Monday, May 20, 2024
Homeስፖንሰር የተደረጉየኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ በፋው የቤስቲዩን ኢ05 ናት (BESTUNE E05) የኤሌክትሪክ መኪና...

የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ በፋው የቤስቲዩን ኢ05 ናት (BESTUNE E05) የኤሌክትሪክ መኪና ይቀላቀሉ

Published on

- Advertisment -

በኢትዮጵያ የትራንስፖርትና የኤሌክትሪክ ዘርፍ በመሰማራ ቀዳሚው የንግድና የአቅርቦት አጋር ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ (ኢቢጂ)፣ ከሚያቀርባቸው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ ቤስቲዮን ኢ05 ናት (BESTUNE E05) የኤሌክትሪክ መኪና ሲያቀርብ በደስታ ነው።

በቻይና ትልቁና እድሜ ጠገቡ የመኪና አምራች በሆነው ፋው ግሩፕ የተሰራው BESTUNE E05፣ ለአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ቁንጮና ልዩ ፈጠራ የታከለበት ነው።

ኢቢጂ የተለያዩ ሞዴል ያላቸው የፋው ትራኮችን፣ ቤስቲዩን አውቶሞቢሎችን፣ ማዝዳ ፓሴንጀር፣ ቀላል የንግድ መኪኖችን እንዲሁም ሻንቱ የግንባታ ቁሳቁሶችን በማቅረብ የሚታወቅ ተአማኒ ኩባንያ ነው።

ባካበተው የዓመታት ልምድና ባለው ኃላፊነት፣ ኢቢጂ የመንገደኞችን የመጓጓዣ ልምድ ለማዘመንና በቤስቲዩን የመጓጓዝ ልምድን ለማምጣት አልሞ እየሰራ ነው።

የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ በፋው የቤስቲዩን ኢ05 ናት (BESTUNE E05) የኤሌክትሪክ መኪና ይቀላቀሉ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ በፋው የቤስቲዩን ኢ05 ናት (BESTUNE E05) የኤሌክትሪክ መኪና ይቀላቀሉ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ቤስቲዩን ኢ05 ናት ካሉት የተለያዩ ባህሪያት መካከል ለየት ባለ ዲዛይንና (ቅርፅ) መሰራቱ አንዱ ነው።  ቤስቲዩን ኢ05 ናት፣ ልዩ ዲዛይን ከመላበሱ በተጨማሪ፣ ጠንካራ የሰውነት ክፍል (ቦዲ)ና ማራኪ የውስጥ ክፍል ያለው ድንቅ የአረንጓዴ ሃይል ልማት አካል የሆነ መኪና ነው።

የአሽከሪካሪው ክፍል በተለየ ሁኔታ የተሰራ ሲሆን፣ ልኬቱም 500 mm x 1020 mm ነው።

ምቹ የሆነው መቀመጫውም 450 mm x 480 mm ስፋት ያለው ሲሆን፣ ምቹ ለማድረግም ለስላሳ ፎም የተገጠመለት ነው።

የመቀመጫ መደገፊያው 177 ዲግሪ ማዕዘን አለው። በስድስት አይነት የማኑዋል አማራጭ መቀመጫውን ማስተካከልም ይቻላል። አማራጭ የአየር ማናፈሻና የእያንዳንዱን ተጓዥ ምቾት የሚያስጠብቅ በአራት መንገድ በኤሌክትሪክ የሚሰራ የወገብ መደገፊያ አለው።

ከዚህ በተጨማሪም ከC-class መኪኖች ጋር ሲነፃፀር፣ 1007 mm የሚረዝም ሰፊና በቂ የእግር ማስቀመጫ ስፍራ አለው።

የፊት ተሳፋሪ የመቀመጫ መደገፊያ ሙሉ ለሙሉ መታጠፍና ወደፊት መሳብ የሚችል በመሆኑ፣ ከኋላ ለተቀመጡ ተሳፋሪዎች ሰፋ ያለ ቦታ እንዲያገኙ ያስችላል።፡ ለኋላ ተሳፋሪዎች ምቶች የሚሰጡ አማራጭ የእጅ መደገፊያም የተገጠመለት ነው።

ቤስቲዩን ኢ05 ናት 120 ኪሎዋት ኤሌክትሪክ ሞተር የተገጠመለት በመሆኑ፣ ጉዞን አመቺ ያደርጋል። የመኪናው የውስጥ ክፍል ሰፊ በመሆኑ እስከ አምስት ተሳፋሪዎችን አዝናንቶ ይይዛል። አምስት በሮች ያሉት መሆኑም፣ምቾች የሚሰጥ ነው። መኪናው ዘመናዊ የደህንነት ባህሪያት ማለትም AEB+FCW (Active Emergency Breaking width forward collision warning)፣  LED የላይ መብራቶች፣  through + type የፊት መብራቶች ያሉት በመሆኑም፣ በማንኛውም አይነት ሁኔታ እይታን በመጨመር ደህንነትን ለማስጠበቅ ያስችላል።

የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ በፋው የቤስቲዩን ኢ05 ናት (BESTUNE E05) የኤሌክትሪክ መኪና ይቀላቀሉ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ በፋው የቤስቲዩን ኢ05 ናት (BESTUNE E05) የኤሌክትሪክ መኪና ይቀላቀሉ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ቤስቲዩን ዲዛይን ሲደረግ ለደህንነት ቅድሚያ ተሰጥቷል 

መኪናው 3H ከፍተኛ ጥንካሬ ያለው ቦዲ፣ ከፍተኛ ጥንካሬ ያለውና 67 በመቶ የብረት ጥንካሬ በሚመዝን፣ የቴርሞፎርሚንግ ብረት መጠኑ ከ16 በመቶ በላይ በሆነ ቁሳቁስ የተሰራ ነው። ከፊት መቀመጫው ፊት ለፊት ሁለት ኤርባግ (የአደጋ መከላከያ) የተገጠመለት ሲሆን፣ ለኋላ መቀመጫው ህፃናት ከፍተው እንዳይወጡ የሚያስችል (Child Lock) እና ISOFIX ተገጥሞለታል። ሚዛናዊነቱን ለመጠበቅና የመቆጣጠር አቅሙን ለማጠናከርም የ BOSCH9.3 ጀነሬሽን ኤሌክትሪክ ፕሮግራምም (ESP) ተጭኖለታል።

በኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ የአውቶሞቲቭ ቢዝነስ ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር አያሌው ይማም እንደሚሉትም፣ መኪናው የዘመናዊ ቴክኖሎጂ መገለጫ የሆነ የመቆጣጠሪያ ስርአት አለው።

መኪናው ተሳፋሪዎች በቀላሉ እንዲወጡና እንዲገቡ የሚያስችል በኤሌክትሪክ የሚሰራ ተንሸራታች በር አለው። ከዚህ በተጨማሪ በሩ መከፈቱን ወይም ተሳፋሪ እየወረዱ መሆኑን ለእግረኞች የሚጠቁምና ጐንና ጐን ያሉትን ነገሮች የሚያሳየይ ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ፣ TPMA (የመኪና ጐማ ደህንነት መቆጣጠሪያ ስርአት) እና ጂፒኤስ (አቅጣጫ መጠቆሚያ) አለው። ተሳፋሪዎች ከኋላ መቀመጫ ሲወጡ ብቻ ምልክት የሚያሳይ የቁጥጥር ቴክኖሎጂ የተገጠመለት መሆኑ፣ የፋው ግሩፕ በቅርቡ በሰራው ቤስቲዩን  ኢ05 መኪና ላይ ብቻ የሚገኙ የተለዩ ባህሪያት ናቸው።

እንደ ኤሌክትሪክ መኪና፣ መኪናው የተሰራው ፋው የኤሌክትሪክ ፕላትፎርም በሆነው FME መሆኑ ቀላልና ብቁ እንዲሆን አስችሎታል።

5.5 kwh አቅም ያለው ባትሪ፣ 100kw የሞተር ሃይል፣ 260 nm የመጠምዘዝ አቅም የNEDC ማይሎች 419km፣ በቤት ውስጥና ውጪ ባትሪ ቻርጅ ለማድረግ የሚያስችል የቻርጅ አማራጭ፣ በ30 ደቂቃ በፍጥነት ቻርጅ ለማድረግ የሚያስችል አዳፕተር ያለው መሆኑ የቤስቲዩን መኪና ባትሪን በቻይና ተመራጭና ቁጥር አንድ እንደሚያደርገው በፋው የኢትዮጵያና የሌሎች አፍሪካ አገሮች ማናጀር ቺን ዢንግ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ በፋው የቤስቲዩን ኢ05 ናት (BESTUNE E05) የኤሌክትሪክ መኪና ይቀላቀሉ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ በፋው የቤስቲዩን ኢ05 ናት (BESTUNE E05) የኤሌክትሪክ መኪና ይቀላቀሉ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

በአይን የሚታዩ እንደ የማስነሻ በተን (start button)፣ መልቲፋንክሽናል ስቲሪንግ ዊል፣ ፓወር ዊንደስ፣ ሪር ቪው ሚረር ፓወር ሲዊች እና አማራጭ 10 ኢንች ተች ኮንትሮል LCD ስከሪን  የተገጠመለት መሆኑ፣ ምቾትን የሚሰጥና መኪናውን የመቆጣጠር አቅምን የሚያጠናክር ነው።

ቤስቲዩን ኢ05 ናት (BESTUNE E05) ተከታዮቹ ስፔሲፊኬሽኖች አሉት፡-

ርዝመት – 4450 mm

ስፋት – 1840 mm

ቁመት – 1680 mm

የጐማ ስፋት -2850 mm

ግራውነድ ክሊራንሰ – 167 mm

የመሸከም አቅም (crub weight) – 1650 /1700 kg

የቤስቲዩን መኪና ተፈላጊነት ከፍተኛ ነው። መኪናው ለህዝብ ይፋ ከመሆኑ አስቀድሞ ከተመረቱ 20 መኪናዎች ውስጥ አምስቱ ተሸጠዋል። የቀሩትም ገዢዎች እየተጠባበቁ ነው።

ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ የተገልጋዩን ፍላጐት ለማርካት ከሽያጭ በኃላ የመለዋወጫ እቃዎች ሽያጭ፣ ሰርቪስ፣ ጥገና እና እድሳትን ጨምሮ የተሟላ አገልግሎት በዘመናዊ ወርክሾፑ የሚሰጥ መሆኑን ያረጋግጣል።

ኢኳቶሪያል በዝነስ ግሩፕ ለመኪናው የሶስት ዓመታት ወይም 100,000 ኪሎ ሜትር ዋስትናም  ይሰጣል።

መኪናው ይፋ ሲሆን የተገኙት  ቺን ዢንግ፣  ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ አገልግሎቱን ለመስጠትና ለመደገፍ አቅም እንዳለው ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

ጠንካራ መለያ (ብራንድ) የመፍጠርንና ለተገልጋዮች ከሽያጭ በኋላ ተአማኒነት ያለው አገልግሎት መስጠት አስፈላጊ እንደሆነም አክለዋል።

™ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ በሚያቀርባቸው መኪናዎች ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመቅረፍና በቂ የመለዋወጫ እቃዎችን ለማቅረብ እንዲችል ደንበኞቹን ማናገር አለበት∫ ሲሉም ተናግረዋል።

ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ በአውቶሞቲቭ ዘርፍ፣ በሃይል ዘርፍ፣ በግንባታና በፋርማሲ ዘርፎች በመሰማራት ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አበርክቶ እያደረገ ይገኛል።

የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ በፋው የቤስቲዩን ኢ05 ናት (BESTUNE E05) የኤሌክትሪክ መኪና ይቀላቀሉ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ በፋው የቤስቲዩን ኢ05 ናት (BESTUNE E05) የኤሌክትሪክ መኪና ይቀላቀሉ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ከ30 ዓመታት በላይ መኪና በማከፋፈል ስራ ልምድ ያካበተው ድርጅቱ፣ ISO 9001:2008 እና ISO 9001:2015 ሰርተፍኬቶች፣ ከፋው ግሩፕ ደግሞ የዓመቱ የአከፋፋይ እውቅናና ምርጥ የአገልግሎት ሰጪ ሽልማቶችን ጨምሮ የተለያዩ ሽልማቶችን አግኝቷል።

የቤስቲዩን ኢ05 ናት የኤሌክትሪክ መኪና፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ ቅንጡ ባህሪያትና ዘመናዊ የደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂዎችን መላበሱ፣ በዘመናዊ አውቶሞቲቨ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማርሽ ቀያሪ ያደርገዋል። ልዩ ዲዛይን፣ ማራኪ የውስጥ ክፍል፣ ጠንካራ የኤሌክትሪክ ሞተር ያለው መሆኑ የተለየና አስደሳች የማሽከርከር ልምድን የሚያላብስ ያደርገዋል። በመሆኑም ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ከፋው ግሩፕ ጋር በመሆን የወደፊቱ መጓጓዣ የሆነውን ቤስቲዩን E05 ናት መኪናን እንዲገዙ ይጋብዝዎታል።

የኤሌክትሪክመኪናአብዮትመገለጫየሆነውን BESTUNE E05 መኪናለማሽከርከርየቀረበልዎእድልአያምልጥዎ! º. ለዚህምደብረዘይትመንገድ፣አቃቂ፣አዲስአበባየሚገኘውንየኢኳቶሪያልቢዝነስግሩፕየምርትማሳያስፍራይጐብኙ።የወደፊቱትውልድትራንስፖርትንይቀላቀሉ!!

የቅርብ ጊዜ መጣጥፎች

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ ጭማሪዎች የሚደረጉባቸው የተለያዩ አጋጣሚዎችና ሰበቦች...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት ብትችል፣ ከበርካታ ታዳጊ አገሮች የተሻለ...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር የሥልጣን መንበር...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣ እንደነገሩም ሆነ ለአንደበት ወግ ያህል...

ተመሳሳይ

ወንድማማቾቹን ለከፍተኛ ጉዳት የዳረገው ብሔር ተኮር ግጭት

ኢትዮጵያን በርካቶች የብዙኃን እናት፣ የብዙኃን አገር፣ ሲሉ ይጠሯታል፡፡ ለዚህም የተለያዩ ማንነቶች፣ ባህሎችና ሃይማኖቶች መኖሪያ...

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም በቶነር አሴምብሊንግ ስራ የተሰማራ ድርጅት...

ኦርቶፔዲክስ

በጡንቻ መገጣጠሚያ እና የአጥንት ህመሞች ላይ የላቀ ጥበብ፡- የአጥንት ጉዳትን ችግር ከመመርመርም ያለፈ የአጥንትና መገጣጠሚያ...