Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለቴክኖሎጂ የጎንዮሽ ጉዳት የተጋለጡ ተማሪዎች

ለቴክኖሎጂ የጎንዮሽ ጉዳት የተጋለጡ ተማሪዎች

ቀን:

የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ በየዕለቱ አዳዲስ መረጃዎችን ከማቀበል ጀምሮ ጊዜንና ገንዘብን ለመቆጠብ እንዲሁም ድካምን ለመቀነስና ልዩ ልዩ ተግባራትን ለማናወን ፈጣን፣ ቀላልና ተመራጭ በመሆን በማገልገል ላይ ቢሆንም፣ የጎንዮሽ ጉዳት ማስከተሉ አልቀረም፡፡

ቴክኖሎጂው በርካታ ጥቅሞች እንዳሉት ሁሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ይዞ ስለመምጣቱ፣ ሆኖም ችግሮቹን ለመቀልበስ የሚሠሩ ሥራዎች አናሳ መሆናቸውና ግንዛቤም በአግባቡ አለመፈጠሩ ይነገራል፡፡

ለቴክኖሎጂ የጎንዮሽ ጉዳት የተጋለጡ ተማሪዎች | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
አቶ ሚካኤል አማረ

ችግሩም ቴክኖሎጂውን ያበለፀጉ አገሮችን ጭምር እየተፈታተነ ሲሆን፣ ባላደጉ አገሮች ውስጥ እያስከተለ ያለው የዓይን ሕመምና ሥነ ልቦናን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳቶችም ከፍተኛ ስለመሆናቸው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ኢትዮጵያም የዚሁ ችግር ሰለባ መሆኗ በስፋት እየታየ ነው፡፡ ኢንተርኔትን በመጠቀም በየዕለቱ በርካታ ወንጀሎች ሲፈጸሙ ይስተዋላል፡፡ የቤተሰብ መስተጋብር መቀነስ፣ የዕለት ከዕለት ግንኙነትን ከቴክኖሎጂ ጋር በማድረግ ማኅበራዊ ሕይወትን መናድ፣ ረዥም ጊዜ ለቴክኖሎጂ አመጣሽ ወጎች በመስጠት መደበኛ ትምህርትን ችላ ማለት፣ የራስን ባህል መዘንጋትና ሌሎችም የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸው፡፡

በኢንተርኔት አማካይነት ከሚፈጸሙ ወንጀሎች በተለይ በሕፃናትና በታዳጊዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ወሲባዊ ጥቃት እየተበራከተ መምጣት ደግሞ አሳሳቢው ችግር ስለመሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው፡፡

ፆታዊ ጥቃትን መሠረት ያደረጉ ወንጀሎች በብዛት እየተፈጸሙባቸው ካሉ በይነ  መረቦች መካከል ፌስቡክና ቴሌግራም የተባሉት ዋነኞቹ ስለመሆናቸውም ይነሳል፡፡

በእነዚህ በይነ መረቦች አማካይነት በተለይ አጠቃቀሙና ግንዛቤው የሌላቸው ሕፃናት ለወሲባዊ ጥቃት መጋለጣቸውን ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

ናሽናል ሴንተር ፎር ሚሲንግ ኤንድ ኤክስፕሎትድ ችልድረን የተባለ ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2017 በኢትዮጵያ ባደረገው ጥናት፣ ከዘጠኝ ሺሕ በላይ ሕፃናት በበይነ መረብ አማካይነት ፆታዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል ሲል ይፋ ማድረጉን ቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ በመረጃነት ይጠቀሳል፡፡

መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገውና ሕፃናት በበይነ መረብ የሚደርስባቸውን ወሲባዊ ጥቃት የሚያጠና እንደሆነ የሚነገርለት ተቋም፣ በተመሳሳይ እ.ኤ.አ. በ2019 ጥቃቱ ቀድሞ ከነበረበት ከዘጠኝ ሺሕ ወደ 15 ሺሕ ማደጉን፣ ቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ ይጠቁማል፡፡ በኢንተርኔት አማካይነት በተለይ የሕፃናት ወሲባዊ ጥቃት በእጅጉ እየጨመረ ስለመምጣቱ ማሳያ እንደሆነም ያክላል፡፡

ለችግሩ ከወዲሁ መፍትሔ ሊፈለግለት ይገባል የሚሉት በቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ ቻይልድ ፕሮቴክሽንና አድቮኬሲ ስፔሻሊስት አቶ ሚካኤል አማረ ናቸው፡፡

ቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች አካላት ልዩ ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩበት ይገባል ያሉት ባለሙያው፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድገት የሕፃናት ወሲባዊ ጥቃትና ብዝበዛን እየጨመረ መምጣቱን ዩኒሴፍ እ.ኤ.አ. በ2021 ያወጣውን መረጃ መሠረት አድርገውም ገልጸዋል፡፡

በበይነ መረብ አማካይነት በተለይ በሕፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል ያስችላል የተባለ ፕሮጀክት፣ በአዲስ አበባ በሚገኙ የተመረጡ ትምህርት ቤቶች ለመተግበር ወደ ሥራ መግባቱንም የቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ የፕሮግራምና ስፖንሰርሺፕ ዳይሬክተር አቶ አባዲ አምዲ ተናግረዋል፡፡

ቴክኖሎጂ ባደገ ቁጥር የጎንዮሽ ጉዳቱም አብሮ እያደገ ይመጣል ያሉት አቶ አባዲ፣ በተለይ ከኢንተርኔት አጠቃቀም መስፋፋት ጋር ተያይዞ በሕፃናት ላይ እየደረሰ ያለው ወሲባዊ ጥቃት ከአሳሳቢ ደረጃ መድረሱን አንስተዋል፡፡

በኢንተርኔት አማካይነት እየደረሱ ያሉ ጥቃቶች በተለይ በትልልቅ ከተሞች ጎልተው የሚታዩ በመሆናቸው፣ ድርጅታቸው ፕሮጀክት ቀርፆ መሥራት መጀመሩን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፣ በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ በ13 ወረዳዎችና በስድስት ክፍላተ ከተሞች ባሉ 20 ትምህርት ቤቶችን እንደሚያጠቃልል ጠቁመዋል፡፡

ፕሮጀክቱ  በአሥር ሚሊዮን ብር በጀት ለመተግበር የታቀደ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 11 ሚሊዮን 887 ሺሕ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆችና የመንግሥት አካላት ተደራሽ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡

ትምህርት ቤቶች እንዴትና በምን ተመረጡ ለሚሉት ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት አቶ አባዲ፣ በትምህርት ቤቶቹ በተደረገ ዳሰሳ ተማሪዎች ስማርት ስልክ በብዛት እንደሚጠቀሙና ችግሩም ጎልቶ በመታየቱ ነው ብለዋል።

ፕሮጀክቱ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት በትምህርት ቤቶች፣ በወላጆችና በመምህራን እንዲሁም በባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ እንደሚሠራ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ምንም እንኳን ተማሪዎች ማንኛውንም ስልክ ወደ ትምህርት ቤት ይዘው እንዳይሄዱ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ክልክል ቢሆንም፣ ወላጆች ልጆቻቸውን የጠቀሙ መስሏቸው ስልኮችን በመስጠት ለአደጋ እየዳረጓቸው ነው ብለዋል።

ይህ ደግሞ ተማሪዎች በትምህርታቸውም ሆነ በማንኛውም እንቅስቃሴ ደካማና ለሱስ ተጋላጭ እንዲሆኑ በማድረግ ብቁ ዜጋ ለማፍራት እንቅፋት ስለመሆኑ አቶ አባዲ ተናግረዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...