Tuesday, April 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናበአክሲዮን አሻሻጥ ላይ የተሠሩ ወንጀሎችን ወደኋላ በመመለስ ምርምራ ይደረጋል ተባለ

በአክሲዮን አሻሻጥ ላይ የተሠሩ ወንጀሎችን ወደኋላ በመመለስ ምርምራ ይደረጋል ተባለ

ቀን:

በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አነሳሽነት የተዋቀረው በርካታ የመንግሥት ተቋማት ያሉበት የካፒታል ገበያ ተዓማኒነት ግብረ ኃይል፣ በአክሲዮን መሸጥና መግዛት ላይ የተሠሩ ወንጀሎችን ወደኋላ በመመለስ እንደሚመረምር ተገለጸ፡፡

ባለሥልጣኑ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ እንዲሁም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያሉበት የካፒታል ገበያ ተዓማኒነት ግበረ ኃይል ዋነኛ ኃላፊነቱ፣ በማጭበርበርና በሕገወጥ የአክሲዮን ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን መለየትና ለፍትሕ ማቅረብ ነው፡፡

በርካታ መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ በመጭበርበር አክስዮን እየገዙ ያሉ ግለሰቦችን ለመጠበቅና ጥፋተኞችን ለሕግ ለማቅረብ መሥራት እንደሚጀምር የተነገረለት ግብረ ኃይሉ፣ ወደኋላ በመመለስም በአክሲዮን አሻሻጥ ላይ ወንጀሎች ተብለው የተለዩ ጉዳዮችንም በመተንተን እንደሚሠራ የባለሥልጣኑ ኃላፊዎች አሳውቀዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የባለሥልጣኑ ኃላፊዎች ይህን ያሳወቁት፣ የሁሉም ተቋማት ኃላፊዎች በተገኙበት ሐሙስ የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም. በቤስት ዌስተርን ፕሪሚየር ዳይናስቲ ሆቴል የመግባቢያ ሰነድ በተፈራረሙበት ወቅት ነው፡፡

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘለዓለም መንግሥቴ፣ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ፣ እንዲሁም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የግብረ ኃይሉን የምርመራና ወንጀለኞችን ተጠያቂ የማድረግ ሥራ በሚመለከት ከሪፖርተር ለተነሳላቸው ጥያቄ ማብራሪያ የሰጡት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ‹‹በቂ የሆነና ፍርድ ቤት ተወስዶ ሊያስቀጣ የሚችልበት መረጃ›› እስካለ ድረስ፣ ወደኋላም በመሄድና በመመርመር ግብረ ኃይሉ ለፍርድ እንደሚያቀርብ ተናግረዋል፡፡

‹‹ወንጀል እስከተሠራ ድረስ በአገሪቱ ሕግ መሠረት መሠራት ያለበት ነገር አለ፤›› ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የንግድ ሕጉን ምሳሌ በመግለጽ አክሲዮን የሚሸጡ ድርጅቶች የኢንቨስትመንት መግለጫ አዘጋጅተው ለኢንቨስተሩ መስጠት እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡ ‹‹በቴሌቪዥን ማስታወቂያ ከሚያስነግሩት የትኞቹ ናቸው የኢንቨስትመንት መግለጫ ሰጥተው የሚያውቁት?›› ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

በንግድ ሕጉ የተቀመጠውን ድንጋጌ ከመጣስ ባሻገርም፣ ‹‹መመርያ ኖረም አልኖረም›› በካፒታል ገበያ አዋጅ መሠረት የሚጠይቁ መሥፈርቶችንም ጥሰው የሚሠሩ እንዳሉ ገልጸዋል፡፡

ግብረ ኃይሉ በአጠቃላይ ገበያ ውስጥ ያሉት እንቅስቃሴዎች ምን እንደሆኑ፣ ምን ጉድለት እንዳለባቸው፣ እንዲሁም እንዴት መሥራት እንዳለባቸው እያየ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ባለሥልጣናት ከሌሎች ቴክኖሎጂ ላይ መሠረት አድርገው የደኅንነት ሥራዎች ከሚሠሩ የመንግሥት ተቋማት ጋር፣ የቴክኖሎጂን መሠረተ ልማትና አቅም ለማሳደግ የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ተቋማቱም የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ እንዲሁም የብሔራዊ መታወቂያ ሲሆኑ የሁሉም ተቋማት ዋና ኃላፊዎች ከካፒታል ገበያ ዋና ዳይሬክተር ጋር በሥነ ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...