Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊጉራማይሌው የመዲናዪቱ አካባቢ ጥበቃ

ጉራማይሌው የመዲናዪቱ አካባቢ ጥበቃ

ቀን:

ብዙዎች አዲስ አበባ ከተማን የአፍሪካ መዲና የዲፕሎማቶች መሰባሰቢያ ሲሉ ይጠሯታል፡፡ የአፍሪካ መሪዎችም የኅብረቱ መቀመጫ በመሆኗ አዘውትረው ይመላለሳሉ፡፡ ከተማዋ መሪዎቿን ለመቀበል ብቁ አይደለመችም መሠረተ ልማቷ አልተስፋፋም የሚሉትን ምክንያቶች በማቅረብ ከአፍሪካ ኅብረት መቀመጫነት ለማንሳት አንዳንድ የአፍሪካ አገሮች የተለያዩ ሙከራዎችን አድርገዋል፡፡

በአፍሪካ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ ከኅብረቱ መቀመጫነት እንድትርቅ በየመድረኩ የሚያነሱ እንደ ሴኔጋል፣ ጋና፣ ደቡብ አፍሪካና ሊቢያ የመሳሰሉ አገሮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ምክንያታቸው ደግሞ የውኃ፣ የመብራት፣ የመንገድ፣ የሆቴልና የመኖሪያ ቤት ችግር የመሳሰሉት መሠረተ ልማቶች አልተሟሉም የሚል እንደነበር ይጠቀሳል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ጥያቄዎቹም ለአዲስ አበባ መልካም አጋጣሚዎችን ይዘው የመጡ ይመስላሉ። ምክንያቱም ከነበረችበት ተክለ ቁመና  እንደ ማንቂያ ደወል ሳይሆን አልቀረም፡፡ ሌላው ቢቀር የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ሲቃረብ ጀምሮ ስብሰባው ተጠናቆ መሪዎች እስኪሄዱ ድረስ የሚሠሩ ሥራዎች ዓመቱን ሙሉ ከሚሠሩት አይተናነሱም፡፡ 

የኅብረቱ ስብሰባ ሲቃረብ መንገዶች ይፀዳሉ፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች ከያሉበት ተፈልገው ተጭነው ወደየመጡበት አካባቢ ይመለሳሉ፣ ሊስትሮዎችና በየመንገድ ዳሩ ተኮልኩለው የሚታዩ የእኔ ቢጤዎች ለጊዜው ገለል እንዲሉ ይደረጋል፡፡

የፖለቲካና የዲፕሎማሲ መዲና ብቻ ሳትሆን የአገሪቱ የባህልና ቱሪዝም መናኸሪያ፣ የየብሔረሰቦች የጋራ መኖሪያና መሰባሰቢያ የሆነችው አዲስ አበባ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ‹‹አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ አበባ እናደርጋለን›› በማለት የከተማ አስተዳደሩ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን የተለያዩ መመሪያና ደንቦችን በማውጣት የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ከተማዋን ከማስዋብ አንፃር መንግሥት ፕሮጀክት ቀርፆ የወንዝ ዳር ልማቶችንና የመዝናኛ ፓርኮችን የገነባ ሲሆን፣ በግለሰቦችና በግል ተቋማት ትልልቅ ሆቴሎችና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ሲገነቡ ይስተዋላል፡፡

በተለይ ደግሞ እንደ ዓለም አቀፍ ችግር ሆኖ የመጣውን የአየር ብክለት ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም ከቆሻሻ የፀዳች ከተማ ለማድረግ፣ የአዲስ አበባ ከተማ  የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሲሠራ መቆየቱን ሐሙስ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት አመላክቷል፡፡

በግማሽ ዓመቱ ሕግን ተላልፈው ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎችን ያመነጩ ተቋማት ላይ ማስጠንቀቂያ ከመስጠት እስከ ማሸግ፣  ከፍ ሲልም የንግድ ፈቃዳቸውን እስከ መሰረዝ የሚደርሱ ዕርምጃዎችን መውሰዱን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዲዳ ድሪባ ተናግረዋል።

