Friday, May 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበሁዋዌ ክፍለ አኅጉራዊ የአይሲቲ ውድድር ኢትዮጵያን የወከሉ ዘጠኝ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

በሁዋዌ ክፍለ አኅጉራዊ የአይሲቲ ውድድር ኢትዮጵያን የወከሉ ዘጠኝ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

ቀን:

በየዓመቱ የሚካሄደው የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለስምንተኛ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለስድስተኛ ጊዜ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ሁዋዌ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባካሄደው አገር አቀፍ የማጣሪያና ማጠቃለያ ውድድር ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያለፉ ሲሆን፣ ኢትዮጵያን ወክለውም በቱኒዝያ በሚካሄደው ስምንተኛው የሁዋዌ አይሲቲ (2023-2024) ክፍለ አኅጉራዊ ፍፃሜ ውድድር እየተሳተፉ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ፣ ከዘጠኝ አገሮች ከተውጣጡ 90 ተማሪዎች ጋር የሚወዳደሩም ይሆናል፡፡

- Advertisement -

የሁዋዌ ኢትዮጵያ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ፣ ማሊ፣ ካሜሩን፣ ሴኔጋል፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዝያ፣ ሊቢያ፣ ግብፅና ሞሮኮ ለፍፃሜ በቀረቡበት የዘንድሮ ውድድር፣ ከኢትዮጵያ ከ1,000 በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ተመዝግበው፣ 280 ተማሪዎች ካሉበት ሆነው የአገር አቀፍ ውድድር ማጣሪያ ፈተናውን በበይነ መረብ ተሳትፈዋል።

ከእነሱም መካከል 80ዎቹ በአገር አቀፍ የፍፃሜ ውድድሩ ተሳትፈው፣ ዘጠኙ ለክፍለ አኅጉሩ የሁዋዌ አይሲቲ የማጠናቀቂያ ውድድር አልፈዋል፡፡ የመጨረሻ ውድድሩ በቱኒዝያ የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. የተጀመረ ሲሆን፣ ዛሬ መጋቢት 1 ቀን ይጠናቀቃል።

ሁዋዌ አይሲቲ ውድድር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የተነደፈ የአይሲቲ ክህሎት ማሳደጊያና ማበልፀጊያ መድረክ ነው። የሁዋዌ አይሲቲ ወድድር ጥራት ያለው የአይሲቲ ተሰጥዖ ዕድገትን ለማፋጠን፣ ለኢንዱስትሪው ብቁ ተሰጥዖዎችን ለማዘጋጀትና ለመምረጥ፣ የመስኩ ባለተሰጥዖዎችን ወደፊት ለማቅረብና ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ንቁ ተሳታፊዎችን ለማበርከት፣ የመስኩ ፍላጎትና አቅርቦት በቂ እንዲሆን ለማበረታታትና በዘላቂነት አስተዋፅኦ ለማድረግ የሚሠራ ነው።

በቱኒዝያ በውድድር የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ከጅማ፣ ከሐሮማያና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች የተገኙ ሲሆን፣ ተማሪዎቹን ለማበረታታትም ሦስት መምህራን አብረው እንዲጓዙ ተደርጓል።

ከዚህ ቀደም በቻይና ሼንዘን ከተማ ከግንቦት 16 እስከ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በተካሄደው ሰባተኛው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ ውድድር፣ ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የሦስተኛ ደረጃ በመውጣት መሸለማቸው ይታወሳል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...