Monday, May 27, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በሰሜን ኢትዮጵያ በርካታ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋረጠ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

በአማራ ክልል ክፍል በሦስት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ በደረሰ ጉዳት በርካታ የአማራ፣ የአፋርና የትግራይ ከተሞች ከአገልግሎት ውጪ መሆናቸው ታወቀ፡፡

ደረሰ የተባለው ጉዳት ከደብረ ማርቆስ-ባህር ዳር የተዘረጋው የ400 ኪሎ ቮልት ተሸካሚ በቆይ በተባለች ከተማና በደብረ ወርቅ ከተማ መካከል በደረሰ ችግር ኃይል ባህር ዳር ማከፋፋያ መድረስ አለመቻሉን፣ እንዲሁም ከባህር ዳር – በደብረ ታቦር – ንፋስ መውጫ – ጋሸና – አላማጣ የሚያልፈው የ230 ኪሎ ቮልት ተሸካሚ መስመር ከንፋስ መውጫ ወጣ ብሎ ባጋጠመው ችግር አላማጣ ማከፋፈያ መድረስ አለመቻሉን፣ የአማራ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰሎሞን ጣሰው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም በተመሳሳይ ከለገጣፎ ከተማ ተነስቶ በደብረ ብርሃን-ሸዋ ሮቢት-ኮምቦልቻ ማከፋፈያ ደርሶ ወደ አላማጣ የሚያልፈው የ230 ኪሎ ቮልት መስመር ሸዋ ሮቢት ላይ ባጋጠመው ችግር፣ ኮምቦልቻ ማከፋፈያ መድረስ አለመቻሉን፣ በዚህም ከኮምቦልቻ ተነስቶ ከዓለም ከተማ አቅስታ ማከፋፈያ ለደቡብ ወሎ ዞን ከተሞች የኤሌክትሪክ አግልግሎት ተቋርጧል ብለዋል፡፡

ከሸዋ ሮቢትና ከከሚሴ ከተሞች በስተቀር በአብዛኞቹ የሰሜን ምሥራቅ የአገሪቱ አካባቢዎች ኃይል መቋረጡን፣ እንዲሁም በአማራ ክልል አብዛኞቹ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የገለጹት አቶ ሰሎሞን፣ ከኮምቦልቻ በባቲ መስመር ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የአፋር ክልል መዲና ሰመራ፣ የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች፣ እንዲሁም በወልዲያ አላማጣ መስመር ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የትግራይ ክልል መዲና መቀሌን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ከተሞች ኃይል እንደ ተቋረጠባቸው ተናግረዋል፡፡

አቶ ሰሎሞን የጉዳቱ ምክንያት ግጭት ሊሆን እንደሚችል ግምቶች ቢኖሩም፣ በትክክል ይህ ነው ብሎ መናገር አይቻልም ብለዋል፡፡ ‹‹በትግራይ ክልል ከተከዜ ኃይል ማመንጫ ለማግኘት እየሞከሩ መሆኑን ሰምተናል፤›› ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን የቴክኒከ ቡድን እያሰማራን ነው ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ መድረስ የማይቻልባቸው ቦታዎች መኖራቸውን ገልጸው፣ ረቡዕ የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚቻለው ሁሉ ተደርጎ የተቋረጠውን ኃይል ለማስጀመር ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች