Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየሊቢያ ተፃራሪ መሪዎች የተስማሙበት አዲስ ጥምር መንግሥት ምሥረታ

የሊቢያ ተፃራሪ መሪዎች የተስማሙበት አዲስ ጥምር መንግሥት ምሥረታ

ቀን:

በሊቢያ እ.ኤ.አ. በ2011 የተቀሰቀሰው የዓረብ አብዮት፣ የአገሪቱን መሪ ሙአመር ጋዳፊ ሕይወት ከመንጠቅ ባለፈ፣ ለአገሪቱ ያመጣው ዴሞክራሲያዊ ለውጥ የለም፡፡ አገሪቱ ላለፉት 13 ዓመታትም ሰላሟን አጥታ ከርማለች፡፡

በየጎራው ትጥቅ አንስተው የተሠለፉ ዜጓቿ መስማማት አቅቷቸውም፣ የአፍሪካ የነዳጅ ማማ የነበረችውን ሊቢያ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ከተዋታል፡፡ አገሪቱ በማይስማሙ ሁለት መንግሥታት እንድትመራም ሆኗል፡፡ የውክልና ጦርነት መናኸሪያና የተለያዩ ኃያላን አገሮች ፍላጎት መፈጸሚያም ሆናለች፡፡  

የሊቢያ ተፃራሪ መሪዎች የተስማሙበት አዲስ ጥምር መንግሥት ምሥረታ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የሊቢያ ሦስት መሪዎች በግብፅ በዓረብ ሊግ ዋና ጸሐፊ አህመድ አቦል የተመራውን ውይይት ተካፍለዋል (አሶሺዬትድ ፕሬስ)

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሙአመር ጋደፊ ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ፣ በተለያዩ ጎራዎች የተሠለፉ ታጣቂዎችንና መሪዎቻቸውን ለማስማማትና ሰላም ለማስፈን የተባበሩት መንሥታት ድርጀት (ተመድ)፣ የዓረብ ሊግና ሌሎችም ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ከርሟል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ዛሬ ላይ አገሪቱ በሦስት ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎችም ትመራለች፡፡ መቀማጫቸውን ትሪፖሊ ያደረጉት የፕሬዚዳንት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አል መንፊ፣ የከፍተኛ መንግሥት ምክር ቤት መሪ ሞሐመድ ታካላ እንዲሁም በቤንጋዚ የሚገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቃል አቀባይ አጉሊያ ጎላህ የሊቢያ ሦስት ቁልፍ መሪዎች ናቸው፡፡

መሪዎቹ በዓረብ ሊግ ጋባዥነት በግብፅ ካይሮ በተደረገ ውይይት የተሳተፉ ሲሆን፣ የተከፋፈለችውን ሊቢያ ለመታደግም ጥምር መንግሥት መመሥረት በሚለው የመፍትሔ ሐሳብ ላይ መስማማታቸውን ዘ ናሽናል ዘግቧል፡፡

ከ10 ዓመታት በላይ የፈጀውን የሊቢያ ፖለቲካዊ ቀውስ ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2021 ታኅሣሥ በተመድ የሚደገፍ ምርጫ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ በምርጫ ሕጎችና በዕጩዎች ብቃት ላይ በተነሱ ግጭቶች ምክንያት ሳያሳካ ቀርቷል፡፡ ይህም ሊቢያ በምዕራብ ሊቢያ ትሪፖሊ እንዲሁም በምሥራቅ ቤንጋዚ በተቀመጡ ተቀናቃኝ መንግሥቶች እየተመራች እንድትቀጥል አድርጓል፡፡

ይህንን የተስተጓጎለ ምርጫ ዳግም ለማስፈጸምና በአገሪቱ ሰላም ለማስፈን መንግሥት በማስፈለጉም፣ የጥምር መንግሥት እንዲመሠረት በሁለቱ ከተሞች የሚኖሩት መሪዎች ተስማምተዋል፡፡

እሑድ መጋቢት 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በካይሮ የተደረሰውን ስምምነት፣ ‹‹ወሳኝ ጅማሮ›› ሲሉ የፕሬዚዳንታዊ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት አል መንፊ ተናግረዋል፡፡

ትሪፖሊ የሚገኙት በቤንጋዚ ያለውን፣ በቤጋዚ ያለው በትሪፖሊ ያሉትን መንግሥቶች ዕውቅና የማይሰጡ በመሆኑም፣ የጥምር መንግሥት መመሥረቱ በፖለቲካና በአመራር ጽንፍ የረገጡትን የሊቢያ ፖለቲከኞች ወደ አንድ ለማምጣት ያስችላል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2011 የሊቢያውያን መሪ ሙአመር ጋዳፊን ከሥልጣን ካወረደውና ለግድያቸው ምክንያት ከሆነው የዓረብ አብዮት ማግሥት ጀምሮ፣ ላለፉት አሥራ ሦስት ዓመታት በእርስ በርስ ጦርነትና በውጭ ጣልቃ ገብነት ስትፈተን የከረመችው ሊቢያ፣ ኢኮኖሚዋ ወድቋል፣ ከተሞቿ ፈራርሰዋል፣ ነዋሪዎቿ በስቃይ ውስጥ ከርመዋል፣ በርካቶች ሞተዋል፣ ተሰደዋል፡፡

አላባራ ባለው ጦርነት ውስጥም ሊቢያውያን ተከፋፈለው ከርመዋል፡፡ ችግራቸውን ይፈታል የተባለው ምርጫ በ2021 ይካሄዳል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ሳይሳካ መቅረቱ ይታወሳል፡፡ በጦርነቱ አገራቸው መፈራረሷን፣ አንድነታቸው መፍረክረኩን፣ ለችግር መጋለጣቸውን በመግለጽም ‹‹የጋዳፊ አስተዳደር ይሻለን ነበር፤›› ያሉም ነበሩ፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...