Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

እስቲ በዚች አንቀጽ ትንሽ እንቆዝም!

ትኩስ ፅሁፎች

ጳውሎስ ኞኞ በአገር ፍቅር ስሜት የተቃጠለ ጸሐፊ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ይሁን እንጂ ለአቡነ ማቴዎስ በትክክል የፈረደላቸው አይመስለኝም፡፡ አቡኑ በትውልድ ግብፃዊ ቢሆኑም ታማኝነታቸው ለሃይማኖታቸውና ለኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ነበር፡፡ ያም ሆኖ በአጋጣሚ ከሃይማኖታቸውን የሚቃረን የመንግሥት ሐሳብ ቢገጥማቸው፣ ለሃይማኖታቸው ማድላታቸው የመርህ ሰው ያስኛቸዋል እንጂ ከሀዲ አያስብላቸውም፡፡ ስለዚህ ‹‹የኢትዮጵያ ጉዳይ ጉዳያቸው ስላልሆነ›› የሚለው የጳውሎስ ኞኞ ክስ ምንም መሠረት የለውም፡፡

በንጉሠ ነገሥቱና በፓትርያርኩ መካከል ልዩነት አለ፡፡ ንጉሡ ካለው ሁኔታ አንፃር የሚያዋጣውን የሚመርጡ ‹‹ፕራግማቲስት›› የፖለቲካ ሰው ናቸው፡፡ ሀቀኛ የሃይማኖት መሪ ከሆንህ ግን ሁኔታው ተለወጠ ብለህ የምትለውጠው አይኖርም!

በጊዜው ንጉሡ ሰይፍ ታጥቂያለሁ ብለው ‹‹አንተ የምስር ነጫጭባ! ትፈታለህ ብያለሁ ትፈታለህ?›› ብለው አለመሳፈጣቸው ዕርፍና ይመስለኛል፡፡ ቤተ መንግሥት በሠራዊቱ ተማምኖ በቤተ ክህነት ውስጥ አለመግባቱ ሥልጣኔ ነው፡፡

አፄ ምኒልክም ሆነ ተራኪው ጳውሎስ የበላ ወታደር ከጾመ ወታደር የተሻለ ይዋጋል የሚል አስተሳሰብ ነበራቸው፡፡ ዘመናዩ ሳይንስ ግን ጾም የተሻለ ጉልበት እንደሚያጎናጽፍ ደርሶበታል፡፡ ስትጾም ለጽሞና፣ ለዕርጋታ የሚያግዙ ሆርሞኖችን ማምንጨት ትችላለህ! አንዱ የምግብ ምርምር ሊቅ በቅርቡ ሲናገር እንደሰማሁት፣ ‹‹የተራበ ተኩላና የጠገበ አንበሳ ቢታገሉ ተኩላው ያሽንፋል፡፡ የተራበ ተኩላ በሙሉ ኃይልና ቁርጠኝነት ነው የሚፋለመው፡፡ የጠገበ አንበሳ ግን ማረፍና መተኛት ነው የሚፈልገው፡፡

ምናልባት የዓድዋ ላይ አርበኞች፣ ከጠላቶቻቸው በሚልቅ ጉልበትና ወኔ የተዋጉበት ምክንያት ስለጾሙ ይሆን? እንዲያ ከሆነ ደግሞ አቡነ ማቴዎስም (ባለማወቅም ቢሆን) ለአርበኞች ተጨማሪ ጉልበት አከፋፍለዋል ማለት ነው፡፡

  • በዕውቀቱ ሥዩም
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች