Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትለአዲስ የዓለም ክብረ ወሰን የሚጠበቀው የለንደን ማራቶንና የሚጠበቁት ኢትዮጵያውያን

ለአዲስ የዓለም ክብረ ወሰን የሚጠበቀው የለንደን ማራቶንና የሚጠበቁት ኢትዮጵያውያን

ቀን:

የዓለም አትሌቲክስ የፕላቲንየም ደረጃ የሰጠው የጎዳና ውድድሩ የለንደን ማራቶን የሚካሄደው በዕለተ እሑድ ሚያዝያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ሲሆን፣ ከወዲሁ የአትሌቲክስ ቤተሰቡን ትኩረት ስቧል፡፡

የዓለም አትሌቲክስ እንደዘገበው፣ በሴቶች በታሪክ ከመጀመሪያዎቹ አራት ፈጣን ሯጮች ትዕግስት አሰፋ፣ ኮስጌን፣ ቼፕንገቲች እና ጄፕቺርቺርን መካከል  በተለይ ሦስቱ የዓለም ክብረ ወሰንን ለመስበር እንደሚፎካከሩ ተጠብቋል፡፡

ፉክክሩን በበላይነት የምትመራው ኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት አሰፋ በዓመቱ መባቻ በበርሊን 2፡11፡53 በሆነ ሰዓት በመፈጸም፣ የኬንያዊቷን ብሪጂድ ኮስጌይ ሰዓት ከሁለት ደቂቃ በላይ በማሻሻል የዓለም ክብረ ወሰንን መስበሯ ይታወሳል፡፡

- Advertisement -

ለአዲስ የዓለም ክብረ ወሰን የሚጠበቀው የለንደን ማራቶንና የሚጠበቁት ኢትዮጵያውያን | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ከሁለቱ አትሌቶች ባሻገር ብርቱ ተፎካካሪ በመሆን ክብረ ወሰኑ ላይ ካነጣጠሩት መካከል የኦሊምፒክ ሻምፒዮኗ ፔሬስ ጄፕቺርቺር፣ የ2019 የዓለም ሻምፒዮኗ ሩት ቼፕንገቲች፣ የምንጊዜም አራተኛዋ ፈጣን ሴት፣ የ2022 የለንደን ማራቶን ሻምፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ያለምዘርፍ የኋላውና የ2021 የለንደን ማራቶን አሸናፊዋ ጆሲሊን ጄፕኮስጌይ ይገኙበታል።

በለንደን ማራቶን ከሚወዳደሩት ውስጥ በሚያስደንቅ ሁኔታ አሥር ሴቶች ከ2፡17፡30 በታች በመፈጸም ምርጥ ሰዓት አስመዝግበዋል። የበርካታ የዓለምና የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዋ አልማዝ አያና፣ በቅርቡ የዱባይ ማራቶን አሸናፊዋ ትዕግስት ከተማ፣ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት መገርቱ ዓለሙና ኬንያዊቷ ሺላ ቼፕኪሩይ በዝርዝሩ ውስጥ አሉበት።

ከዋክብቱን አትሌቶች ለክብረ ወሰን ለማብቃት ወንድ አሯሯጮች መዘጋጀታቸው ታውቋል፡፡

‹‹በሴቶች የማራቶን ሩጫ በወርቃማ ዘመን ውስጥ ነን፤›› ሲሉ የተናገሩት የለንደን ማራቶን የዝግጅት ዳይሬክተር ሂዩ ብራሸር ናቸው። ፓውላ ራድክሊፍ በ2003 በለንደን ማራቶን ያስመዘገበችው አስደናቂው የዓለም ክብረ ወሰን 2፡15፡25፣ በብሪጊድ ኮስጌን ለመሰበር የቻለው በ16ኛው ዓመት መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ ከወራት በፊት በበርሊን ባሳየችው አስደናቂ ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰንን በላቀ ደረጃ ያሳደገችው ትዕግስት አሰፋን ጨምሮ ሌሎች አራት ሴቶች ከፓውላ ጊዜ በበለጠ ፍጥነት መሮጥ ችለዋል። ይህም ሆኖ በ2017 በለንደን ማራቶን ሜሪ ኪታኒ ያስመዘገበችው 2፡17፡01 ተጠቃሽ ነው።

