Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የፍትሕ አርበኛ አስፈላጊነት

ትኩስ ፅሁፎች

‹‹ተላላ ነው አገር ተላላ ነው ይሄዳል እንደ ሰው

ጀግና ተሯሩጦ ሄዶ ካልመለሰው።››

የፍትሕ አርበኝነት ፈርጀ ብዙ ነው። የሆነው ሆኖ ባለቤት ካልጮኸ ጎረቤት አይረዳም ይባላል። የአገር ባለቤት አገር ሲጎዳ ዓይቶ ዝም ማለት የለበትም። የአገርና የመርህ ፍቅር ለፍትሕ ወሳኝ ናቸው። አገር ወዳድ ግለሰቦች በግብረ ገብነትና በራስ መተማመን ከፍ ያሉ ስለሆኑ በማኅበረሰባቸው ውስጥ ያለውን የሥነ ምግባር፣ የፍትሕና ርትዕ መርሆዎች የመጠበቅና የማስጠበቅ ፍላጎታቸው ከፍተኛ ነው። ለዚህ ዓላማ ይታመናሉ፣ ይኖራሉ፣ ይጎዳሉ፡፡ እና አስፈላጊ ሲሆን ያለ ስስት በፈገግታ ይሞታሉ። የነፃነት ዛፍ ሲደርቅ በጀግኖች ደም ይለመልማል እንዳለው ቶማስ ጀፈርሰን። ግለሰቦች ፍትሐዊነትን፣ እኩልነትንና የሕግ የበላይነትን በማክበር ላይ እንዲሠሩ ያነሳሳሉ። እነዚህ የመርህ ሰዎች ለፍትሕ በመቆም፣ ሙስናን በመዋጋት፣ የዜጎችን መብትና ነፃነት በማስከበር ግምባር ቀደም ናቸው። ኢፍትሐዊነትን ፊት ለፊት ይጋፈጡታል እንጂ አያጎነብሱለትም።

ጀግኖች አርበኞች የፍትሐዊ ሕግ ሥርዓት አስፈላጊነትን ይገነዘባሉ። ኅብረተሰቡ የዜጎችን መብትና ነፃነት የሚጠብቅ ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍና ተግባር ከሌለው መበልፀግ እንደማይችል ተገንዝበው በማይመች ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑ እንኳን ለሌሎች ያስገነዝባሉ። አርበኞች በሕግ ሥርዓቱ ላይ በንቃት ይሳተፋሉና ይደግፋሉ፣ ፍትሕ እንዲሠፍንና ማንም ከሕግ በላይ እንዳይሆን ይታገላሉ። እያንዳንዱ ግለሰብ በከበሬታና ፍትሐዊ በሆነ መልኩ እንዲስተናገድ ያበረታታሉ።

አርበኞች ሰብዓዊ መብቶችን በመደገፍና በመጠበቅ ግንባር ቀደም ናቸው። በእያንዳንዱ ግለሰብ የተፈጥሮ ክብርና ዋጋ ያምናሉ፡፡ እናም እነዚህን መብቶች በኅብረተሰባቸው ውስጥ ለማስጠበቅና ለማስተዋወቅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ይሠራሉ። አርበኞች አድልኦን፣ ጭቆናንና ኢፍትሐዊነትን በመቃወም ከተገለሉት ወይም ከተቸገሩት ጎን ይቆማሉ። የመናገር የመሰብሰብና የሃይማኖት ነፃነት፣ እንዲሁም ፍትሐዊና ግልጽ የፍትሕ ሒደት የማግኘት መብት እንዲከበር ይታገላሉ። አርበኞች ሰብዓዊ መብቶችን በንቃት በመጠበቅ ፍትሐዊና ሁሉን አቀፍ ማኅበረሰብ ማለትም ሪፐብሊክ እንዲመሠረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ።

እውነተኛ ፍትሕ ከሕግ ሥርዓት በላይ የሚሄድ፣ ሰብዓዊነትና መንፈሳዊነት፣ ብሎም የአገር ማኅበራዊ ትስስር የሚሸፍን መሆኑን ይገነዘባሉ። ፍትሐዊ፣ እኩልና ሁሉንም ያካተተ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ይሠራሉ። አርበኞች እንደ ድህነት፣ የትምህርት ዕድል ልዩነቶችና የጤና አጠባበቅ ተደራሽነት ያሉ ማኅበራዊ እኩልነት ለሚመለከቱ ፖሊሲዎች ይሟገታሉ። ሕዝቡን ያነቃሉ። ሁሉም ሰው የመሳካትና የመልማት እኩል ዕድል እንዲኖረው በማረጋገጥ በተጠቃሚዎችና በተገለሉት መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ይጥራሉ። ማኅበራዊ ፍትሕን በማሳደግ አርበኞች ለኅብረተሰባቸው ሁለንተናዊ ደኅንነትና ስምምነት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

  • መስፍን ሙሉጌታ (ዶ/ር) ‹‹ፍትሐዊ ሪፐብሊክ››
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች