Monday, May 27, 2024
Homeስፖንሰር የተደረጉየአየርላንድ ብሔራዊ ቀን - የቅዱስ ፓትሪክ ቀን - 2016 (እ.ኤ.አ. 2024)

የአየርላንድ ብሔራዊ ቀን – የቅዱስ ፓትሪክ ቀን – 2016 (እ.ኤ.አ. 2024)

Published on

- Advertisment -

የቅዱስ ፓትሪክ ቀን ላይ ሆነን መጪውን ጊዜ ስንቃኝ

በእያንዳንዱ የቅዱስ ፓትሪክ ቀን በአለም ዙሪያ ያሉ የአየርላንድ ኤምባሲዎች ብሄራዊ ቀናችንን በኩራት ለማክበር እና አየርላንድን ከተቀረው አለም ጋር የሚያስተሳስረውን ጠንካራ ግንኙነት በማሰላሰል በዓሉን ያከብራሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የአየርላንድ ኤምባሲም ከዚህ የተለየ አይደለም። በየዓመቱ ማርች 17፣ አየርላንድ እና ኢትዮጵያን የሚያገናኘውን ጠንካራ እና ታሪካዊ ግንኙነት በጥልቀት እናሰላስለዋለን። ይህ ግንኙነትም አነሰ ቢባል እ.ኤ.አ. በ1936 የወቅቱ የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ኤሞን ደ ቫሌራ የሙሶሎኒ ጣሊያን የኢትዮጵያ ወረራን በመቃወምና የአፄ ኃይለ ሥላሴን የድጋፍ ጥሪ በመንግስታቱ ድርጅት ሲደግፉ እስከነበረበት ጊዜ ይዘረጋል። የኢትዮጵያውያንን ህይወት ለማሻሻል የአየርላንድ ቄሶች፣ እህት መነኮሳት እና ሚስዮናውያን በ20ኛው መቶ አመት ያደረጉት የነበረውን ጥረት፣ እንዲሁም ቦብ ጊልዶፍና ሌሎችም በኢትዮጵያ ውስጥ በ1970ዎቹ ተከስቶ ለነበረው የረሃብ መቅሰፍት ለመታደግ ያከናወኗቸውን ተግባራት እናስታውሳለን። የአየርላንድ ኤምባሲ በአዲስ አበባ ከተከፈተ ከ1986 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. ከ1994) ወዲህ የአየርላንድ እና የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዘንድሮ 30 ዓመታትን ስናከብር ወቅቱ ለኤምባሲ ከቶም የማይረሳ ነው።

በአየርላንድ ውስጥ በብዙ የዓለም ማዕዘናት የሚታወቀውን ብሔራዊ ቀን በማግኘታችን ዕድለኛ እንደሆንን እንገነዘባለን። በአለም አቀፍ ደረጃ የአየርላንድ የዘር ግንድ አለን ከሚሉ ከ70 ሚሊዮን በላይ ሰዎች እና ሌሎችም ለአየርላንድ ያላቸውን ፍቅር በተለያዩ መንገዶች ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር አየርላንድን ለማክበር የቅዱስ ፓትሪክ ቀን ዕድሉን ሰጥቶናል።

የአየርላንድ የራሷ ታሪክ የረሃብ፣ የድህነት እና የግዳጅ ስደት ልምዶችን ያጠቃልላል። በ 1965 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. በ1973) ወደ አውሮፓ ህብረት ከገባን በኋላ ያገኘነው አንጻራዊ እድገት እና ብልጽግና ቢያንስ እስከ 1990ዎቹ ድረስ በሰሜን አየርላንድ ከበረው ግጭት ጋር አብሮ ተጉዟል። እነዚህ ልምምዶች፣ ግልጽ በሆነ ደረጃ፣ ዛሬ በዙሪያችን ያለውን ዓለም ላይ ያለንን እይታችንን ቀርፀውታል። በዚህ ታሪክ እና አየርላንድ ባጋጠሟት በእነዚህ ፈተናዎች ምክንያት በዓለም ዙሪያ የቅዱስ ፓትሪክን ቀን አከባበር የምንመለከተው በታላቅ ኩራት።

ዛሬ በዓለማችን ውስጥ እንደ ብሔራዊ ቀን ያለ ነገር “ማክበር” የሚለው ሃሳብ በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ ማመንታትን ቀስቅሶ ሊሆን ይችላል። ዛሬ በዓለም ዙሪያ፣ በዩክሬን፣ በጋዛ፣ በአፍሪካ ቀንድ ከባባድ ፈተናዎችን እያየን ነው። በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች በከፍተኛ መከራ ውስጥ ሆነው ይሰቃያሉ። ነገር ግን፣ በአየርላንድ ውስጥ ለብዙዎች የቅዱስ ፓትሪክ ቀን በዓል ብቻ ሳይሆን የአየርላንዳዊያን ውድ የሆኑ ጠንካራ መርሆችንን እና እሴቶቻችን የምናከብርበት ቀን ነው። ዕለቱ የአየርላንድ እና የአየርላንድ ህዝቦች ዕጣ ፈንታቸውን ለማሻሻል እና እነሱም ሆኑ አለማችን የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች ለመጋፈጥ ህይወታቸውን ያበረከቱትን አስተዋፅኦ የምናከብርበት ቀን ነው።

ከዚህ አኳያም እንደዚህ አይነት ታላላቅ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ በምንፈልግበት ወቅት ወደ ወጣቶች መመልከታችን ምንም አያስደንቅም። ወጣቶች ለአየር ንብረት ድንገተኛ አደጋ ዓይኖቻችንን በመክፈት እና በቅሪተ አካል ነዳጆች ላይ ያለንን ጥገኝነት የሚቀንሱ እና ንፁህ የኢነርጂ መጻኢ ጊዜን ለመቀዳጀት የሚያስችሉ አዳዲስ መፍትሄዎችን ለማስገኘት ቀዳሚዎቹ ናቸው። በአለም አቀፍ ደረጃ ወጣቶች ለአለም አቀፍ ህግ እና ለባለብዙ ወገን ተቋማት እና እንደ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ያሉ ቁልፍ ተዋናዮች ህግን መሰረት ያደረገ ስርአትን፣ ዘላቂ ልማትን እና ሰብአዊ መብቶችን በመደገፍ በአንድነት እንዲናገሩ እና እንዲሰሩ በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ። አየርላንድ ለአለም ባላት አቀራረብ እነዚህ ጉዳዮች ቁልፍና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ናቸው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አየርላንዳውያን ወጣቶች ኢትዮጵያውያንን ትምህርት እንዲያገኙ አስችለዋል፣ አሁንም በማስተማር ላይ ይገኛሉ። ሰብአዊ ተግባራትንና እጅግ ወደኋላ የቀሩ ዜጎችን ህይወት ለማሻሻል የሚያስችሉ ሌሎች ስራዎችንም በማከናወን ላይ ይገኛሉ። የእነዚህ ሁሉ ጥረቶች ጥምረትና ቅንጅት ደግሞ አየርላንድ ለሁሉም የተሻለ አለምን ለማስገኘት ያላትን ርዕይን ለማሳካት አስተዋፅዖ ያደርጋሉ።

አየርላንድን ለመዋዕለ ንዋይ፣ ለንግድ፣ ለመጎብኘት እና ለመማር ጥሩ ቦታ በሚያደርጓት ነገሮች ወሳኝ ቦታ ላይ ያሉት ወጣቶች ናቸው። ኩባንያዎች በአየርላንድ ውስጥ ሥር የሰደዱት በኢኮኖሚያችን የስኬት ሪከርድ፣ መረጋጋት፣ ለንግድ ሥራ ቀላልና ምቹ መሆን፣ እንዲሁም 450 ሚሊዮን ሕዝብ ያለውን የአውሮፓ ኅብረት ገበያን በማግኘታቸው ምክንያት ነው። ነገር ግን ኩባንያዎቹ በአየርላንድ ውስጥ ሊገኙ የቻሉባቸው ሌሎች ምክንያትች አሉ፤ እነሱም ላቅ ያለ ተሰጥዖና ችሎታ እንዲሁም ከአውሮፓ ህብረት አገራት የተውጣጡ ባለ ብሩህ አእምሮና ዓለምአቀፋዊ ትስስር ያላቸው ወጣቶች መገኛ በመሆኗም ነው።

