Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
የሳምንቱ ገጠመኝየ ሳ ም ን ቱ ገ ጠ መ ኝ

የ ሳ ም ን ቱ ገ ጠ መ ኝ

ቀን:

አንዳንዴ የሚያጋጥሙን ነገሮች ወቅታዊነታቸውን መጠበቃቸው ብቻ ሳይሆን፣ የሰዎችን ስሜት ኮርኳሪ መሆናቸው ይገርማል፡፡ በየደረስንባቸው ሥፍራዎች እንዲህ የሚገራርሙ ነገሮች ሲያጋጥሙን በማስታወሻ የመያዝ ልምድ ስለሌለን፣ ገጠመኞቻችን በቃል ከአንዱ ወደ አንዱ እየተላለፉ እንዲሁ ባክነው በመቅረታቸው ሁሌም ያንገበግበኛል፡፡ አንዳንዴ ለማመን የሚያዳግቱ ነገሮች ሲያጋጥሙን እንዲህም አለ ወይ የምንለው ያህል፣ እንደ ዘበት እያየን ትኩረት የማንሰጣቸው ነገሮችም አሉ፡፡ ነገር ግን የሚገጥሙንን ነገሮች መመዝገብ ወይም በአዕምሮ ውስጥ ይዞ ላላዩ ወይም ላልሰሙ ማጋራት መልካም ነው፡፡ ቢያንስ የውይይት ባህል ያዳብራል፡፡

በቀደም ዕለት ያጋጠመኝን አስቂኝ አጋጣሚ ለጋዜጣው አንባቢያን ማካፈል የግድ በመሆኑ እንዲህ ልንገራችሁ፡፡ ከሜክሲኮ መገናኛ የተሳፈርንበት ታክሲ በየደረሰበት እያወረደና እየጫነ የተንቀረፈፈ ጉዞውን ቀጥሏል፡፡ በታክሲው ላይ የሚሳፈሩ የተለያዩ ሰዎች አንዴ ከወያላው፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከሾፌሩ ጋር እየተጨቃጨቁ መውጣታቸውንና መውረዳቸውን ቀጥለዋል፡፡ በዚህ መሀል ደግሞ ተረብ ጣል የሚያደርጉም አልጠፉም፡፡

አንዳንዱ ሰው በሞባይሉ ሲደወልለት በቶሎ ስለማያነሳው የማንሰማው የድምፅ ዓይነት አልነበረም፡፡ የአንደኛዋ ስልክ ሲጮህ መንፈሳዊ መዝሙር ተሰማ፡፡ ካሁን አሁን ስልኳን አነሳችው ስንል ጭራሽ በእጇ ይዛው የሚደወልላትን ጥሪ ችላ በማለት መዝሙሩን ታስኮመኩመን ጀመር፡፡ አንድ በስጨት ያለ ሰው፣ ‹‹እባክሽን መዝሙሩን ዘግተሽ ለጥሪው መልስ ስጪ፣ አትበጥብጪን…›› ሲላት ቆጣ ብላ፣ ‹‹ለበረከት ብዬ ነው እንጂ ለእንዳንተ ዓይነቱማ የምሥጋና መዝሙር ማሰማትም አያስፈልግም…›› ስትለው ሰውዬው አንገቱን ወዝውዞ ዝም አለ፡፡ በዚህ መሀል ከመሀል ወንበር አንዱ፣ ‹‹ቅዱስ መጽሐፉ እንዲህ ይላል እንዴ?›› ሲላት ሰውየው ደግሞ፣ ‹‹ቅዱስ መጽሐፉን ብታውቀው ኖሮ መቼ ትታበይ ነበር…›› ብሎ በነገር ሸነቆጣት፡፡ የቃላት ጦርነቱ ያሠጋው ሌላው፣ ‹‹እባካችሁ ተረጋጉ በፖለቲካው ላይ ይህንን ጨምረንበት መቆሚያችን የት ሊሆን ነው?›› ሲል ዝምታ ለአፍታ ሰፈነ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ትንሽ ቆይቶ ግን የአውራ ዶሮ ጩኸት ተሰማ፡፡ ለካስ የጮኸው የአንደኛው ተሳፋሪ አሮጌ ሞባይል ስልክ ነበር፡፡ ይኼኛውማ ታክሲውን ዶሮ ተራ አስመሰለው፡፡ ጥሪው እስኪያበቃ ድረስ በአውራ ዶሮ ጩኸት በጠበጠን፡፡ ወያላው በመገረም፣ ‹‹ምነው የዶሮው ነጠላ ዜማ እንዲህ በዛ?›› አለው፡፡ ሰውዬው ምንም እንዳልተፈጠረ በሚመስል ስሜት፣ ‹‹የዶሮ ጩኸት እኮ በጣም ደስ ይላል…›› ሲል ሁላችንም ሳንወድ ሳቅን፡፡ ወደው አይስቁ ማለት እንዲህ አይደል? ‹‹የዶሮ ጩኸት እንዲህ ሲያስደስት ዛሬ ገና መስማቴ ነው፡፡ አንዳንዱ እኮ ተናገር ሲሉት ይዘጋል…›› እያለ ሲነጫነጭ የሌሎችን ንጭንጭ የሚቀሰቅስ ይመስል ነበር፡፡

