Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየባቢሌ ዝሆኖች ከመጠለያ ወጥተው የሰው ሕይወት እያጠፉ መሆናቸው ተነገረ

የባቢሌ ዝሆኖች ከመጠለያ ወጥተው የሰው ሕይወት እያጠፉ መሆናቸው ተነገረ

ቀን:

  • አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አራት ሰዎች መሞተቸው ተገልጿል

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል የሚገኘው የባቢሊ ዝሆኖች መጠለያ ለኢንቨስትመንት በመሰጠቱ፣ ዝሆኖቹ ከመጠለያ በመውጣት የሰው ሕይወት እያጠፉ መሆናቸውን፣ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆኑ ጥቁር ዝሆኖችን ጨምሮ 31 አጥቢ እንስሳትና ከ220 በላይ የአዕዋፋት ዝርዎች እንዳሉት የሚነገርለት የባቢሌ መጠለያ፣ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን መኮንን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ለኢንቨስትመንት በመስጠቱ ምክንያት በርካታ ዝሆኖች ከመጠለያው በመውጣት በአካባቢው በሠፈሩ ሰዎች ላይ አደጋ እያስከተሉ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ በአገሪቱ ካሉ 27 ብሔራዊ ፓርኮች ውስጥ አንዱ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ መጠለያውም በአሁኑ ወቅት በሰው ሠራሽ ችግር ምክንያት ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደሚገኝ አክለው ገልጸዋል፡፡

በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ በተደረገው ሕገወጥ ሠፈራ ዝሆኖቹ የሚኖሩበትና የሚራቡበት ቦታ በእርሻ፣ በከሰል ምርት፣ በመንገድና በመኖሪያ ቤት ግንባታ ደኑ በመመናመኑ ዝሆኖቹ ከመጠለያ እየወጡ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ የተጋረጠበትን አደጋ ለመቅረፍ ባለሥልጣኑ ከኦሮሚያ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣንና ከኢንቨስትመንት ቢሮ ጋር በመነጋገር፣ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ሰፊ እንቅስቃሴ እያካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሠረት በአካባቢው ያላግባብ ቦታ የተሰጠው ግለሰብ ውሉ እንዲቋረጥና ከመጠለያው እንዲወጣ ውሳኔ እየጠበቁ እንደሆነ ገልጸው፣ በሌላ በኩል ደግሞ በአካባቢው የነበሩ ደኖችን መንጥረው ቦታውን ለመጠቀም በእንቅስቃሴ ላይ ያሉ ባለሀብቶች በሕግ እንዲጠየቁ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ አብዛኛው ለኢንቨስትመንት በመዋሉ ዝሆኖች እየወጡ እንደሆነ፣ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ የአራት ሰዎችን ሕይወት መቅጠፋቸውን አክለዋል፡፡

ባለሥልጣኑ ከዚህ በፊት የነበሩበትን ክፍተቶች በመሙላት ከዞን አስተዳደር ጋር በመነጋገር፣ በሰዎችም ሆኑ በዝሆኖች ላይ የሚደርስ ችግርን ለመቅረፍ እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ‹‹አፕል ሥሪ›› የተባለ ኩባንያ የዝሆኖች መጠለያ የሆነውን ቦታ ለኢንቨስትመንት መውሰዱን፣ ኩባንያውንም ከአካባቢው ለማስወጣት ክርክር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት የነበሩ ኢንቨስተሮችም አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጉን ያስታወሱት አቶ ሰለሞን፣ ‹‹አፕል ሥሪ›› የተሰኘው ኩባንያ 200 ሔክታር መሬት የሚሆን መሬት ከመጠለያው ለኢንቨስትመንት መውሰዱን አስረድተዋል፡፡

በመጠለያው ውስጥ የሚገኙ ዝሆኖች በትክክለኛ አሠራር በመጠለያ እንዲቆዩ ከኦሮሚያና ከሶማሌ ክልሎች አመራሮች ጋር ውይይት ይደረጋል ብለዋል፡፡

በዚህ መሠረት በዚህ ወር በቱሪዝም ሚኒስቴር አስተባባሪነት ውይይቱ የሚደረግ መሆኑን ገልጸው፣ ውይይቱም የሚደረግበት ዋና ዓላማ የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሚረዳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡  

በሶማሌ ክልል ዝሆኖችን በመግደል በሕገወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ መኖራቸውን ጠቅሰው፣ ከስድስት ዓመታት በፊት በተደረገ ጥናት መሠረት ከ400 እስከ 500 ዝሆኖች በመጠለያው ይኖሩ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ከዚህ በፊት የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ያወጣው ጥናት እንደሚያሳየው፣ በመጠለያው ጣቢያ ውስጥ ለታየው ሕገወጥ ሠፈራ ዋነኛው ምክንያት የውኃ ፍላጎት ነው፡፡ ዝሆኖቹም ኑሯቸውን ያደረጉት ውኃና ዛፍ ባለበት አካባቢ መሆኑን አሥፍሯል፡፡ በዚህም ምክንያት በሰዎችና በዝሆኖች መካከል ተደጋጋሚ ግጭት እንደሚነሳና በሁለቱም ላይ ጉዳትና ሞት ማስከተሉን ጥናቱ አክሏል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞንና በሶማሌ ክልል የፋይዳና የረር ዞኖችን የሚያዋስነው የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ 6,980 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት እንዳለው፣ ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ክፍል በእርሻ መሸፈኑን የባለሥልጣኑ መረጃ ያሳያል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...