Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊኢትዮጵያ 240 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የደን ካርበን አከማችታ ለመሸጥ ቃል ገባች

ኢትዮጵያ 240 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የደን ካርበን አከማችታ ለመሸጥ ቃል ገባች

ቀን:

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. 2030 ድረስ 240 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የደን ካርበን አከማችታ ለዓለም አገሮች ለመሸጥ ቃል መግባቷን፣ የኢትዮጵያ ደን ልማት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ደን ልማት የተፈጥሮ ደንና ንብረት ምርምር ዳይሬክተር አበጀ እሸቴ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አዲሱ የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ደንብ፣ የኢትዮጵያ የካርበን ሽያጭ በሕግ እንዲመራ የሚያደርግና የግል ዘርፉ ተሳትፎ የሚያሳድግ ነው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ27ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተወያይቶ እንዲፀድቅ ውሳኔ ካሳለፈባቸው የሕግ ማዕቀፎች መካከል አንዱ ‹‹የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ረቂቅ ደንብ›› መሆኑ ይታወሳል፡፡

- Advertisement -

በደን ካርበን ሽያጭ በባለቤትነት የሚመሩ ተዋናዮች ሊኖራቸው የሚችሉ መብቶችና ግዴታዎች በደንቡ ላይ መቀመጡን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ አብዛኛውን ጊዜ የኢትዮጵያ ደን ልማት ላይ የግል ዘርፍ ተሳትፎ አነስተኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የደን ካርበን ላይ ባለቤቱ ማን እንደሆነና የመሸጥ የመለወጥ መብት እንዴት እንደሆነ በግልጽ በደንቡ ላይ መቀመጡን ገልጸው፣ በአሁኑ ወቅት አንድ ሜትሪክ ቶን ካርበን በዘጠኝ ዶላር እየተሸጠ ነው ብለዋል፡፡

በሚኒስትሮች ምክር ቤት በፀደቀው ደንብ ላይ አራት ዓይነት የደን ባለቤቶች እንዳሉ የሚያሳይ ሲሆን፣ አንደኛው ባለቤትነቱ የመንግሥት የሆነ የማኅበረሰብ ደን፣ የማኅበራትና የግል ደን ባለቤቶች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡  

ደንቡም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት፣ የካርበን ክምችትን በዓለም አቀፍ ግብይት በማስገባት የኢትዮጵን የደን ሀብት ለማልማትና ለማስጠበቅ የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ደን አልሚዎች የካርበን ሽያጭን በፈለጉት ገንዘብ መሸጥ መለወጥ እንደሚችሉ ገልጸው፣ ሽያጩ በሚከናወንበት ወቅት መንግሥት ወይም ሌላ አካል እንደ ሦስተኛ ወገን ሆኖ በሽያጩ የሚሳተፉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ በፊት በወላይታ አካባቢ የማኅበረሰብ ደን አልሚዎች የካርበን ሽያጭ መፈጸማቸውን፣ ይህንንም ሽያጭ ተግባራዊ ሲሆን፣ ‹‹ወርልድ ቪዥን›› እንደ ሦስተኛ ወገን ሆኖ እንዳሻሻጣቸው አክለው ገልጸዋል፡፡

የትኛውም የካርበን ሽያጭ የሚያከናውን አካል ከግዥ ጋር ስምምነት በመፈጸም መሸጥ እንደሚችልና 80 በመቶ ያህሉን ክፍያም ሻጮች የሚወስዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የካርበን ሽያጭ በዘፈቀደ እንዳይሆን መመርያ ለማውጣት ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸው፣ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2010 የሙቀት አማቂ ጋዞችን የምትለቀው 247 ሜትሪክ ቶን እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ይህም ሌሎች አገሮች ከሚለቁት አንፃር ከግማሽ በመቶ በታች እንደሆነ፣ አሁን ባለው ሁኔታው እ.ኤ.አ. ከ2010 እስከ 2030 ድረስ ኢትዮጵያ የምትለቀው 403 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የዓለም አቀፍ ስምምነትን ላይ  ኢትዮጵያ የራሷን ድርሻ መውሰዷን ድርሻዋንም እ.ኤአ. እስከ 2030 የሚቆይ መሆኑን ገልጸው፣ በዚህም ስምምነት መሰረት ኢትየጵያ በራሷ አቅም ተጠቅማ የምትቀንስ መሆኑን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በሌሎ አገሮች ድጋፍ ተደርጎላት ተግባራዊ የምታደርግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡  

ከዚህ በፊት በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የደን አልሚዎች የካርበን ሽያጭ በማከናወን 40 ሚሊዮን ዶላር ማግኘታቸውን፣ በኢንዱስትሪም ሆነ በነዳጅ የሙቀት አማቂ ጋዝ ለሚለቁ አገሮች ይህንን በተመለከተ በየዓመቱ ስብሰባ የሚካሄድ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

እ.ኤ.አ. 2030 ድረስ ኢትዮጵያ የደን ሽፋኗን 30 በመቶ ለማድረስ ዕቅድ መያዟን ገልጸው፣ የተራቆቱ መሬቶቿንም መልሰው እንዲያበቅሉ ማድረግና አዳዲስ ደኖችን መፍጠር ላይ ትኩረት ሰጥታ የምትሠራ ይሆናል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በየዓመቱ 3.5 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል በዕቅድ ደረጃ መቀመጡን፣ አንድ ዛፍም እንደተተከለ ለካርበን ሽያጭ እንደሚያገለግልና ቢያንስ አሥር ሳንቲም ውፍረት ሊኖረው እንደሚገባ ጠቅሰው፣ ይህንንም ለማድረግ ቢያንስ አሥር ዓመት ሊፈጅ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...