Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበሕዝብ በዓላት አከባባር ወቅት በሕግ የተደነገገ ሰንደቅ ዓላማ እንዲውለበለብ ጥያቄ ቀረበ

በሕዝብ በዓላት አከባባር ወቅት በሕግ የተደነገገ ሰንደቅ ዓላማ እንዲውለበለብ ጥያቄ ቀረበ

ቀን:

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕዝብ በዓላትንና የበዓላት አከባባርን ለመወሰን በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ባደረገው ውይይት፣ በሕዝብ በዓላት ወቅት በሕግ የተደነገገ ባንዲራ እንዲውለበለብ ጥያቄ ቀረበ፡፡

ለዓመቱ አጋማሽ ዕረፍት ወጥቶ የተመለሰው ምክር ቤቱ በ16ኛ መደበኛ ስብሰባው በረቂቁ ላይ ውይይት ሲያደርግ፣ በረቂቁ ላይ ብቸኛውን አስተያየት የሰጡት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ከፈና ኢፋ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ የምክር አባሉ በሰጡት አስተያየት አብዛኞቹ በዓላት ሲከበሩ የሕዝብን ክብርና ሰብዕና የሚነኩ ልምዶች እንደሚስተዋሉ ጠቅሰው፣ በረቂቅ አዋጁ በዝርዝር እንዲታይ ጠይቀዋል፡፡

የአገሪቱ  በሕግ የተደነገገ ሰንደቅ ዓላማ በበዓላት ወቅት እንዲታይ የጠየቁት የምክር ቤት አባሉ፣ ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች አገር ናት ብለዋል፡፡ በአንዳንድ  የሕዝብና የሃይማኖት በዓላት ወቅት የሌሎችን ብሔሮች ክብርና  አጠቃላይ ሁኔታ የሚያጓድሉ ማየታቸውን፣ አንዳንዴም በጦር መሣሪያ የታገዙና ሥነ ልቦናን የሚነኩ ሁኔታዎች ስለመኖራቸው ገልጸው፣ በቀጣይ አዋጁ ውይይት ሲደረግበት ያቀረቡት ሐሳብ ታሳቢ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

ለዝርዝር ዕይታ የተመራውን ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ የሕዝብ በዓላት ለዜጎች ሥነ ምግባርና አገራዊ ሥነ ምግባር ግንባታ፣ ለአገርና ሕዝብ ያላቸው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ፣ ሕጋዊ ዕውቅና እንዲኖራቸውና በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበሩ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሕዝብ በዓላትና የዕረፍት ቀናት አዋጅ ቁጥር 16/1967 ሲሻሻል የሕዝብ በዓላትንና የዕረፍት ቀንን የወሰነና በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበር የደነገገ ቢሆንም፣ የሕዝብ በዓላት ሊያበረክቱት የሚችሉትን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ሊያስገኝ በሚቻል መንገድ በድምቀት የሚከበሩበትን ዝርዝር የአከባበር ሥርዓት ያላስቀመጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሥራ ላይ ያለው አዋጅ ለበዓላቱ አከባበር ከመንግሥት የሚጠበቀውን ሰላምና ደኅንነት የማስጠበቅና በቂ የሚዲያ ሽፋን የመስጠት ኃላፊነት የሚደነግግ በመሆኑ ሰፋ ያሉ ጉድለቶች የሚታዩበት እንደሆነ ተናግረው፣ ነባሩን አዋጅ ከማሻሻል ይልቅ ሙሉ ለሙሉ በአዲስ መተካት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ አዋጁ በሦስት ክፍሎችና በ19 አንቀጾች መደራጀቱን አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ብዙ በአደባባይ የሚከበሩ ሃይማኖታዊና ብሔራዊ በዓላት እንዳሏት የምክር ቤት አባላት አስታውስው፣ በዓላት በሚከበሩበት ወቅት በአብዛኛው የሕዝብን ሰብዕናና ክብር የሚነኩና አንዳንድ አላስፈላጊ ባህሪዎችም ስለሚታዩ ረቂቅ አዋጁ የሚመራለት ቋሚ ኮሚቴ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩና ሌሎችን ጉዳዮች ታሳቢ ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡

ፓርላማው የኢትዮጵያ ሜዳይ፣ ኒሻንና ሽልማት አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር ዕይታ በዋናነት ለውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና በተባባሪነት ለሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ መርቷል።

ምክር ቤቱ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንን የሠራተኞች አስተዳደር ደንብና የ16 ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞችን ሹመት መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...