Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምበቻይና አዲስ ዓመት የሚጠናከረው የቻይናና ሩሲያ ስትራቴጂክ ትብብር 

በቻይና አዲስ ዓመት የሚጠናከረው የቻይናና ሩሲያ ስትራቴጂክ ትብብር 

ቀን:

አዲስ የጨረቃ ዓመቷን ቅዳሜ የካቲት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. የተቀበለችው ቻይና፣ ከሩሲያ ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ ትብብር ይበልጥ አጠናክራ እንደምትቀጥል በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል አስታውቃለች፡፡

ከምዕራባውያኑ ጋር ልዩነታቸው እየሠፋ መምጣቱን ተከትሎ የሩሲያና የቻይና ግንኙነት የተጠናረ ሲሆን፣ ይህንኑ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርም የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢጂንፒንግ፣ ከሩሲያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በአዲሱ የቻይና ዓመት ይበልጥ እንደሚጠናከር ገልጸዋል፡፡

ቻይና አዲስ ዓመት ከመቀበሏ ከሁለት ቀናት አስቀድሞ ለሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስልክ የደወሉት ዢጂንፒንግ፣ ሁለቱ አገሮች ስትራቴጂክ ትብብራቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳውቀው፣ ፑቲን ይህንኑ ይቀበሉ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የሁለቱን አገሮች ብሔራዊ ደኅንነት፣ ፍላጎታቸውንና ደኅንነታቸውን ለመጠበቅ አገሮች ግንኙነታቸውን ማጠናከር እንደሚባቸውም ዢጂንፒንግ መግለጻቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡

በውስጥ ጉዳዮቻቸው ላይ የማንንም ጣልቃ ገብነት እንዳይቀበሉም አጽንኦት ሰጥተውታል፡፡ ከምዕራባውያን ጋር በተለይ በሌሎች አገሮች ጉዳይ ጣልቃ ገብነትን በተመለከተ የማይስማሙት ሩሲያና ቻይና፣ የምዕራባውያኑን እንቅስቃሴን በተናጠል ሆነው የሚመክቱት ሆኖ አላገኙትም፡፡

የቻይና አዲስ ዓመት ከመግባቱ አስቀድሞ በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረገው የስልክ ውይይትም፣ አገሮቹ ቀድሞ የነበራቸውን የሞቀ ግንኙነት የሚያጠናክር ነው፡፡

በጥቅምት 2016 ዓ.ም. በቻይና በተካሄደው የቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም፣ መሪዎቹ የጎንዮሽ ውይይት ባደረጉበት ወቅት፣ ፑቲን ለቻይናና ለሩሲያ መጠናከርና መቀራረብ ዋናው ምክንያት ‹‹የጋራ ሥጋት›› መኖሩ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ቻይናና ሩሲያ በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ያጠናከሩት ግንኙነት በምዕራባውያኑ ዘንድ በዓይነ ቁራኛ ይታያል፡፡ በተለይ ከዓመት በላይ ባስቆረው የዩክሬን የሩሲያ ጦርነት፣ ቻይና ለሩሲያ ትረዳለች የሚል ሥጋትም አለ፡፡

ቻይና በሩሲያና በዩክሬን መካከል ባለው ጦርነት ገለልተኛ መሆኗን በተደጋጋሚ በነበሩ ጦርነቱን የማስቆምና ፖለቲካዊ መፍትሔ የማፈላለግ መድረክ ላይ አሳይታች፡፡ ሆኖም ምዕራባውያኑ ‹‹ሩሲያ ዩክሬንን ወራለች›› ብለው ሩሲያን ሲያወግዙ ቻይና ይሁንታዋን አልሰጠችም፡፡

ምዕራባውያኑ ከጥር 2015 እስከ 2016 ዓ.ም. ባለው ጊዜ በሩሲያ ላይ በአገርም፣ በተቋምም ደረጃ ከ10 ሺሕ በላይ በሚሆኑ ሩሲያውያን እንዲሁም ከሦስት ሺሕ በላይ ተቋማት ላይ ገደብ ጥለዋል፡፡

የገደቡ መጣል ዋና ዓላማ የሩሲያን ኢኮኖሚ ለማንኮታኮት ቢሆንም፣ ቻይና ለሩሲያ የወሳኝ ጊዜ የኢኮኖሚ አጋር ሆናታለች፡፡

ሲኤንኤን በታኅሣሥ 2016 ዓ.ም. ባወጣው ዘገባ፣ ቻይናና ሩሲያ እ.ኤ.አ. በ2023 በመጀመሪያዎቹ 11 ወራት በተለያዩ ዘርፎች በነበራቸው ትብብር፣ በአገሮች መካከል የነበረው የንግድ ልውውጥ 200 ቢሊዮን ዶላር መሻገሩን ገልጿል፡፡

የዓለም ሁለተኛ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ቻይና፣ አሜሪካና አጋሮቿ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ መጣላቸውን ተከትሎ፣ የሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ የሕይወት መስመር የቀጠለችውና ይህንን የምታደርገው፣ ሁለቱም አገሮች መሠረት ያደረጉትን የሁለትዮሽ ፖለቲካዊ እምነት ተመርኩዘው ነው፡፡

‹‹የወደፊቱ ግንኙነት መጠናከርን እያየን በበርካታ ፈተናዎችና ችግሮች ወቅት አብረን ቆመናል፤›› ያሉት ዢጂንፒንግ፣ ግንኙነቱ ለሁለቱ አገሮች አዳዲስ የልማት ዕድሎች እያስገኘ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የሁለቱን መሪዎች የስልክ ውይይት አስመልክቶ ከክርምሊን ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፣ መሪዎቹ በመካከለኛው ምሥራቅና በዩክሬን ያለውን ሁኔታ ጨምሮ በተለያዩ ቀጣናዎች ዙሪያ ዝርዝር ውይይት አድርገዋል፡፡

እንደ ሩሲያ መግለጫ፣ ሩሲያና ቻይና መካከለኛው ምሥራቅ ላለው ችግር የፍልስጤም ጉዳይን በፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ዓለም አቀፍ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት መፍታት አለበት ብለው ያምናሉ፡፡

ቤጂንግ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ባወጣችው መግለጫም፣ በእስራኤልና በጋዛ ሐማስ መካከል ባለው ግጭት፣ በዓለም አቀፍና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረውበታል ብላለች፡፡

ቤጂንግ፣ እስራኤል ከሐማስ በኩል ለደረሰባት ድንገተኛ ጥቃት እያደረገች ያለውን ወታደራዊ ምላሽ በመኮነን፣ ፍልስምና ለእስራኤል የጋራ መፍትሔ እንዲያመነጩ ትፈልጋለች፡፡ የፍልስጤም ነፃ ግዛት መመሥረት ግጭቱን ለመፍታት ያስችላል ስትልም ታምናለች፡፡

ሩሲያና ቻይና በዓለም አቀፉ ጉዳዮች ዙሪያ የራሳቸውን የትብብር ማዕቀፍ እያጠናከሩ ይገኛሉ፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚኖሩ አጀንዳዎች ጎን ለጎን ከመቆም ባለፈም፣ የተለየ ዓለም አቀፍ ቡድን እየፈጠሩ ነው፡፡ የብሪክስና የሻንጋይ ኮኦፕሬሽን ኦርጋናይዜሽንም የዚሁ ማሳያ ናቸው፡፡

ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ብሎም የሩሲያ ቻይና ግንኙነት ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን ለማረጋጋት ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተውታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...