Saturday, May 18, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ፍሬከናፍር‹‹በየቀኑ ሟቾችን እየቆጠርን በኀዘን ለመኖር የተፈረደብን ሆነናል››

‹‹በየቀኑ ሟቾችን እየቆጠርን በኀዘን ለመኖር የተፈረደብን ሆነናል››

ቀን:

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. የተያዘውን የጾመ ነነዌ አስመልክቶ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ፡፡ በነነዌ ጾም መቀበያ ዋዜማ ላይ፣ በቤተክርስቲያኒቱ ጥንታዊ ከሆኑት ገዳማት አንዱ በሆነው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የሚገኙ መነኮሳት የሰማዕትነትን ጽዋ ተጎንጭተዋል ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ዓለሙን ትተው በፈቃዳቸው ረሀብተኛ እና ጥማተኛ ሆነው አገርን በጸሎት የሚጠብቁ መነኮሳት ጫካው መኖሪያችሁ፣ ዳዋው ልብሳችሁ፤ ቅጠሉ ምግባችሁ መሆን አይችልም ተብለው በሥጋ መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ለእነርሱ ክብር ቢሆንም ለቤተክርስቲያን ግን ታላቅ ደወል ያሰማ ክስተት ነውና ውሉደ ክህነት ቤተክርስቲያናችሁን የምትጠብቁበት፣ የመከራውን ማዕበል ለማለፍ በመንፈሳዊ ፍቅር አንድነትን ማጽናት የሚያስፈልግበት ጊዜ መሆኑን አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም ታላቅ አገር ይዘን፣ ምድሩ ሳይጠበን አመል እያጋፋን ነውና ጾማችን፣ ጸሎታችን ከእግዚአብሔር ፊት ደርሶ ለአገር ደኅንነት፡ ለሕዝብ ድኅነት እንዲያመጣልን፣ እግዚአብሔር ይቅር ብሎን ዘመኑን በምሕረት ያሻግረን ዘንድ በታላቅ ንስሐ፣ በጸሎትና በአስተብቍዖት ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ አባታዊ መልዕክታችንን በመሐሪው አምላክ ስም እናስተላልፋለን ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