Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበዓመት ውስጥ አዲስ በኤችአይቪ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከስምንት ሺሕ መላቁን ጤና ሚኒስቴር...

በዓመት ውስጥ አዲስ በኤችአይቪ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከስምንት ሺሕ መላቁን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

ቀን:

55 ሚሊዮን በላይ ኮንዶሞችን እያሠራጨሁ ነው ብሏል

በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2030 ኤችአይቪ ኤድስ የማኅበረሰብ የጤና ችግር ወደ ማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ በተከናወኑ ተግባራት ውጤቶች ቢመዘገቡም፣ እ.ኤ.አ በ2022 እና በ2023 በተሠራው አገራዊ የኤችአይቪ ሥርጭት ግምታዊ ዳሰሳ፣ 8,257 ሰዎች አዲስ በኤችአይቪ እንደተያዙ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የካቲት 5 ቀን የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የኮንዶም ቀን አስመልክቶ በተሰጠ መግለጫ የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና ጤና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ተገኔ ረጋሳ (ዶ/ር) ዳሰሳውን ጠቅሰው እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ወቅት ከ610,350 በላይ ሰዎች ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ 11,322 የሚሆኑ ሰዎችም በኤድስ ምክንያት ሞተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እንደ ተገኔ (ዶ/ር)፣ አዲስ በኤችአይቪ የሚያዙ ስዎች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል፡፡ ለዚህም አሁናዊ የኤችአይቪ ሥርጭት ምጣኔም ከአንድ በመቶ በታች 0.91 በመቶ መሆኑ ማሳያ ነው፡፡

ለኤችአይቪ ተጋላጭ ከሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሴተኛ አዳሪዎች የሥርጭት ምጣኔ ከአጠቃላይ የማኅበረሰብ ሥርጭት ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው፡፡ ወጣቶች፣ ተማሪዎች፣ የሆቴል ቤቶች አስተናጋጆችና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ሠራተኞች እንዲሁም የረዥም መንገድ አሽከርካሪዎች ለኤችአይቪ ያላቸው ተጋላጭነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንም ተናግረዋል፡፡

ለሥርጭቱ አለመገታት የባህርይ ለውጥ አለመምጣት ዋና ተግዳሮት በመሆኑ በተከታታይ የባህርይ ለውጥ ላይ መሠራት ያስፈልጋል ያሉት ተገኔ (ዶ/ር)፣ የኮንዶም አጠቃቀምን በተመለከተ የግንዛቤው ሥራ መጠናከር እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

ተገኔ (ዶ/ር)፣ መንግሥት የበሽታውን ሥርጭት አስቀድሞ ለመከላከል በአገር አቀፍ ደረጃ ከ55 ሚሊዮን በላይ ኮንዶሞችን እያሠራጨ መሆኑን ቢጠቁሙም፣ ዛሬም ኮንዶም በስፋት ካለመገኘቱም በላይ ዋጋው ውድ ሆኗል፡፡

በመግለጫው ላይ የተገኙት የኤኤችኤፍ የኢትዮጵያ ካንትሪ ፕሮግራም ዳይሬክተር መንግሥቱ ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)፣ የኤችአይቪ ሥርጭት ከፍተኛ በሆኑባቸው በሴተኛ ተዳዳሪዎች፣ በወጣቶች፣ በተማሪዎች፣ በሆቴል ቤቶችና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከሁለት ሚሊዮን በላይ ኮንዶም በነፃ ማሠራጨታቸውን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ኮንዶም ለማሠራጨት በግዥ ሒደት ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በአዲስ አበባ የኮንዶም ሥርጭትን አስመልክቶ ሪፖርተር በኅዳር 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የኤችአይቪ ኤድስ ዘርፍ ምላሽ ማስተባባሪያ ጽሕፈት ቤት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ከሆኑት ሲስተር ፈለቀች አንዳርጌ ጋር በነበረው ቆይታ፣ ኮንዶም የኤችአይቪ ሥርጭትን ለመቀነስ ከሚተገበሩት የመከላከያ መንገዶች ዋነኛና ትልቁን ድርሻ የሚይዝ ቢሆንም፣ እንደ ልብ ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን ዘግቦ ነበር፡፡

ኮንዶም ቀድሞ ከተለያዩ አካላት ድጋፍ ይደረግበት ስለነበር በነፃ በቀላሉ ማግኘት ይቻልም ነበር፡፡ አገልግሎቱን ማግኘት የሚፈልግ በጤና ጣቢያዎችና ለሴተኛ አዳሪዎች በተዘጋጁ ማረፊያ ቦታዎች ማግኘት ቢችልም፣ በነፃ መምጣቱ ከቆመ በኋላ የኮንዶም እጥረቱ ይታያል፡፡ ያለውም በውድ ዋጋ እእይተሸጠ ነው፡፡

ኮንዶም ለገበያ እየቀረበ የሚገኘው፣ ለፋርማሲዎችና ለግል የጤና ተቋማት ሦስቱ ፍሬ በ16 ብር ቢሆንም፣ ለተጠቃሚው ከ50 ብር በላይ ሆኗል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች ጭራሹንም ተደራሽ አይደለም፡፡ በዚህ ዋጋ ገዝቶ የመጠቀም አቅሙም ዝቅተኛ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በመንግሥትና በግል ተቋማት የተሠሩ ሥራዎችን ከመቅጽበት ወደኋላ ሊመለስ ይችላል፡፡

በኢትዮጵያ ከአንድ ሺሕ በላይ ወረዳዎች ያሉ ሲሆን፣ ከእነዚህ 222ቱ ከፍተኛ ተጋላጭ ተብለው ተለይተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከሚገኙ 121 ወረዳዎች ውስጥ 48ቱ አንደኛ ደረጃ፣ 51 ሁለተኛ ደረጃ፣ 20ዎቹ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ መጠጥ ቤቶችና መዝናኛ ቦታዎች በብዛት የሚገኝባቸው ሥፍራዎች ደግሞ ለሥርጭቱ ተጋላጭ መሆናቸውንም ሪፖርተር ዘግቦ ነበር፡፡

ጤና ሚኒስቴር 55 ሚሊዮን ኮንዶም እያሠራጨሁ ነው ቢልም፣ በአዲስ አበባ በወፍ በረር ባደረግነው ቅኝት የኮንዶም እጥረት መኖሩን፣ እጥረት ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ ቦታዎች አለመኖሩን ለመታዘብ ችለናል፡፡

ሕይወት ትረስት ኮንዶም ፋርማሲ ውስጥ በ50 ብር ሲሸጥ፣ የሆቴል ቤቶችና መጠጥ ቤቶች የጥበቃ ሠራተኞችም በተመሳሳይ ዋጋ እንደሚሸጡ ታዝበናል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...