Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየዲጂታል ዕውቅና ያለው የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም የድኅረ ምረቃ የሚሰጥ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ የለም...

የዲጂታል ዕውቅና ያለው የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም የድኅረ ምረቃ የሚሰጥ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ የለም ተባለ

ቀን:

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአይሲቲ መሠረተ ልማትን በማሳደግ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ቢያደርጉም፣ በአሁኑ ጊዜ በዲጂታል መርሐ ግብር ዕውቅና ያለው የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም የድኅረ ምረቃ ትምህርት የሚሰጥ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ እንደሌለ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ያስታወቀው ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን፣ ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲና ከሻያ ሾኔ ተቋማት ጋር በመተባበር ጠንካራ የትምህርት ሥርዓት ለመገንባት በ‹‹E-Learning for Strengthening Higher Education (e-SHE)›› ፕሮግራም አማካይነት የዲጂታል መማር ማስተማር ሥርዓትን የማጠናከር ሥራ እየተገበረ መሆኑን ባስታወቀበት ወቅት ነው፡፡  

ሚኒስቴሩ የትምህርት ተደራሽነትን፣ ጥራትንና አግባብነትን በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል ከያዛቸው ዕቅዶች መካከል አንዱ የ‹‹ገጽ ለገጽ›› (Face to Face) ትምህርትን የሚደግፍ የኤሌክትሮኒክ ወይም ዲጂታል ትምህርት ቴክኖሎጂን በ50 የመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመተግበር ነው፡፡ 

‹‹የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በማስፋፋት ረገድ የሚታይ ለውጥ ያስመዘገብን ቢሆንም፣ የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አንፃር ትልቅ ችግር ውስጥ እንገኛለን፤›› ያሉት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃም (ዶ/ር) ናቸው፡፡

የኤሌክትሮኒክ ወይም ዲጂታል ትምህርት ተደራሽነትንና አግባብነትን በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል አንደኛው አማራጭ እንደሆነ ገልጸው፣ ‹‹በተለይ የገጽ ለገጽና የኤሌክትሮኒክ ትምህርትን ማዋሀድ በተለያዩ አገሮች የሚተገበር ስለሆነ፣ ይህንንም በእኛ አገር ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዶ እየተሠራ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የኤሌክትሮኒክ ትምህርት አሰጣጥ በዓለም ላይ ትልቅና ስመ ጥር በሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ የተናገሩት ሥራ አስፈጻሚው፣ አሁንም በኢትዮጵያ የተጀመረው የትምህርት አተገባበር ሥርዓት ይህንኑ የሚያሳይ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሥነ ምግባር የታነፁ፣ ሥራ ፈጣሪና የሥራ ገበያውን ፍላጎት የሚያሟሉ ምርታማ ዜጎች በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ክፍተት መኖሩን ገልጸዋል፡፡

የኤሌክትሮኒክ ትምህርትን በከፍተኛ ትምህርት ውስጥ ለመጀመር በአዲስ አበባ፣ በባህር ዳር፣ በሐዋሳ፣ በድሬዳዋና በጅማ ዩኒቨርሲቲዎች መልቲ ሚዲያ ስቱዲዮዎች መገንባታቸውን አስረድተዋል፡፡

በአምስት ዓመታት ውስጥ 800 ሺሕ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችንና 35 ሺሕ መምህራንን በዲጂታል የሰው ሀብት ልማት ለመድረስ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

የስቱዲዮዎቹ መሠረታዊ ዓላማ ዩኒቨርሲቲዎቹ የተሻሉ መምህራንና የዲዛይን ባለሙያዎችን በመጠቀም ጥራቱን፣ እንዲሁም አግባብነቱን የጠበቀ የኤሌክትሮኒክ ኮርስ በመቅረፅ ሥራውን ማቀላጠፍ ነው ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ በአቅራቢያቸው የሚገኙ ቢያንስ አሥር ዩኒቨርሲቲዎች የየራሳቸውን ስቱዲዮ እስኪያቋቁሙ ድረስ በጋራ አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በተለይ ዲጂታል መልቲ ሚዲያ ስቱዲዮዎች ተገንብተው ወደ ሥራ መግባታቸው፣ የትምህርት ጥራት ተደራሽነትና አግባብነትን ለማረጋገጥ ተጨማሪ ግብዓት ይሆናሉ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በትምህርት ሚኒስቴር፣ በዩኒቨርሲቲዎችና በአጋር ድርጅቶች ወደፊት ለሚመሠረቱ የመልቲ ሚዲያ ስቱዲዮዎች መነሻ ሆነው እንደሚያገለግሉ ገልጸዋል፡፡  

‹‹ስቱዲዮዎቹ በአጠቃላይ ‹‹E- learning for strengthening Higher Education›› (e-SHE) የሚተገበሩ ሥራዎች የኤሌክትሮኒክ ትምህርትን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ለመጀመር መሠረት የሚጥሉ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የኤሌክትሮኒክ ትምህርት ወዳለበት ዓለም አቀፍ ጥራት ተቋሞቻችንን ለማብቃት ይህንን ሊደግፍ የሚችል የፖሊሲና የስትራቴጂ ለውጥ ለማምጣት፣ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር መሥራት ያስፈልጋል፤›› ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ በትምህርት ጥራትና አግባብነት ረገድ ከፍተኛ ክፍተት እንዳለና ከዚህ በፊትም የተለያዩ ጥናቶችና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የምዘና ሥርዓታችን የሚጠቁሙ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ‹‹እነዚህና መሰል የትምህርት ዘርፍ ተግዳሮቶችን ወደ ሌሎች ቴክኖሎጂ ተኮር የመማር ማስተማር አማራጮች እንድናመራ ያደርጉናል፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡  

የከፍተኛ ትምህርትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ በቴክኖሎጂ መደገፍ መሠረታዊ ነገር ሆኖ በመታየቱና የተሻሉ ተማሪዎች ለማፍራት በመፈለጉ የመልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ ሊቋቋም መቻሉን፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የኤሌክትሮኒክ ትምህርት አሰጣጥ የተሻሉ ምሩቃንን ለማፍራት ለተጀመሩ ሥራዎች ስለሚጠቅም፣ ዩኒቨርሲቲው በዚህ ፕሮግራም መታቀፉ የትምህርት ጥራትን የበለጠ እንዲያሳድግ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ያለው እንደገለጹት፣ የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ወጣቶችን ለሥራና ለሥራ ፈጠራ የሚያስፈልጉ ክህሎቶችን እንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...