ሌላው ተጠባቂ ውድድር የወንዶች የማራቶን ፉክክር ነው፡፡ በከፍተኛ ደረጃ ግምት ያገኙት የኒውዮርክ ማራቶን ሻምፒዮኑ ኢትዮጵያዊ ታምራት ቶላ፣ የሁለት ጊዜ የኒውዮርክ ከተማ ማራቶን አሸናፊው ጂኦፍሪ ካምዎሮር እና የበርካታ የዓለምና የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ቀነኒሳ በቀለ ናቸው።

በ2023 የቫሌንሺያ ማራቶን 2፡03፡11 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የሁለት ጊዜ የዓለም የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሞሰነት ገረመውና አሌክሳንደር ሙቲሶ ሙኒዮ በውድድሩ ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያዊው ዳዊት ወልዴ የ2019 የቫሌንሢያ አሸናፊ ክንዴ አጥናውና የዓለም የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ልዑል ገብረ ሥላሴ ሌሎቹ ተወዳዳሪዎች ናቸው።

ዘገባው አክሎ እንደገለጸው፣ ለእንግሊዝ የሚሮጡት ኤሚል ካይረስ እና ካልም ሃውኪንስ ጥሩ ሰዓት አላቸው። የ2022 የዓለም የቤት ውስጥ የ3000ሜ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊው ማርክ ስኮት የማራቶን የመጀመሪያ ሩጫውን ያደርጋል። ከመጀመርያዎቹ ምርጦቹ 11ዱ መካከል ስድስቱ ኢትዮጵያውያት ሲሆኑ አምስቱ ኬንያውያት ናቸው፡፡ በወንዶች ምድብ ከመጀመርያዎቹ ምርጥ ሰዓት ካላቸው 10ሩ መካከል ሰባቱ ከኢትዮጵያ፣ ሁለቱ ከኬንያ አንዱ ከብራዚል ናቸው፡፡

ምርጦቹ ሯጮችና ሰዓታቸው በከፊል

በሴቶች

ትዕግስት አሰፋ (ኢት) 2:11:53

ብሪጂድ ኮስጌይ (ኬን) 2:14:04

ሩት ቼፕንገቲች (ኬን) 2:14:18

ትዕግስት ከተማ (ኢት) 2:16:07
አልማዝ አያና (ኢት) 2:16:22
መገርቱ ዓለሙ (ኢት) 2:17:09
ፔሬስ ጄፕቺርቺር (ኬን) 2:17:16
ጆሲሊን ጄፕኮስጌይ (ኬን) 2:17:23
ያለም ዘርፍ የኋላው (ኢት) 2:17:23
ሺላ ቼፕኪሩይ (ኬን) 2:17:29
ጽጌ ኃይለሥላሴ (ኢት) 2:22:10
       ወንዶች
ቀነኒሳ በቀለ (ኢት) 2:01:41
ሞሰነት ገረመው (ኢት) 2:02:55
ሙቲሶ ሙንያኦ (ኬን) 2:03:11
ታምራት ቶላ (ኢት) 2:03:39
ዳዊት ወልዴ (ኢት) 2:03:48
ክንዴ አጥናው (ኢት) 2:03:51
ልዑል ገብረሥላሴ (ኢት) 2:04:02
ጂኦፍሬይ ካምዎሮር (ኬን) 2:04:23
ሰይፉ ቱራ (ኢት) 2:04:29
ዳንኤል ዶ ናሲ

ሜንቶ (ብራዚል) 2:04:51

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...