Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊከተቆጣጣሪውም የተሠወሩ ሕገወጥ ምግብ አምራቾች

ከተቆጣጣሪውም የተሠወሩ ሕገወጥ ምግብ አምራቾች

ቀን:

በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጪ በርካታ ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች ይሠራጫሉ፡፡ ከእነዚህ ምርቶች ምን ያህሉ በሕገወጥ መንገድ ገብቷል? ወይም ተመርቷል? የሚል ጥልቅ መረጃ ባይኖርም፣ በተለያዩ ጊዜያት የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን መድኃኒትና የተለያዩ ምግብ ነክ ምርቶችን ‹ሕገወጥ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ፣ መሥፈርት አላሟሉም› በማለት ከገበያ እንዲሰበሰቡና እንዲወገዱ ማድረጉን ሲገልጽ ይሰማል፡፡ በቅርቡ አምራቹና ይዘቱ የማይታወቅ የዘይትና የጨው ምርት መያዙንና ኅብረተሰቡም ምርቶቹን እንዳይጠቀም ማሳሰቡም ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ አስገዳጅ ደረጃቸውን ሳያሟሉ ጥራታቸውን ያልጠበቁና ኅብረተሰቡን ለጤና ጠንቅ የሚዳርጉ ምግቦችና መጠጦች ተመሳስለው፣ በፋብሪካ ተመርተው ለገበያ እየቀረቡና ሸማቹን እያደናገሩት ያሉ ምርቶች ተበራክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ያወጣውን አስገዳጅ ደረጃ ሳያሟሉ የተገኙ ምግቦችና መጠጦችን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን በየወቅቱ ከገበያ እየሰበሰበ ያስወግዳል፡፡

- Advertisement -

ባለሥልጣኑም 44 ዓይነት የምግብ ዘይት፣ 39 በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው ዓይነቶችን ደኅንነታቸው ያልተረጋገጡና የት እንደተመረቱ ያልታወቁ ናቸው በማለት ከገበያ እንዲወጡ፣ ኅብረተሰቡም እንዳይጠቀማቸው አግዷል፡፡

እነዚህን ምግቦችና መጠጦች ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም ከማሳሰብና ወደ ገበያ ከቀረቡ በኋላ እየሰበሰቡ ከማንሳት ይልቅ፣ ከመመረታቸው በፊት ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ ለምን አልተቻለም? ለሚለው የምግብና የመጠጦች ኢንዱስትሪና ምርምር ልማት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ በቀለ መኩሪያ ምላሽ ሰጥተውናል፡፡

እንደ ሥራ አስኪያጁ፣ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምግቦች በኮንትሮባንድ ገብተው ይሁን፣ ተመሳስለው ተሠርተው፣ እንዴትና ከየት እንደሚሠሩ ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል፡፡

በትክክለኛው መንገድ ደረጃቸውን ጠብቀው የሚመረቱ ምርቶችን ከጥሬ ግብዓታቸው ጀምሮ ለምግብነት እስኪበቁ ድረስ፣ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደረግላቸው የሚናገሩት አቶ በቀለ፣ በዚህ ሒደት ተመርተው ለገበያ የሚቀርቡ ማናቸውም ምግቦችና መጠጦች በጤና ላይ የሚያደርሱት እክል እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ በድብቅ ተመሳስለው ጥራታቸውን ሳይጠብቁ ሕገወጥ በሆነ መንገድ ተመርተው ለገበያ የሚቀርቡ ምግቦች በብዛት ሊኖሩ እንደሚችሉ የተናገሩት አቶ በቀለ፣ ድርጊቱ በሰዎች ጤና ላይ የሚያደርሰውን የጤና እክል በመገንዘብ ሁሉም ሰው ሕገወጥ አምራቾችንም ሆነ አቅራቢዎችን ለሕግ አሳልፎ በመስጠት የመፍትሔ አካል መሆን እንዳለበት ይመክራሉ፡፡

ምግብና መጠጥ ነክ ነገሮችን የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎችን የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር በሚያደርገው የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምር ልማት ማዕከል በበኩሉ፣ እስካሁን በተመዘገቡ ፋብሪካዎች በሚመረቱ ምርቶች ምንም ዓይነት የጥራት መጓደልም ሆነ ከደረጃ በታች የሆኑ ምግቦችና መጠጦች ሲመረቱ አለመገኘቱን ሥራ አስኪያጁ አክለዋል፡፡

ነገር ግን በሕገወጥ መንገድ በኢንዱስትሪ ተመርተው ያለ ምንም መለያ (ብራንድ) ጥራታቸውን ሳይጠብቁ ገበያ ላይ የሚውሉ ምግቦች ‹‹ከየት መጡ?›› ለሚለው ለእነሱም እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው ያስረዳሉ፡፡

አመሳስለው የሚያመርቱ ሕገወጦችን ተከታትለው ለመያዝና መነሻቸውን ለማወቅ ቢሞክሩም፣ እንዳልተሳካላቸውና ሕገወጥ አምራቾችን መያዝ እንዳልቻሉ ጠቁመዋል፡፡

በሕገወጥ መንገድ የሚመረቱ ምግቦች በጤና ላይ ከሚያደርሱት አሉታዊ ተፅዕኖ ባሻገር፣ ጤናን ሊጠብቁ ወይም በሽታን ሊከላከሉ የሚችሉ ንጥረ ምግቦች ሳያሟሉ ሊቀሩ ስለሚችሉ በቀጥታ የጤና እክል ባያስከትሉም በሽታን የመከላከል አቅማቸው ደካማ ሊሆን ይችላል ሲሉ ያስረዳሉ፡፡  

በድብቅ የሚያመርቱ አምራቾች የኢትዮጵያ ስታንዳርድ ኢንስቲትዩት የሚጠይቀውን ደረጃ እንደሚያሟሉ፣ በዚህ መንገድ የሚያመርቱትም ከግንዛቤ ጉድለት፣ ከመሥሪያ ቦታ እጥረት፣ ከራስ ወዳድነትና ከመሳሰሉት እንደሚመነጭ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ ተቋማት ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ባህሩ ታደሰ ይገልጻሉ፡፡

በሕገወጥ መንገድ ሲያመርቱ የተገኙ ግለሰቦች መኖራቸውን ጠቅሰው፣ የሚያመርቱበት ማሽን፣ የሰው ኃይል አጠቃቀማቸውና የሚያመርቱበት ቦታ ታይቶ ሕጋዊ ማረጋገጫ እንዲሰጣቸው መደረጉንም ያክላሉ፡፡

ደረጃቸውን ሳይጠብቁ የታሸጉ ምግቦችን ለገበያ የሚያቀርቡ ነጋዴዎች በምክርና በማስጠንቀቂያ፣ አለፍ ሲል የሚሠሩበትን ቦታ በማሸግ የሚወሰደው ዕርምጃ፣ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምግቦች በሰዎች ላይ ከሚያደርሱት የጤና እክል አኳያ በቂ አይደለም የሚሉት አቶ ባህሩ፣ ይህንን ሲፈጽሙ የተገኙ ግለሰቦች ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ታይቶ ቅጣት እንደሚወሰንባቸው ጠቁመዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...