Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

አዲስ አበባ የደረሱት የዓለም የቤት ወስጥ ሻምፒዮኖቹ

ትኩስ ፅሁፎች

የዓለም አትሌቲክስ ያዘጋጀውና ከየካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት በእንግሊዝ ግላስኮ ከተማ በተካሄደው፣ 19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የተካፈለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዓለም አምስተኛ ከአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን አጠናቋል። ሻምፒዮኖቹን የያዘው ልዑክ ትናንት የካቲት 26 ቀን አዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ሲደርስ የክብር አቀባበል ያደረጉለት፣ የስፖርት ሚኒስትር ደኤታ መስፍን ቸርነትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከስፖርቱ ቤተሰብ ጋር በመሆን ነው፡፡ በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ በሴቶች 800 ሜትርና 1500 ሜትር በጽጌ ዱጉማና በፍሬወይኒ ኃይሉ የወርቅ ሜዳሊያዎችን፣ በሴቶች 3000 ሜትር በጉዳፍ ፀጋይ የብር ሜዳሊያ፣ እንዲሁም በወንዶች 3000 ሜትር በሰሎሞን ባረጋ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ ፎቶዎቹ አትሌቶቹ በግላስኮ የነበራቸውን የልምምድና የውድድር ቆይታ እንዲሁም በአዲስ አበባ የተደረገላቸውን አቀባበል በከፊል ያሳያሉ፡፡

 

አዲስ አበባ የደረሱት የዓለም የቤት ወስጥ ሻምፒዮኖቹ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

አዲስ አበባ የደረሱት የዓለም የቤት ወስጥ ሻምፒዮኖቹ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች