Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየወጣቶች አሁናዊ ሁኔታዎችና የተሰነዘሩ መፍትሔዎች

የወጣቶች አሁናዊ ሁኔታዎችና የተሰነዘሩ መፍትሔዎች

ቀን:

የኢትዮጵያ ወጣቶች በዘርፈ ብዙ ማኅበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚያልፉ ናቸው፡፡ የእነዚህን ወጣቶች ችግር በመቅረፍ፣ በአገር ልማትና ዕድገት ውስጥ ሚና እንዲኖራቸው በመንግሥትና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በርካታ ጥረቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

መፍትሔ በማፈላለግ ረገድ ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ፓስጋር ከተባለ ለአፍሪካ ማኅበራዊ አስተዳደር ምርምር አጋርነት (Partnership for African Social and Governance Research) ከሚባል ድርጅት ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ወጣቶች ያሉባቸውን አሁናዊ ሁኔታዎች በተመለከተ ጥናት አካሂዷል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ መምህር የሆኑት አዳምነሽ አጥናፉ (ረዳት ፕሮፌሰር) እንደገለጹት፣ ወጣቶች ምን ይፈልጋሉ? እንዴት እየኖሩ ነው? የሚገጥሟቸውን እክልና ተግዳሮት በምን ዓይነት መልኩ እየተወጡ ነው? በሚለው ዙሪያ ለሦስት ዓመት ያህል ጥናት ተካሂዷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሶማሌ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ኦሮሚያና ደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኙ ወጣቶች ዙሪያ ተነሳሽነትንና ፅናት የተመለከተ (Ethiopian Women and Men Inspiration and Resliance) በሚል ርዕስ ጥናት መካሄዱንና የጥናቱ ዓላማም የወጣቱ ፍላጎት ምን ይመስላል? ወጣቱ ወዴት እየሄደ ነው? ምን እክል ይገጥመዋል? ችግሮቹንስ እንዴት እየፈታ ነው? የሚለውን ውጤት ለመንግሥትና በወጣቶች ዙሪያ ለሚሠሩ ተቋማት ለማመላከት ነው፡፡

እንደ ረዳት ፕሮፌሰሯ ገለጻ፣ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ወጣቶች ጥያቄ ዙሪያ የተሠራው ጥናት ዓላማው፣ መደርደሪያ ላይ እንዲቀመጥ ሳይሆን መሬት ላይ ወርዶ መተግበር ስለሚችልበት ሁኔታ ለመወያየትና በዚህም መነሻነት አዳዲስ ደንቦች፣ መመሪያዎችና ፖሊሲዎች የሚቀረፁበትን መንገድ ለማመላከት ጭምር ነው፡፡

የጥናት ቡድኑ ባካሄደው ጥናት የተገኘው ውጤት እንደሚያመለክተው ወጣቱ ተስፈኛ ወጣት እንደሆነ፣ መቻሉን የሚያውቅ፣ መንገድን ካገኘ ወይም የሚፈልገው ነገር ከተመቻቸለት ‹‹አደርገዋለሁ›› ብሎ የሚያምን ነው የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሯ፣ ጥናቱ እስካሁን በወጣቶች ዙሪያ የነበረውን ትርክት የቀየረ ነው፡፡

ወጣቱ ደካማ፣ አቋራጭ ፈላጊ፣ ተስፋ የቆረጠ፣ በሱስ (በጫት፣ በሲጋራ፣ በአልኮልና በአደንዛዥ ዕፆች) የተጎዳ ነው ተብሎ በጥቅሉ ሲፈረጅ የቆየ ነው፡፡ እንደተባለውም ወጣቱ ያለበት ሁኔታ ‹‹የተባለው›› ሆኖም ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የሆነበት ምክንያት ወጣቱ ሞራል ስለሌለው፣ ሰነፍ ስለሆነ፣ ራሱን ለመለወጥ ፍላጎትና ተስፋ ስለሌለው ሳይሆን ሁኔታዎች ስላልተመቻቹለት ነው፡፡

በተጨማሪም ወጣቱ ያለው ክህሎትና በኢትዮጵያ ያለው የሥራ መስክ ያልተቀራረበ መሆን፣ የተማረና የሠለጠነውም ወጣት ሥራ አጥ ሆኖ የመቀመጡ ነገር ሌላው መታየት የሚገባው ጉዳይ መሆኑን የሚናገሩት ምሁሯ፣ ይህንን ክፍተት ለማጥበብና ወጣቱን ከሥራ ጋር ለማገናኘት መንግሥትና በወጣቶች ዙሪያ የሚሠሩ ተቋማት አጽንኦት ሊሰጡት ይገባል ብለዋል፡፡

አሁን ባገኘነውና በሠራነው ጥናት መሠረት ወጣቱ ተስፋ ያለውና መለወጥ የሚችል ነው፡፡ ሥራ መሥራትን የሚሻ እንጂ ሥራ ፈትቶ መቀመጥ የሚወድ አይደለም፡፡ በመሆኑም የወጣቱ ወደ ሥራ መሠማራት ለኢትዮጵያ ልማትና ዕድገት ከፍ ያለ አበርክቶ ያለው በመሆኑ ሊታሰብበት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

የጥናቱ ዓላማ፣ የጥናቱን ግኝት ለሚመለከታቸው አካላት በማቅረብ፣ ችግሮቹ በምን መልኩ መፈታት አለባቸው? የወጣቶችን ጥያቄዎች በመመለስ ረገድ እስከ ምን ድረስ መጓዝ ይጠበቅብናል?›› የሚለውን የወደፊት አቅጣጫ የሚወስን በመሆኑ፣ ከወጣቶችና ከወጣቶች ጋር ከሚሠሩ የተለያዩ ተቋማት የሚገኘውን ግብረ መልስ በማዳበር ተግዳሮቻቸውን በመቅረፍ ረገድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ሚና መወጣት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

በጥናት መድረኩ ላይ ወጣቶች፣ የወጣት ማኅበራት ተወካዮች፣ በወጣቶች ዙሪያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...