Monday, May 27, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ‹‹በታሪኩ›› ለመጀመሪያ ጊዜ ግዙፍ 20 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ጋር ተፈራረመ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • የአውሮፕላኖቹ ዋጋ እስከ 11 ቢሊዮን ዶላር እንደሚገመት ተገልጿል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ‹በታሪኩ› ካሉት አውሮፕላኖች ግዙፍ ናቸው ያላቸውን እስከ 20 የሚደርሱ የቦይንግ 777-9 አውሮፕላኖች ለመግዛት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

በትናንትናው ዕለት የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰውና የቦይንግ ኩባንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ብራድ ማክሙለር በተገኙበት የፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ተፈጽሟል፡፡

አውሮፕላኖቹ በርካታ ዘመናዊ የሚባሉ ቴክኖሎጂዎችን እንዳካተቱ የተነገረላቸው አውሮፕላን ሲሆን፣ አየር መንገዱ ለመግዛት የመግባቢያ ሰነዱን መፈራረሙንና  በመግዛቱ ከአፍሪካ ቀዳሚ አየር መንገድ ያደርገዋል፡፡

አውሮፕላኖቹ በሁሉም ሊኖሩ በሚችሉ መቆሚያ ቦታዎች እንዲቆሙ ሆነው፣ ክንፋቸውና ሞተሮቹ የተሠሩ ሲሆን፣ ቦይንግ፣ በጥገና በኩል ትንሽ ወጪ የሚያስወጣና በአገልግሎት ደግሞ ለረዥም ጊዜ እንዲያገለግል ሆኖ የተሠራ ነው፡፡ ለተሳፋሪዎችም የተሻለ ምቾት እንዲሰጥና መስኮቱም ሰፋ ያለ ሆኖ የተሠራው ነው፡፡

አውሮፕላኑ 50 የቢዝነስ መቀመጫዎች፣ 390 የኢኮኖሚ መቀመጫዎች፣ በድምሩ 440 መቀመጫዎች እንዲኖሩት ሆኖ ነው የተሠራው፡፡ ይህም ‹‹በኢትዮጵያ አየር መንገድ ታሪክ ትልቁ አውሮፕላን እንደሚሆን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡

እነዚህን 20 አውሮፕላኖችን ጨምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ያዘዛቸውንና ለመቀበል የሚጠብቃቸው አውሮፕላኖች ብዛት ወደ 104 ተጠግቷል፡፡ በነዳጅ ቁጠባ በኩል የቦይንግ 777-9 አውሮፕላኖች ውጤታማና እስከ 10 በመቶ ነዳጅ እንደሚቆጥቡ ነው የተገለጸው፡፡

አየር መንገዱ እ.ኤ.አ. በ2027 ሦስቱን አውሮፕላኖች ለመቀበል የሚጠብቅ ሲሆን፣ በ2029 ደግሞ ሌሎች ሦስት አውሮፕላኖችን ለመቀበል ይጠብቃል፡፡ ቀሪዎቹን ደግሞ ከ2030 በኋላ ለመቀበል እንደሚጠብቁ ነው ዋና ሥራ አስፈጻሚው በሰጡት ማብራሪያ መረዳት የተቻለው፡፡

የአውሮፕላኖቹ ዋጋ ወደ 11 ቢሊዮን ዶላር እንደሚጠጋም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡    

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች