Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአፍሪካ ጨዋታዎች በአክራ

የአፍሪካ ጨዋታዎች በአክራ

ቀን:

እንደ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች በየአራት ዓመቱ የሚካሄደው የአፍሪካ ጨዋታዎች፣ በጋና አስተናጋጅነት ከዓርብ የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሦስት ከተሞች እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ 54 አገሮች ብሔራዊ ቡድኖቻቸውን እያወዳደሩ ይገኛሉ፡፡

በአክራ፣ ኩማሲ እና ኬፕ ኮስት ከተሞች ለ13ኛ ጊዜ የሚካሄዱት አኅጉራዊው ጨዋታዎች 29 ስፖርቶችን ያካተቱ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በዘጠኝ ስፖርቶች ትፎካከራለች፡፡

የአፍሪካ ጨዋታዎች በአክራ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
በዋና ደረት ቀዘፋ ለፍጻሜ የደረሰችው ብርሃን ደመቀ

ይህ የመድበለ ስፖርታዊ ውድድር መካሄድ የነበረበት እ.ኤ.አ. በ2023 ቢሆንም ወደ ዘንድሮ እንዲራዘም የተደረገው መሠረተ ልማቱ ባለመሟላቱ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የአፍሪካ ጨዋታዎች በጋና ርዕሰ መዲና አክራ ባለፈው ዓርብ ምሽት የተከፈተው በጋና ፕሬዚዳንት ናና ዳንኩዋ አኩፎ አዶ አማካይነት ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው የአፍሪካ ጨዋታዎች፣ በአኅጉር ዙሪያ የአንድነት፣ የስፖርታዊ ጨዋነትና ብልጫ ያለው መድረክ ነው ማለታቸው ተዘግቧል።

‹‹ዛሬ እዚህ በተሰባሰብንበት ወቅት እንደ አፍሪካውያን በውስጣችን ያለውን አስደናቂ ችሎታና መንፈስ ለማሳየት፣ አገሮች ተሰባስበው የውድድርና የፉክክር ጉዞአቸውን ጀምረዋል፤›› ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። ልዩነትን ማክበር ለጋራ ማንነታችን ጥንካሬን እንደሚያመጣ እንገነዘባለን በማለት ጭምር፡፡

የአፍሪካ ጨዋታዎች በአክራ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ዋናተኞቹ ውድድራቸውን ሲጀምሩ

‹‹የአፍሪካን ህልም እንወቅ›› በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች በ29 የስፖርት ዘርፎች ከ4,000 በላይ አትሌቶች ይሳተፉበታል፡፡ ለዘንድሮው የፓሪስ ኦሊምፒክ ለማለፍ በማጣሪያነት የሚገለግሉ ስምንት ስምንት ስፖርቶች ይገኙበታል።

 የአፍሪካ ጨዋታዎች ከአኅጉሪቱ የተውጣጡ አትሌቶችን በየአራት ዓመቱ ያገናኛል። ውድደሮቹን በበላይነት እንደሚመራው የአፍሪካ ኅብረት አገላለጽ ከሆነ፣ ዝግጅቱ የአትሌቶችን ተሰጥኦዎችን ለማሳየት፣ የአፍሪካን ባህላዊ እሴቶችና ቅርሶች ለማክበር እንዲሁም አብሮነትን ለማስፈን እና ውህደትን ለመፍጠር ያለመ ነው።

ቀደም ሲል ‹‹የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች›› በመባል የሚታወቁት ጨዋታዎች ከኦሊምፒክ በፊት ባለው ዓመትን ተንተርሰው በየአራት ዓመቱ ይካሄዳሉ። ዘንድሮ 52 አገሮች እየተወዳደሩ ሲሆን፣ ይህም ትክክለኛው የመላው አፍሪካ ስፖርታዊ ውድድር መሆኑን ያሳየ ነው።

