Tuesday, April 23, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ አክሲዮን ማኅበርን ለማቋቋምና ከሚያስፈልገው አንድ ቢሊዮን ብር ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነውን ካፒታል ማሰባሰብ መቻሉን ገለጸ፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ላይ የ50 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ግዥ መፈጸሙን አስመልክቶ በተደረገው የፊርማ ሥርዓት ላይ እንደተገለጸው፣ እስካሁን ኩባንያው ለማሰባሰብ ካቀደው አንድ ቢሊዮን ብር ውስጥ ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ ችሏል፡፡

የአክሲዮን ኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን ካሳሁን (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ አሁን የታየው የአክሲዮን ሽያጩ አፈጻጸም የአክሲዮን ሽያጩ የማጠናቀቂያ ጊዜ ነው ተብሎ ከተቀመጠው ማርች 29 ቀን 2024 በፊት አክሲዮን ኩባንያውን ለመሥራት የሚያስችለው ካፒታል ይሟላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከማርች በፊት ይህንን አክሲዮን የገዙት የግል ዘርፉ ኩባንያዎች ቁጥርም ከ25 በላይ መድረሱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከዚህ ውስጥ የ50 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ከገዛው ግሎባል ባንክ ኢትዮጵን ጨምሮ እስካሁን ወደ 15 የሚሆኑ ባንኮች አክሲዮኖችን የገዙ ስለመሆናቸው ታውቋል፡፡ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የገዛው የ50 ሚሊዮን ብር አክሲዮን በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ አክሲዮን ኩባንያ ውስጥ የአምስት በመቶ ባለቤት ድርሻ እንዲኖረው ያስችለዋል፡፡

በአሁኑ  ወቅት የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ከፍተኛ ለውጥ ላይ ያለ መሆኑን የገለጹት የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የኮርፖሬት ስትራቴጂ ትራንስፎርሜሽን አሲስታንስ ቺፍ ኦፊሰር ወ/ሮ መዓዛ ወንድሙ ለዚህ ማሳያ የሚሆነውን ለውጭ ባንኮች ገበያው መክፈት አንዱ ነው፡፡

ከዚህም ሌላ እንደ ካፒታል ገበያ መፈጠርና የመሳሰሉ ተግባራት የፋይናንስ ዘርፉን ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሸጋገረው ስለሆነ ባንካቸው ይህንን ለውጥ ተከትሎ በተፈጠሩት አዳዲስ አሠራሮ ላይ ተሳትፎውን ለማጉላት ከESX ጋር አብሮ ለመሥራትና የኩባንው ባለድርሻ ለመሆን ውሳኔ በማሳለፍ የ50 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ሊገዛ መቻሉን ገልጸዋል፡

በካፒታ ገበያ ውስጥ እንዲህ ባለው ሁኔታ ተሳታፊ መሆናቸው እንደ አገር ያለወን ጠቀሜታ በማሰብ ጭምር መሆኑን ያስረዱት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ በዚህ ኢንስትመንት ውስጥ መሳተፍ ለባንካቸውም ሆነ ለአገር ጠቃሚ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ኩባንያውን ለማቋቋም የሚያስፈልገውን ካፒታል ለማሟላት ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ የቆየ ሲሆን፣ እስካሁን ያሰባሰበው የካፒታል መጠንም አክሲዮን ኩባንያውን ለማቋቋምና ኩባንያውን ሥራ ለማስጀመር አስፈላጊ የሆነ የቴክሎጂ ግዥዎችን ለመፈጸም ያስችላል ተብሏል፡፡ አክሲዮን ኩባንያው እስከ መስከረም 2017 ዓ.ም. በይፋ ሥራ ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡

‹‹ገበያውን ለማደራጀት መጀመሪያ የሚያስፈልገው ካፒልትና የሰው ኃይል ነው፤›› ያሉት ሥራ አስፈጻሚው፣ የገበያው መመርያዎችና ውሎች ቀደም ተብሎ ሲሠራ የቆየ በመሆኑ ከምሥረታው በኋላ ሥራውን ለመጀመር የማይከበድ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ሌላው ኩባንያውን ሥራ ለማስጀመር ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገበት ያለው ጉዳይ የቴክኖሎጂ ግዥ ሲሆን፣ ይህንን ቴክኖሎጂ ለመግዛት ጨረታ ወጥቶ በሒደት ላይ እንደሚገኝና በቅርቡም ይፋ እንደሚደረግ ታውቋል፡፡    

የአክሲዮን ሽያጩ ኩባንያው ሥራ በአብዛኛው ከባንክ ሥራ ጋር በጣም የተሳሰረ እንደሆነ የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ አብዛኛዎቹ ባንኮች የአክሲዮን ግዥ መፈጸማቸውን ተጠቁሟል፡፡

