Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊልሂቅ የሕግ አማካሪና ጠበቃ አቶ ሞላ ዘገየ (1945-2016)

ልሂቅ የሕግ አማካሪና ጠበቃ አቶ ሞላ ዘገየ (1945-2016)

ቀን:

ከቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት (1923-1967) ጀምሮ በወታደራዊ መኰንንነት፣ በፖለቲካ አመራርነት እንዲሁም ከሦስት አሠርታት በላይ በሕግ አማካሪነትና በጥብቅና ሙያ አገራቸውን በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ ያገለገሉት የሕግ አማካሪና ጠበቃው አቶ ሞላ ዘገዬ ናቸው፡፡

 

ገጸ ታሪካቸው እንደሚያመለክተው፣ በ1961 ዓ.ም. የክብር ዘበኛ ሠራዊት አባል በመሆን በማይጨው ጦር ሰፈር በመሐንዲስ መምሪያ አገልግለዋል፡፡ ቅድመ አብዮት ለሥርዓተ መንግሥት ለውጥ በተነሳው ሕዝባዊ አመፅ በመሪነትና በአስተባባሪነት በመታገላቸው ከየካቲት እስከ ሰኔ 1966 ዓ.ም. ድረስ በንጉሠ ነገሥቱ የፀጥታ ኃይሎች ለአምስት ወራት ታስረዋል፡፡ ደርግ ከተቋቋመ በኋላ ከተፈቱት ቀደምት የሠራዊት ታጋዮች አንዱ ነበሩ፡፡

- Advertisement -

አቶ ሞላ በተለይ በገበሬው ይፈጸም የነበረውን ግፍ አጥብቀው የሚጠሉ በመሆኑና ከተፈቱም በኋላ ለትግላቸው አመቺ ሁኔታ በመፈጠሩ በወታደራዊ ደርግ የመጀመርያ ዓመታት በበርካታ ኃላፊነት ላይ ተመድበው አገልግለዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የለውጥ ሐዋርያ፣ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴርና የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የመንግሥት ተጠሪ፣ የአስበ ተፈሪና የጅግጅጋ አውራጃዎች ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ሠርተዋል፡፡

በተለይ የአሰበ ተፈሪ አስተዳዳሪ በነበሩበት ጊዜ ‹‹ፀረ አብዮተኛ‹‹ ተብለው ታስረው የነበሩ ሕፃናትና ወጣቶችን በመታደግ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ማድረጋቸው፣ አውራጃውም በግብርና፣ በደን ልማትና በመሠረተ ትምህርት ማስፋፋት ከሐረርጌ አውራጃዎች በአንደኝነት እንዲጠራ ማድረጋቸው ይወሳል፡፡

የጅግጅጋ አውራጃ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተመደቡት በኢትዮ ሶማሊያ ጦርነት ወቅት ከፍተኛ ውድመት ከደረሰበት በኋላ ነበር፡፡ በአመራርነት በተመደቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሕዝቡን በማስተባበር የጅግጅጋ ከተማና ወረዳዎች በተሻለ እንዲታደሱ፣ ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ፣ ጤና ጣቢያዎች ሥራ እንዲጀምሩ ማድረጋቸው የሚያብራራው ገጸ ታሪካቸው፣ ከዚህም ሌላ በታሪክ የሚታወሱበትን የጅግጅጋን ከተማ ማስተር ፕላን ለመጀመርያ ጊዜ በማሠራት እንዲሁም የጎልማሳዎች ማሠልጠኛ ጣቢያዎች፣ ሙዓለ ሕፃናትና የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላትን አስገንብተዋል፡፡ በእነዚህ ሁሉ ተግባራት በአውራጃው ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ አክብሮትና ተወዳጅነትን አትርፈዋል ይላል፡፡

በሲዳሞ ክፍለ ሀገር የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን (ኢሠፓአኮ) የቁጥጥር መምሪያ ኃላፊ የነበሩት አቶ ሞላ፣ የመጨረሻው መንግሥታዊ መሥሪያ ቤታቸው የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ነበር፡፡

በተማሩት የሕግ ትምህርት በጥብቅና አገልግሎትና በንግድ ሥራ ተሰማርተው ሳለ የ1983 ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ በ1986 ዓ.ም. መጀመሪያ ወራት ላይ ደንበኛቸው የተመሠረተበትን ክስ ለመከታተል ወደ ሕግ ተቋም በሄዱበት ወቅት በሕግ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ተደርገው ያለ አንዳች መረጃና ማስረጃ እስከ ታኅሣሥ 1995 ዓ.ም. ድረስ ለዘጠኝ ዓመታት ገደማ በግፍ መታሰራቸውና ለራሳቸው ተከራክረውና ክሱንም ረተው በነፃ መሰናበታቸው ታሪካቸው ያሳያል፡፡

ከእስርም ከወጡ በኋላ ቀደም ሲል አብረዋቸው ይሠሩ ለነበሩና በእስር ላይ ለሚገኙ ጓዶቻቸው በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር እንዲሰማ በማድረግ፣ በመጨረሻም ከእስር እንዲወጡ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከታቸው ተጠቅሷል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመጥነውን ፖለቲካና ፖለቲካ አላገኘም›› ይሉ የነበሩት አቶ ሞላ፣ በይበልጥ በሕግ ባለሙያነታቸውና በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ሐሳባቸውን በማካፈልና በመሞገት ይታወቃሉ፡፡

‹‹ውይይት›› በመባል በሚታወቀውና እሳቸው በሚያሳትሙት መጽሔት በርካታ መጣጥፎችን በአገራዊ ወቅታዊና መሰል ጉዳዮች ሲጽፉም ይታወቃሉ፡፡ ከሕግ ባለሙያነታቸው በተጨማሪ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ከመስጠት ባለፈ፣ ኢትዮጵያ ስለሚያስፈልጋት ለውጥና እንዴት መመራት እንዳለባት የሚያመላክት ‹‹ሪፎርም›› የተሰኘ መጽሐፍም ጽፈዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜያትም ወዲህ በአገር ደረጃ ያለውን የፖለቲካ ልዩነት አለመግባባትና ችግር በሰላማዊ መንገድ፣ በውይይትና በንግግር እንዲፈቱ ለማድረግ የተለያዩ ጽሑፎችን በመገናኛ ብዙኃን በማውጣት ለአገር ሰላም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የቦርድ አባልም ነበሩ፡፡

ከአባታቸው ከአቶ ዘገዬ አቡዩና ከእናታቸው ከወ/ሮ አጥቢት አየለ በቀድሞው ወሎ ጠቅላይ ግዛት በራያና ቆቦ አውራጃ በቆቦ ከተማ ግንቦት 1 ቀን 1945 ዓ.ም. የተወለዱት አቶ ሞላ ዘገዬ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1979 ዓ.ም. በሕግ ዲፕሎማ አግኝተዋል፡፡

አቶ ሞላ ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ በደረሰባቸው ድንገተኛ ሕመም በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በተወለዱ በ71 ዓመታቸው አርፈዋል፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም የካቲት 29 ቀን በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡

ነፍስ ኄር አቶ ሞላ ዘገየ በ1981 ዓ.ም. ከወ/ሮ ብሩክታዊት ደረሰ (ጂጂ) ጋር ትዳር መሥርተው አንድ ወንድና መንታ ሴት ልጆችን አፍርተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...