እ.ኤ.አ. በ2019 በሞሮኮ በተካሄደው የአፍሪካ ጨዋታዎች የነበሩት ስፖርቶች 26  ሲሆኑ ዘንድሮ በሦስት ጭማሪ አሳይቷል። በ2015 ጨዋታዎች የነበሩት 22 ስፖርቶች ናቸው፡፡

በዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ይፋዊ እውቅና ያለውን አኅጉራዊው የመድበለ ስፖርታዊ ውድድሩ በአፍሪካ ኅብረት፣ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) እና የአፍሪካ ስፖርት ኮንፌዴሬሽኖች ማኅበር በጋራ ተዘጋጅቷል።

የመጀመሪያዎቹ አሥራ አንድ ጨዋታዎች የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ሲባሉ የነበረ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ የአፍሪካ ጨዋታዎች ተብሎ ተሰይሟል።

የኢትዮጵያ ተሳትፎ

ኢትዮጵያ ከምትሳተፍባቸው አንዱ ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች መካከል በሚደረገው የሴቶች እግር ኳስ ነው፡፡ በኬፕ ኮስት ስታዲየም በነበረው የመክፈቻ ጨዋታ ‹‹ጥቋቁሮቹ ልዕልቶች›› የሚል ቅጽል ስም ካለው የጋና ሴት ብሔራዊ ቡድን ጋር የተጫወተው ብሔራዊ ቡድኑ 1ለ0 ተረቷል፡፡ እንደ ዲደብሊው ዘገባ፣ የኢትዮጵያ ቡድን በተከላካይ እና ግብ ጠባቂ ያለመግባባት በተፈጠረ ስህተት ነው በጋና ቡድን የተሸነፈው፡፡

በሴቶች 100ሜ የደረት ቀዘፋ ዋና ውድድር የተሳተፈችው ብርሃን ደመቀ ለፍፃሜ ማለፏ ታውቋል፡፡ ብርሃን ደመቀ ውድድሩ ጥሩ እንደሆነና መልካም ተሞክሮ እንደወሰደች እንዲሁም የራሷንም የግል ሰዓት ማሻሻል እንደቻለች ለሚዲያው ተናግራለች፡፡

ለሁለት ሳምንታት በሚዘልቀው ውድድር ከሚኖሩት ስፖርቶች ብስክሌት፣ የጠረጴዛ ቴኒስ፣ የሜዳ ቴኒስ፣ የመረብ ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ ነፃ ትግል፣ ባድሜንተን፣ ዋና፣ ጁዶ፣ ቴኳንዶ ይገኙበታል፡፡

በመጋቢት መባቻ በተካሄደው በ100 ኪሎ ሜትር የወንዶች የብስክሌት ውድድር የኢትዮጵያ ቡድን በ10ኛነት አጠናቀዋል። ቀጣዩ ውድድር መጋቢት 3 ቀን በወንዶች 59 ኪ.ሜ እና በሴቶች 56 ኪ.ሜ ውድድር የተከናወነ ሲሆን አስቀድመን ማተሚያ ቤት ስለገባን ውጤቱ ይዘን መውጣት አልቻልንም፡፡

ኢትዮጵያ ስኬታማ ውጤት ታመጣበታለች የሚባለው የአትሌቲክሱ ውድድር ማጣሪያው ትናንት ተጀምሯል፡፡ ሜዳሊያዎች በማጥለቅ በደረጃ ሠንጠረዥ ውስጥ እንደምትገባም ይጠበቃል፡፡

ከመጀመሪያው ሳምንት ውጤት በኋላ ግብፅ በድምሩ በ84 ሜዳሊያዎች (47 ወርቅ፣ 19 ብር እና 18 ነሐስ) ቀዳሚ ሆናለች። ናይጄሪያ በ41 ሜዳሊያዎች (16 ወርቅ፣ 10 ብር እና 15 ነሐስ) ሁለተኛ፣ አልጄሪያ በ55 ሜዳሊያዎች (15 ወርቅ፣ 20 ብር እና 20 ነሐስ) ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...