የአክሲዮን ግዥ የፈጸሙ የውጭ የሚጠብቁት ኩባንያዎችን ማንነት ከመግለጽ ቢቆጠቡም፣ ልምድ ያላቸው የአክሲዮን ገበያ ኩባንያዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የዚህ ኩባንያ ዋነኛ ዓላማ 120 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የፋይናንስ ተደራሽነትን፣ ቁጠባንና ኢንቨስትመንቱን ማለማመድ ነው፤›› ያሉት ሥራ አስፈጻሚው፣ የካፒታል ገበያ ሥርዓት መምጣት በርካታ ጠቀሜታዎች ያሉት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በተለይ ባንኮች የማይደርሱበትን ሥራ መሥረትና ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ ካፒታል በማሰባሰቡ ረገድ አማራጭ በመፍጠር ኩባንያው ትልቅ ሥራ ይሠራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡

የአገሪቱ ኢኮኖሚ የፋይናንስ ፍላጎትን በተመለከተ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ፣ የግል ዘርፉ ብቻ በሚቀጥሉ 10 ዓመታት ቢያንስ እስከ 20 ትሪሊዮን ብር እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡

በመንግሥት በኩልም በሚቀጥሉት አሥር ዓመት ያስፈልጋል ተብሎ የሚታሰበው ከ10 ትሪሊዮን ብር ያላነሰ በመሆኑ፣ ይህ ከፍተኛ የፋይናንስ ፍላጎት በባንኮች ብድር ብቻ ሊሳካ እንደማይችል ጠቁመዋል፡፡

የፋይናንስ ፍላጎቱ ከፍተኛ ስለመሆኑ በምሳሌነት ባቀረቡት መረጃ በ2015 የሒሳብ ዓመት የኢትዮጵያ ባንኮች ያበደሩትን የገንዘብ መጠን ከ500 ቢሊዮን ብር የማይበልጥ መሆኑን ነው፡፡

ከዚህ ውጪ በቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትና ከሌላ የፋይናንስ ምንጭ የሚገኘው ፋይናንስ ተደማምሮ ዓመታዊ የፋይናንስ ፍሰቱ ከአንድ ትሪሊዮን ብር እንደማይበልጥ ተናግረዋል፡፡

በአክሲዮን ኩባንያው ዕቅድ መሠረት አብዛኛው የፋይናንስ ፍላጎትን በተቻለ መጠን በአገር ውስጥ እንዲሸፈን ማድረግ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡  

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አገናኝ አባላት እንዳሉት ሁሉ መዋዕለ ንዋይ ገበያውም አገናኝ አባላት እንደሚኖረው፣ ለዚህም ራሱን የቻለ የፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት እንደሚዘረጋ ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን አብዛኛዎቹ ካፒታል ገበያ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ፈቃድ የሚያገኙት ከካፒታ ገበያ ባለሥልጣን ሲሆን፣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ግን ሙሉ በሙሉ የመንግስት ተቋም ነው፡፡

አሁን የኩባንያው ባለአክሲዮኖች የሆኑ ባንኮች ቁጥር 15 ቢሆንም፣ ባንኮች ባለአክሲዮን ባይሆኑም ከኩባንያው ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚሠሩ መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህም አንደኛው የሚሠሩበት መንገድ ቀጥታ የአክሲዮን ኩባንያው ባለቤት በመሆን ትርፍ የሚጋሩበት፣ ሁለተኛው ደግም ባንኮቹ እንደ ኢንቨስትመንት ባንክ ሆነው ሲመጡ ደግሞ አገልግሎት ሰጪ ሆነው እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡

ሌላው ደግሞ አክሲዮን ኩባንያው ላይ ኢንቨስትም ባያደርጉ ኢንቨስትንት ባንክ ባይሆኑም ዕለት ዕለት የትሬዠሪ ሥራ ሲሠሩ ከአክሲዮኑ ኩባንያው ጋር መገናኘታቸው እንደማይቀርም ጥላሁን (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

አክሲዮን ሽያጩ በፍላጎት የሚፈጸም በመሆኑ እስካሁን አክሲዮን ከገዙት የፋይናንስ ተቋማት በተጨማሪ ሌሎቹም ወደፊት የአክሲዮን ባለድርሻ ለመሆን የሚችሉበት ዕድል እንዳለ ተገልጿል፡፡

አክሲዮኖችን ያልገዙ የፋይናንስ ተቋማት ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? ለሚለው ጥያቄ ጥላሁን (ዶ/ር)፣ መሥራች ባለአክሲዮኖቹ በሚያስቀምጡት ዋጋ መሠረት አክሲዮን ገዝተው ሊገቡ እንደሚችሉ ጠቁመሟል፡፡

የውጭ ኩባንያዎች የዚህ አክሲዮን ማኅበር መሥራች አባል ሆነው እንዲገቡ ፍላጎት ያለ በመሆኑ እነሱ እየተጠበቁ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ምናልባትም እነሱ አዎንታዊ መልስ እስኪሰጡ ድረስ ትንሽ ጊዜ ገፋ ሊያደርግ እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡     

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች