Saturday, April 20, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

 • ምን ጉድ ነው የማየው?
 • ምን ገጠመሽ?
 • የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው?
 • ምን አሠራጩ?
 • አልሰማህም?
 • አልሰማሁም፣ ምንድነው?
 • ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ።
 • እ… እሱን ነው እንዴ?
 • አዎ። የምታውቀው ነገር አለ?
 • አዎ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ሲመረቅ የተላለፈ መልዕክት ነው።
 • እና የእውነት ነው?
 • የእውነት ነው የምትይው ምኑን ነው?
 • ራሳቸው አፄ ምኒልክ ናቸው?
 • እሳቸውማ እንዴት ያስተላልፋሉ፣ ሞተው የለ እንዴ?
 • ታዲያ መልዕክት አስተላለፉ የተባለው እንዴት ነው?
 • ሆሎግራም ቴክኖሎጂ የተቀናበረ ምስልና መልዕክት ነው።
 • ሆሎግራም ደግሞ ምንድነው?
 • በአጭሩ የአኔ ምኒልክን የፎቶ ምስል በመውሰድና ድምጻቸውን በማስመስል በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ተቀናብሮ የቀረበ መልዕክት ነው።
 • እንደዚያ ነው?
 • አዎ። መልዕክቱ ትኩረት እንዲያገኝ ታስቦ በቴክኖሎጂ ተቀናብሮ የቀረበ ነው።
 • መጀመሪያውኑ ለምን እንደዚያ ብለው አያስረዱም? ለምን አፄ ምኒልክ መልዕክት አስተላለፉ ብለው ግራ ያጋቡናል?
 • ግራ ተጋብተሽ ነበር?
 • እንዴት አልጋባም?
 • መቼም እሳቸው ሊሆኑ ይችላሉ ብለሽ ጠርጥረሽ ሊሆን አይችልም?
 • ነው እንጂ። በዚህ ዘመን ምን ይታወቃል?
 • እንዴት?
 • መጥተው ይሆናል ብዬ ነዋ?
 • እንዴት ሊመጡ ይችላሉ?
 • ሰምተው ነዋ።
 • ምን ሰምተው?
 • ኢትዮጵያ ውስጥ እየተገነባ ነው የተባለውን።
 • ኢትዮጵያ ውስጥ ምን እየተገነባ ነው ተባለ?
 • ገነት!

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ስልካቸው ጠራ። ደዋዩ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ኃሊፊ እንደሆኑ ሲነገራቸው የስልኩን መነጋገሪያ ተቀበሉ]

 • ሃሎ!
 • እንዴት አሉ ክቡር ሚኒስትር።
 • ደህና ነኝ።
 • ክቡር ሚኒስትር ባስገነቡት የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም በእጅጉ መደነቄን ልንገርዎ ብዬ ነው። በእውነቱ ጥሩ ሥራ ነው።
 • አመሰግናለሁ። ጥሩ ጅምር ነው።
 • ምኑ ክቡር ሚኒስትር?
 • እንዲህ የሚደነቀውን ማድነቅ ጥሩ ጅማሮ ነው ማለቴ ነው። ግን…
 • ግን ምን ክቡር ሚኒስትር?
 • እንዲሁ ስገምት የደወልከው ለዚህ ጉዳይ አልመሰለኝም። ልክ ነኝ?
 • በእርግጥ የደወልኩት ለሌላ ጉዳይ ነው።
 • ምነው? ሰሞኑን ተገናኝተን ከገመገምን በኋላ የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ?
 • የለም።
 • እና ምን ገጠመህ?
 • ሰሞኑን ባደረግነው ውይይት ስምምነት የደረሰንበትን ጉዳይ በተመለከተ ፍቃድዎትን ለመጠየቅ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • የትኛው ጉዳይ?
 • ዘነጉት እንዴ? የተስማማነው እኮ አንድ ጉዳይ ላይ ነበር።
 • ምን ነበር?
 • የፓርቲያችን ሕጋዊ ሰውነት እንዲመለስ ነው የተስማማነው።
 • ኦ… ዘንግቼው ነው። ልክ ነህ።
 • እና በዚያ ጉዳይ ላይ ፍቃድዎትን ለመጠየቅ ነበር።
 • ምን ነበር?
 • ሰሞኑን ባደረግነው ውይይት ሕጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስ ስንግባባ እርስዎ ደግሞ በፍጥነት እንዲተገበር አቅጣጫ ሰጥተው ነበር።
 • አዎ፣ ልክ ነው።
 • ያስታውሱ እንደሆነ ሕጋዊ ሰውነታችን ውድቅ የተደረገው ግንቦት 7 ቀን ነበር።
 • ግንቦት 7 መሆኑ የተለየ ትርጉም አለው?
 • አዎ። ለእኛ መጥፎ ትርጉም አለው።
 • እና አሁን ምን እንዲደረግ ነው የፈለግከው?
 • ትዕዛዝ እንዲሰጡልኝ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • የምን ትዕዛዝ?
 • ሕጋዊ ሰውነታችን በታሪካዊው ቀናችን እንዲመለስ።
 • መቼ ነው።
 • ለካቲት 11።

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...

እጥረትና ውጥረት!

ጉዞ ከስድስት ኪሎ ወደ ቃሊቲ፡፡ ‹‹ይገርማል ቀኑ እንዴት ይሄዳል?››...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪው ቅሬታ የቀረበባቸው አንዳንድ ጉዳዮችን ክቡር ሚኒስትሩ ተመልክተው ምላሽና ውሳኔ እንዲሰጡባቸው ለማድረግ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር እየተወያዩ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር ተቋማችን በሚሰጣቸው አንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ጥያቄ እየተነሳ በመሆኑ ነው ዛሬ ከእርስዎ ጋር ለመወያየት የፈለግኩት። የምን ጥያቄ? ማነው ጥያቄውን ያቀረበው? ጥያቄውን ያቀረቡት የተቋማችን ተገልጋዮች ናቸው። እሺ፣...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ? አላስታውስም። ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር ከውጭ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ምርቶች እያወሩ ነው]

እኔ እምልህ ...ኤል ሲ እንዳይከፈት ተከልክሏል ሲባል አልነበረም እንዴ? ኤል ሲ ደግሞ ምንድነው? ሌተር ኦፍ ክሬዲት ነዋ!? አልገባኝም? አስመጪዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ዕቃ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች አይደል የሚያገኙት? አዎ። ኤል...