በግማሽ ዓመቱ ከተማዋን ከብክለት ለመከላከል ከከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ፣ ከኢኖቬሽንና ልማት፣ ከግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን እንዲሁም ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮና ከሌሎች 27  አጋር አካላት ጋር በትብብር ለመሥራት ታቅዶ 20 ከሚሆኑት ጋር በጋራ እየተሠራ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በየደረጃው የወጡ ሕጎችንና ደንቦችን በመተላለፍ የአካባቢ ብክለት በሚያስከትሉ ፋብሪካዎች፣ አላስፈላጊ ድምፅን በማውጣት አካባቢን በሚረብሹ  የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ ሥርዓት የማስከበር ዕርምጃ በሚመለከታቸው አካላት መወሰዱንም አቶ ዲዳ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጁ ትልልቅ ሆቴሎችና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ለሌሎች አርዓያ መሆን ሲገባቸው የችግሩ ፈጣሪ እየሆኑ መምጣታቸው ተጠቁሟል፡፡ ባለሥልጣኑም በእነዚህ ተቋማት ላይ አጥፍታችኋል ሌሎች የግል ተቋማት እንደሚቀጡት ለመቅጣት ለማለት መቸገሩን ጠቁመዋል፡፡

በርካታ ሕሙማንን፣ ብዙ ተማሪዎችን የያዙ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ለብዙ ሰዎች የሥራ ዕድል ፈጥረዋል የተባሉ ሆቴሎችና ሌሎች የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገድ ላይ ትልቅ ችግር እንዳለባቸው አቶ ዲዳ ጠቁመዋል፡፡

ጉዳዩ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በላይ በመሆኑ የሚያጠፉትን ጥፋት በሚዲያ እንዲገለጥ መደረጉን ዋና ሥራ አስኪያጁ አብራርተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ሁኔታው በዚህ መፈታት ካልቻለ ጉዳዩን ወደ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት በመውሰድ አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

ከሌሎች መሥሪያ ቤቶች ጋር ተናቦ የመሥራት ትልቅ ክፍተት መኖሩን የጠቆሙት   ከአንድ የግል ንግድ ቤትም ሆነ ሆቴል የደንብ አስከባሪ፣ ፖሊስ፣ ንግድ ቢሮና ሌሎችም   በየፊናቸው በመመላለስ አገልግሎት ሰጭውን አካል እያስመረሩ  መሆኑን በማከል ነው።

ነገር ግን ተቀራርቦ በጋራ የመሥራት ልምዱ ቢኖር  የየተቋሙን  ዳታ በማሰባሰብ መሥራት ይቻላል   ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አዳዲስ ለሚከፈቱ እንደ ጭፈራ ቤትና አዋኪ ድምፅ ላላቸው ፋብሪካዎችም ሆነ ሌሎች የንግድ ዘርፎች ለሚሳተፉ አካላት የንግድ ፈቃድ ሲሰጥ አካባቢውን አለመለየቱትና ምን እየተሠራበት እንደሆነ ክትትል ያለማድረግ  በስፋት እንደሚስተዋሉ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል  ባለሥልጣኑ ባቀረበው ሪፖርት በመነሳት በመረጃ አያያዙ ላይ ትችቶችና አስተያየቶች ከባለድርሻ አካላት ተሰንዝረዋል፡፡

የቀረበው ሪፖርት በቁጥር ያልተደገፈና የሁሉንም ባለድርሻ አካላት እንቅስቃሴ ያልዳሰሰ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ለምሳሌ አዲስ አበባ ከተማ ከአየር ብክለት ጋር ተያይዞ ምን ያህል ጉዳት ደርሶበታል የሚለው በዳታ የተሠራ ሪፖርት ሊሆን እንደሚገባ ተመልክቷል። 

በመዲናዋ ያሉ የግልና የመንግሥት ተቋማት በአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚመዘኑበት ሚዛን የተለያየ እንደሆነ ከአንድ ተሳታፊ ተጠቁሟል፡፡ የመንግሥት ተቋማትን በፈገግታ መቀበል የግሎችን ደግሞ ኮስተር ብሎ ለመቅጣት የመቻኮል ሁኔታ ይስተዋላል ብለዋል፡፡

በእያንዳንዱ መሥሪያ ቤት የተሠሩ ሥራዎችና ያልተሠሩት በደንብ ተለይተው በሪፖርቱ መካተት እንደነበረበትና ያልተሠሩትን በመለየት ለቀጣይ ማሻሻያ እንዲደረግባቸው ለማስቻል እንደሚረዳ ጥቆማ ቀርቧል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ነው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋለልኝ ጥበቡ ናቸው፡፡

በመዲናዋ የአካባቢ ጥበቃን ሥራዎች ላይ የተግባራዊ አፈጻጸም ጉድለቶች መኖራቸውን የጠቆሙት አቶ ዋለልኝ፣ የችግሩ ዋና ምክንያትም የመረጃ ማሰባሰቡ ክፍተቶች ያሉበትና ተጨባጭ የሆኑ ማሳያዎች አለማስቀመጡ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...