Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትጽጌ ዱጉማ፡ የዓለም የ800ሜ አዲሷ ሻምፒዮን

ጽጌ ዱጉማ፡ የዓለም የ800ሜ አዲሷ ሻምፒዮን

ቀን:

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ በዓለም ቤት ውስጥ ሻምፒዮና በመካከለኛ ርቀት በሴቶች 800ሜ አዲስ ኮከብ አትሌት ሆና የተገኘችው ጽጌ ዱጉማ ናት፡፡

 በብሪታኒያ ግላስኮ ከተማ አስተናጋጅነት ለሦስት ቀናት የተካሄደው የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የካቲት 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ሲጠናቀቅ ጽጌ፣ በሴቶች 800ሜ በማሸነፍ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ የሴቶች የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮን በመሆን የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች።

ጽጌ በፈጣን አሯሯጧ እንግሊዛዊቷን ተቀናቃኝ ጄማ ሪኪንን በርቀት ያሸነፈቻት በ2፡01፡90 በሆነ ጊዜ በመፈጸም ነው፡፡ በአገሯና በወገኖቿ ፊት የተወዳደረችው ሪኪ በሁለተኛነት ለማጠናቀቅ የወሰደባት ጊዜ 2:02.72 ሲሆን፣ በ2፡03.15 በመግባት በሦስተኛነት ያጠናቀቀችው ደግሞ የቤኒን ተወላጇ ኖኢሊ ሪጎ ናት፡፡

- Advertisement -

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተገኘችው አዲሷ ኮከብ ጽጌ ለመጀመሪያ ጊዜ በአኅጉራዊ ውድድር ላይ ብቅ ያለችው እ.ኤ.አ. በ2017 በአጭር ርቀት ሲሆን፣ የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና በ200ሜ. አሸንፋለች። በ2019 በኢትዮጵያ ሻምፒዮና በ400ሜ የነሐስ ሜዳሊያ፣ በ2021 ብር እና በ2022 ወርቅ ማግኘቷን በዓለም አትሌቲክስ ዘግቧል። ባለፈው ሐምሌ በቤልጂየም በተካሄደው የ800ሜ መደበኛ ውድድር 1፡59.40 ለመፈጸም  ችላለች፡፡

በእሑዱ ፍጻሜ ከጽጌ ጋር አብራ የሮጠችው ሀብታም ዓለሙ ውድድሯን በአምስተኛነት አጠናቃለች፡፡ውድድሩ በእውነት አስደናቂ እንደነበር ለሚዲያ የገለጸችው አዲሷ ሻምፒዮን ጽጌ፣ የተጠቀመችበት ዘዴ ለአንደኛነት እንዳበቃት ተናግራለች፡፡ ቀጣይ  ትኩረቷ ለፓሪስ ኦሊምፒክ ላይ መሆኑንና ሜዳሊያ ማምጣቷ ጥርጥር የለውም ብላለች።የነሐስ ሜዳሊያ ያሸነፈችው ቤኒናዊት ባለማመን ደስታዋን የገለጸችው በትራክ ላይ በመንከባለል ነው፡፡ ቤኒን በአትሌቲክስ የመጀመሪያዋን የዓለም ሜዳሊያ አሸናፊም ሆናለች።በግላስኮው ሻምፒዮና የመዝጊያ ውድድር በሴቶች 1500ሜ. ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ወርቅ ያገኘችው በፍሬወይኒ ኃይሉ አማካይነት ነው፡፡ ፍሬወይኒ ውድድሯን የፈጸመችው በ4:01.46 ሲሆን፣ ተከታተለው 2ኛና 3ኛ ሆነው የገቡት አሜሪካውያቱ ኒኪ ሂልትዝ (4:02.32) እና ኢሚሊ ማካይ (4:02.69) ናቸው፡፡ ከፍሬወይኒ ጋር ሆነው ሲፎካከሩ የነበሩት ድሪቤ ወልቴጂና ወጣቷ ብርቄ ኃይሎም 5ኛና 9ኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት በ800ሜ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የብር ሜዳሊን የወሰደችው ፍሬወይኒ ኃይሉ፣ ዘንድሮ ወርቅ በማምጣቷ ደስታዋን በመግለጽ፣ ውጤቱ በጣም ጥሩ ነው ብላለች። ‹‹ለዚህ ውጤት ዋናው ነገር በቡድናችን ውስጥ መረዳዳት መኖሩ ነው፤›› ያለችው ፍሬወይኒ፣ ‹‹ጠንክረን በሠራን ቁጥር የተሻለ ውጤት እናገኛለን፣ ዋናው ትኩረቴ የፓሪስ ኦሊምፒክ ነው፤›› ብላለች።ኢትዮጵያ በዘንድሮው የ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ከዓለም አምስተኛ፣ ከአፍሪካ አንደኛ ሆና ለማጠናቀቅ የቻለችው፣ የዓለም ሻምፒዮኗና የ5000ሜ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቷ ጉዳፍ ፀጋይ በ3000ሜ ውድድር ሁለተኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ በማግኘቷና በተመሳሳይ ርቀት በወንዶች ያለፈው ሻምፒዮኑ ሰሎሞን ባረጋ ሦስተኛ ሆኖ በመፈጸሙ የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘቱ ነው፡፡ ሻምፒዮኖቹን የያዘው ብሔራዊ ቡድን ትናንት የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ሲደርስ የክብር አቀባበል ያደረጉለት፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ደኤታዎች አቶ መስፍን ቸርነትና ወ/ሮ ነፊሳ አልመህዲ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...