Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅዱራዊው  ምግብ

ዱራዊው  ምግብ

ቀን:

በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክ የተለያዩ ነፍሳት ይበላሉ። ቦቦ የሚባሉት ምስጦች (አሸን) በክረምት ወራት በኩይሳዎቻቸው፣ በከተሞች ውስጥ ደግሞ በኤሌክትሪክ ብርሃን አካባቢ በብዛት ይገኛሉ። ማታ ላይ ኃይለኛ ዝናብ ከጣለ በኋላ ልጆች እየተሯሯጡ አሸኖቹን በመልቀም በቅርጫት ይሰበስቧቸዋል፤ አብዛኛውን ጊዜም አሸኖቹን እየዘገኑ ሲቅሙ የሚሰማቸውን ደስታ ፊታቸው ላይ መመልከት ይቻላል። እነዚህ ምስጦች በፀሐይ ደርቀው፣ በጨውና በበርበሬ ተቀምመውና ተጠብሰው አሊያም በወጥ ወይም በሳምቡሳ መልክ ተሠርተው ይበላሉ።

በበጋው ወራት ወደ አካባቢው የሚመጡት አረንጓዴ ፌንጣዎች ኪንዳጎዞ ይባላሉ። የማዕከላዊ አፍሪካ ነዋሪዎች፣ ተለቅ ተለቅ ያለውን የፌንጣዎቹን ክንፍና እግር ከቀነጠሱ በኋላ ጠብሰው ወይም አገንፍለው ይበሏቸዋል።

በተጨማሪም በመላ አገሪቱ የተለያዩ የአባጨጓሬ ዝርያዎች ይበላሉ። እኛም ኢምብራሲያ የሚባለውን ነፍሳት እጭ እንድንበላ ተጋበዝን። ቡናማ ቀለም ያላት ትልቅ የእሳት እራት በሳፔሊ ዛፎች ላይ እንቁላሏን ትጥላለች። እጮቹ ከተቀፈቀፉ በኋላ መንደርተኞቹ ለቅመው ይወስዱና ያጥቧቸዋል። ከዚያም እነዚህ አባጨጓሬዎች ከቲማቲም፣ ከቀይ ሽንኩርትና ከሌሎች ቅመሞች ጋር እንዲበስሉ ይደረጋል። አንዳንዶቹ እንዳይበላሹ ሲባል ደርቀው ወይም በጭስ ታጥነው ይቀመጣሉ። ይህም እስከ ሦስት ወር ድረስ ሳይበላሹ እንዲቆዩ ያደርጋቸዋል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

– ‹‹ንቁ!›› (2012)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...