እንዲህ፣ እንዲህ እያልን መስቀል አደባባይን ከተሻገርን በኋላ ታክሲዋ ቆመች፡፡ አንዲት ወይዘሮ ወርደው በሌላ ጎልማሳ ተተኩ፡፡ ጎልማሳው ከታክሲ ውስጥ ሲገባ በስልኩ እያወራ ነበር፡፡ ጉዳዩ በውል ባይታወቅም ንግግሩ ከኃይል ጋር የተቀላቀለ ነው፡፡ ‹‹ቆይ ብቻ ላግኘው፣ እኔ አይደለሁም ስመጣ ማንነቴን አሳየዋለሁ…›› እያለ ይፎክራል፡፡ ከወዲያኛው ጫፍ ሰላማዊ እንዲሆን ቢነገረውም፣ ‹‹ሰላም የሚባል ነገር አላውቅም፣ አስፈላጊውን ዕርምጃ ወስጄ አሳየዋለሁ…›› እያለ ዓይኖቹን ያጉረጠርጣል፡፡ ሁላችንም ትንፋሻችንን ውጠን እያዳመጥነው ነበር፡፡ ስልኩንም ዘግቶ በንዴት ይርገፈገፋል፡፡ አንዳንዱ ሰው ምን እየሆነ ነው እንዲህ የተራበ አውሬ ይመስል የሚሆነውን የሚያሳጣው? አንዲት ልጅ እግር ወጣት፣ ‹‹ይኼማ እዚህ ይፎክራል እንጂ ሲደርስ መዝረጥረጡ አይቀርም…›› እያለች በባላገር የአነጋገር ዘዬ ስትናገር ፈገግ አሰኘችኝ፡፡

ታክሲያችን አሁን ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ደርሳለች፡፡ ወያላው ሰውየውን ሒሳብ ጠየቀው፡፡ አምስት ብር አውጥቶ ሰጠው፡፡ ከዚህ በኋላ በዚህ ሒሳብ እንደማይጓዝ ተነገረው፡፡ ‹‹ሒሳቡ በቂ ነው ውኃ ልማት ነው የምወርደው…›› አለ፡፡ ‹‹ውኃ ልማት ከሆነ የምትሄደው ሒሳብ ጨምር አለበለዚያ አምስት ብር ጨምረህ እዚህ ውረድ…›› አለው፡፡ ጎልማሳው ደረቱን ነፋ አድርጎ፣ ‹‹አልወርድም…›› አለው፡፡ ወያላው ቢቸግረው፣ ‹‹አንተ ደግሞ የየትኛው አገር አምባገነን ነህ፣ በል እባክህን ውረድ….›› ሲለው ሁላችንም በሳቅ ታፍነን አፍጥጠን እናይ ጀመር፡፡ ጉልበተኛው ወደ ኃይል ይሸጋገር ይሆን በማለት ሥጋትም ገባን፡፡ ጎልማሳው ሁላችንንም ሲያየን በሥጋት ወይም በጥላቻ እያየነው እንደሆነ ገባው መሰል፣ ‹‹ሕዝቡ ካለ በቃ እወርዳለሁ…›› ብሎ ዘሎ ሲወርድ ታክሲዋ በሳቅ ማዕበል ተርገፈገፈች፡፡

በነገራችን ላይ የመንግሥት ሥልጣን የያዙም ሆነ የመንግሥት ሥልጣን ለመያዝ የሚፈልጉ ሰዎች፣ በተለይ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በታክሲ ወይም በአውቶቡስ አልባሌ ሰው መስለው ቢገኙ፣ ስንትና ስንት ጠቃሚ ትምህርት ያገኙ ነበር፡፡ እኔ በበኩሌ የከተሜ ባህሪ ያልተላበሰ ፖለቲከኛም ሆነ አስተዳዳሪ አይመቸኝም፡፡ ከተሜነት የሚረዳው ብልህ ለመሆንና የሰዎችን ስሜት በቀላሉ ለመረዳት ነው፡፡ የከተማ ሌባ ሲሰርቅ ጭምር በጥበብ ስለሆነ ከማቴሪያል ጉዳት የዘለለ በጤናም ሆነ በሕይወት ላይ ችግር አይፈጥርም፡፡ ይህንን ስል ሌብነትን እያበረታታሁ አይደለም፡፡ ነገር ግን ለማይረባ ገንዘብ ወይም ዕቃ በኮብልስቶን ፈልጦ ከሚገድል ሞኝ የከተሜው ብልጥ ይሻላል ለማለት ነው፡፡

የሆነ ሆኖ ፖለቲከኞች ከከተሜነት በጣም ርቆ ሥልጣኔ የጎደለው ፖለቲካችሁንና እንካ ሰላንቲያችሁን ወደ ጎን ገፍታችሁ፣ ራሳችሁን እያዘመናችሁ ሰው ምሰሉ፣ ሰብዓዊ ሁኑ፣ በሰው ደም አትነግዱ፡፡ ከራሳችሁ በፊት አገር አስቀድሙ፡፡ የአገርን ታሪክና የትውልዶችን መስዋዕትነት እያራከሳችሁ በሕዝብ አትጠሉ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ትውልድና ታሪክ ይጠይቃሉ፡፡ የታሪክ ተጠያቂ መሆንን የመሰለ ዕዳ ለልጆቻችሁም አታውርሱ፡፡ በሌላ በኩል የእምነቶች መሪዎችም ከሰው ትዕዛዝ ይልቅ የፈጣሪን አክብሩ፡፡ ፈጣሪም ጊዜው ሲደርስ ይጠይቃልና፡፡  

(መንገሻ ወርቁ፣ ከልደታ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...