ ድረስ በታላቅ ቅናሽ በማድረግ ባዘጋጀው የሽያጭ መርሐ ግብር ከ1,500 በላይ  ቤቶችን ቤት ፈላጊዎችን መመዝገብ ችሏል፡፡ እነዚህ ተመዝጋቢዎች 40 በመቶ የቤት ዋጋ ቅናሽ የሚያገኙ ሲሆን፣ 100 የሚሆኑት ደግሞ ሙሉ የቤት ዕቃ ተሟልቶላቸው የሚረከቡበት ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኦቪድ ሪል ስቴት 60 ሺሕ ቤቶችን የያዘ አዲስ የመኖሪያ መንደር ለመገንባትም እየተዘጋጀ ሲሆን፣ ይህ መንደር ራሱን የቻለ ከተማ ይፈጥራል ተብሎ የታሰበ ነው፡፡ ለዚህ ግንባታ የሚሆን ቦታም የተከረበ በመሆኑ አጠቃላይ ፕሮጀክቱ ይዘት በቅርቡ ይፋ ይደርጋል ተብሏል፡፡

 በላይ ወጪ የሚጠይቅ አዲስ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡ ይህ አንድ ከተማ የመመሥረት ያህል ይቀጥላል የተባለውን ይህንን ፕሮጀክት በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግም ተገልጿል፡፡

ኦቪድ ግሩፕ በሥራ ከአሥር በላይ ኩባንያዎች ያሉት ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ ኩባንያዎች ከኮንስትራክሽን ኩባንያውና ከሪል ስቴት ኩባንያው ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን የሚያመርቱ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ቢዝነሶች ባሻገር ኩባንያው ዋነኛ ባለድርሻ የሚሆኑበት ባንክ በመሠራት ላይ ይገኛል፡፡

ኩባንያው ከአሥር ዓመታት በላይ የቆየ ሲሆን፣ በኮንስትራክሽን ኩባንያው በኩል የቤቶች ኮርፖሬሽን የመኖሪያ ቤቶች ግንባታዎችን ማካሄዱ ይታወቃል፡፡ ከዚህም ሌላ በአሁኑ ወቅት እየተገነባ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴዓትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሕንፃ ግንባታን ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየገነባ ባለው እንቅስቃሴም የኬብል ትራንስፖርት ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በራሱ ባለቤትነት ከሚገነባቸው የሪልስቴት ግንባታዎች ባሻገር ከጎህ ቤቶች ባንክ ጋር ባደረገው ስምምነት  መሠረት በ1.4 ቢሊዮን ብር ከ200 በላይ ቤቶችን ለመገንባት ተስማምቷል፡፡

ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንፃር 500 ቤቶን በነፃ በመገንባት ማስተላለፉም ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች