Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

እኔ ያንቺ ጀግና

ትኩስ ፅሁፎች

ዘራፍ እኔ ወንዱ ዘራፍ የነጩ ጌታ!፣

በጥቁር ማልገታ ዝናሬን ማልፈታ፤

ከቶ ማልምታታ ዘራፍ፣

ፍ!

እኔ ወንዱ…፣

ለሺ ሽንታም እበቃለሁ አንዱ…፤

የምለብስ ቀጭን ኩታ፣ ሳርስ የምውል በኮታ፣

ባልሽን የገጠምኩ ለታ ያኔ ነው ደስታ፤

ብዬ ፎክሬ መልክ አሳምሬ፣

ያዘኝ ባልሽ እንደ ጥማድ በሬ፤

ፈትጎኝ እንደ ገብስ ግቢ ውጪ ነፍስ፣

አፀፋ ለመመለስ ከእሱ ላለማነስ፤

ነፍስ ስዘራ ደሞ በከዘራ፣

ምን ዓይነት ጨካኝ ነው ልቡ ማይራራ፤

ደጃፍሽ ላይ ደሜን ስዘራ፡፡

አልቻልኩም ዓለሜ ተዋረድኩልሽ፣

ሁለተኛ ላልመኝ የሰው ስርቆሽ፤

አቅም ሳጣ ለመሸሽ፣

ምን ላድርግ ኡ! ኡ! ኡ!፤

ብዬ ጮኽኩልሽ፡፡

                                          – ናትናኤል ኤርሚያስ

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች