Tuesday, May 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበኢትዮጵያ በየዓመቱ አምስት ሺሕ ሴቶች በማሕፀን በር ካንሰር ሕይወታቸውን ያጣሉ

በኢትዮጵያ በየዓመቱ አምስት ሺሕ ሴቶች በማሕፀን በር ካንሰር ሕይወታቸውን ያጣሉ

ቀን:

  • የማሕፀን በር ካንሰር ክትባት በትምህርት ቤቶች ተጀምሯል

በኢትዮጵያ በየዓመቱ አምስት ሺሕ ሴቶች በማሕፀን በር ካንሰር ህይወታቸውን እንደሚያጡ፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዮሐንስ ጫላ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡  

ዕድሜያቸው 14 ለሆኑ ሴት ተማሪዎች የማሕፀን በር ካንሰር ክትባት መርሐ ግብር በቦሌ ክፍለ ከተማ ምሥራቅ በር ቁጥር ሁለት ትምህርት ቤት ሲጀመር የተገኙት ዮሐንስ (ዶ/ር)፣ የጤና፣ የማኅበራዊና የኢኮኖሚያዊ ችግር አንድ ምክንያት የሆነውን የማሕፀን በር ካንሰር በሽታ ለመከላከል እንዲቻል፣ በርካታ ተግባራት እንደሚከናወኑ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ በየዓመቱ አምስት ሺሕ ሴቶች በማሕፀን በር ካንሰር ሕይወታቸውን ያጣሉ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ዮሐንስ ጫላ (ዶ/ር)

በሴቶች ብሎም በማኅበረሰቡ ላይ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እያደረሰ የሚገኘው የማሕፀን በር ካንሰር፣ በዋናነት የሚከሰተው በግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚተላለፍ ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ምክንያት መሆኑን የገለጹት ዮሐንስ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ ለኅብረተሰቡ ከፍተኛ ሥጋት መሆኑንና በገዳይነቱም በሁለተኛ ደረጃ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

የማሕፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት በአዲስ አበባ ከየካቲት 25 እስከ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሆኑ ታዳጊ ሴቶች መሰጠት መጀመሩን የተናገሩት ዮሐንስ (ዶ/ር)፣ በክትባት ዘመቻው 31,485 ሴት ታዳጊ ልጆች ለመከተብ መታቀዱንና በትምህርት ቤትና ከትምህርት ቤት ውጭ ለሚገኙ ሴት ታዳጊ ልጆች ተደራሽ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡

‹‹በሽታውን በክትባት ብቻ መከላከል ሲቻል በቀን በአማካይ ሁለት ሺሕ እህቶችን፣ እናቶችንና ልጆቻችንን እናጣለን፡፡ ይህ በሽታው ምን ያህል አስጊ እንደሆነ ማሳያ ነው፤›› ብለዋል፡፡

 ከሽታው መከላከያ ዋነኛ መንገዶች አንዱ ዕድሜያቸው 14 ዓመት የሞላቸውን ሴት ልጆች መከተብ ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ ዕድሜያቸው ከ30 በላይ ለሚሆኑ ሴቶች በዓመት አንድ ጊዜ የማሕፀን በር ካንሰር ቅድሚያ ምርመራ እንዲያደርጉ ማስቻል ነው፡፡ ሦስተኛው በበሽታው ተይዘው የተገኙትን ማከም በመሆኑ ሁሉም ሴቶች በሚቀጥሉት አምስት ቀናት ውስጥ ወደ ሚቀርባቸው ክትባት መስጫ በመቅረብ የወደፊት ሥጋት የሆነውን በሽታ ዛሬ በቀላሉ ማስወገድ እንዲችሉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ለአምስተኛ ጊዜ በሚካሄደው የማሕፀን በር ካንሰር የመከላከያ ክትባት፣ ከ150 ሺሕ በላይ ሴቶችን መከተብ የተቻለ ሲሆን፣ ዘንድሮም በልዩ ሁኔታ ዕድሜያቸው 14 ዓመት የሞላቸው ታዳጊ ሴት ልጆችን ዒላማ በማድረግ፣ በከተማዋ በሚገኙ 633 በመጀመርያ ደረጃና 187 በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ 31,500 ሴት ታዳጊ ልጆች ክትባቱን ለመስጠት መታሰቡን ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በላይ ከሆኑት ሴቶች ውስጥ፣ ከአምስቱ አራቱ በሕይወት ዘመናቸው ለማሕፀን በር ካንሰር አምጪ ቫይረስ ተጋላጭ እንደሚሆኑ የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...