Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናአይኤምኤፍ በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ያሳስበኛል አለ

አይኤምኤፍ በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ያሳስበኛል አለ

ቀን:

የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች፣ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና በታጣቂ ኃይሎች መካከል ያለው የተራዘመና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሄደው ግጭት እንደሚያሳስበው አስታወቀ፡፡

የገንዘብ ተቋሙ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ጁሊ ኮዛክ ሐሙስ የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው መግለጫ፣ ግጭቱ ኢትዮጵያ ከሰሜኑ የሁለት ዓመት ጦርነት በኋላ ለምታከናውነው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር አስታውቀዋል፡፡

‹‹በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የተከሰቱት ግጭቶች በእርግጥም አሳሳቢና የሚረብሹ ናቸው። እነዚህን ሁነቶች በቅርበት እየተከታተልን ነው፡፡ በአሜሪካ በኩል ስለግጭቱ የሚቀርበውን ሥጋት የገንዘብ ተቋሙ እንደሚከታተልና ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ተስፋ እናደርጋለን፤›› ብለዋል፡፡

- Advertisement -

ከሳምንታት በፊት በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው የነበሩት የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር፣ በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሰውና በፓርላማው አሸባሪ ተብሎ ከተሰየመው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነግ ሸኔ) ጋርም ሆነ፣ በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሰው የፋኖ ኃይል ጋር የሚያካሂዳቸውን ግጭቶች ለማስቆምና ለማደራደር አሜሪካ ዝግጁ መሆኗን ገልጸው፣ ወታደራዊ አማራጭ ሰላማዊ መፍትሔ እንደማያመጣ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እየታየ ነው ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመጥቀስ፣ መንግሥት ለዜጎች ከለላ እንዲያደርግና ወንጀለኞችን ተጠያቂ እንዲያደርግ አሳስበው ነበር፡፡

ኢትዮጵያ እያጋጠሟት ነው ያሏቸውን ዓበይት ተግዳሮቶች በተለይም የምግብ ዋስትና ችግር፣ ሰብዓዊ ፍላጎቶች፣ ድኅረ ግጭት መልሶ ግንባታ፣ ከፍተኛ የዋጋ ንረት፣ እንዲሁም የአገር ውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳዎችን ለመደገፍ፣ የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄ ቀርቦልናል ሲሉ የአይኤምኤፍ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡

በጥቅምት 2016 ዓ.ም. በነበሩት ንግግሮች የመንግሥትን የኢኮኖሚ መርሐ ግብርና የተጠየቀውን ፕሮግራም የሚያጠናክሩ ማሻሻያዎችን እንዴት እንደሚደግፍ ጥሩ ለውጦች መታየታቸውን፣ አሁንም ውይይቶች በመካሄድ ላይ እንደሆኑ፣ በሚቀጥሉት ሳምንታት ሌላ የገንዘብ ተቋሙ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጣ ኃላፊዋ አረጋግጠዋል፡፡

ኢትዮጵያ የብድር ዕፎይታ ለማግኘት በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ በኩል የዕዳ ሽግሽግ ለማድረግ ውይይት ማካሄድ ከጀመረች የሰነባበተች ሲሆን፣ ከወራት በፊት በፈረንሣይና በቻይና በሚመራው የፓሪስ ክለብ አማካይነት የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ላይ መድረሷ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...