አየርላንድ ስራ ፈጠራ ዋጋ የሚሰጥባትና ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ምርቶቻቸውንና ሃሳባቸውን ለዓለም አቀፍ ገበያ እንዲያቀርቡ ድጋፍ የሚደረግባት አገር ነች። አብዛኛዎቹ እነዚህ ሃሳቦች ያበቡትም ዓለም አቀፋዊ ዝናን ባገኘውና በደህንነቱ፣ በመልካም አቀባበሉ የበለጸገ ባህል ከባቢን ለአየርላንድና ከዓለም ዙሪያ ለተወጣጡ በሺህዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶች በማስገኘቱ መስህብ ሊሆን በቻለው የአየርላን የዩኒቨርሲቲ ወይም የከፍተኛ ትምህርት ስርዓት ውስጥ አማካኝነት ነው።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአየርላንድ ኤምባሲ በየዓመቱ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ወደ አየርላንድ በማስተርስ ፕሮግራም ደረጃ ጥናታቸውን እንዲያከናውኑና ከዚህ ከበለጸገው የትምህርት ስርዓትም ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረጉ ኩራት ይሰማዋል። በ 2017 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 2024) ተጨማሪ 12 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በአየርላንድ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በአየርላንድ በማስተርስ ዲግሪ ደረጃ ጥናታቸውን ያከናውናሉ፤ ይህ ቁጥርም በአንድ አመት ውስጥ ከፍተኛው ነው። እነዚህ ተማሪዎችም በአየርላንድ የተማሩ ከ200 በላይ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ፈለግ በመከተል ትምህርታቸውን ጨርሰው ሲመለሱም ለኢትዮጵያ ልማት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ለማበርከት እና በሁለቱ አገሮቻችን መካከል ጠንካራ የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለመፍጠር እንደቀደምቶቻቸው ይንቀሳቀሳሉ።

በመሆኑም፣ አየርላንድ፣ የአየርላንድ ህዝብ እና በአዲስ አበባ የሚገኘው የአየርላንድ ኤምባሲ ዕለቱ ያስገኘላቸውን ዕድል በመጠቀም በዚህ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. ማርች 17/2024) ለኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለቅዱስ ፓትሪክ በዓል አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን። ወደፊትም አብረን ስንጓዝ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን አየርላንድን እና ኢትዮጵያን ተጠቃሚ የሚያደርግ ጥልቅ አጋርነትን እናስቀጥላለን። በጋራ ሁላችንም ለእድገት፣ ለሰላም፣ ለሰው ልጅ ክብር እና ለሁሉም እኩልነት የጋራ ድምፅ መሆን እንችላለን።

አንድ የድሮ አይሪሽ አባባል አለ፡- – “ሁላችንም የምንኖረው አንዳችን በአንዳችን ጥላ ውስጥ ነው” – የሚል። ይህ አባባልም በመጪዎቹ ዓመታት በዓለም ላይ ላሉ ወጣቶቻችን አንዳች ተጨባጭ እውነት ሆኖ ይቀጥላል። አንዳችን አንዳችንን መጠበቅና መደገፍ ብሎም ዘላቂ አጋርነትን መገንባት ከዛሬ ጊዜ የበለጠ አስፈላጊ ሆኖ አያውቅም። በዚህ የቅዱስ ፓትሪክ ቀን የእኛም ትኩረት ይኸው ነው።

የቅርብ ጊዜ መጣጥፎች

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ ኃይለ ማርያም የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና የኢኮኖሚ ግስጋሴ ከማምጣት ወይ ከመንኮታኮት...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ ብቻ አይደለም፡፡ በየጊዜው እየባሰ የመጣው...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ከባድ...

ተመሳሳይ

ወንድማማቾቹን ለከፍተኛ ጉዳት የዳረገው ብሔር ተኮር ግጭት

ኢትዮጵያን በርካቶች የብዙኃን እናት፣ የብዙኃን አገር፣ ሲሉ ይጠሯታል፡፡ ለዚህም የተለያዩ ማንነቶች፣ ባህሎችና ሃይማኖቶች መኖሪያ...

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም በቶነር አሴምብሊንግ ስራ የተሰማራ ድርጅት...

ኦርቶፔዲክስ

በጡንቻ መገጣጠሚያ እና የአጥንት ህመሞች ላይ የላቀ ጥበብ፡- የአጥንት ጉዳትን ችግር ከመመርመርም ያለፈ የአጥንትና መገጣጠሚያ...