Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን ማስተናገድ የሚችል ሰው ሠራሽ ሳር የተተከለለት የድሬዳዋ ስታዲየም

ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን ማስተናገድ የሚችል ሰው ሠራሽ ሳር የተተከለለት የድሬዳዋ ስታዲየም

ቀን:

ኢትዮጵያ ሦስት የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታን በ1954 ዓ.ም. ሦስተኛውን፣ በ1960 ስድስተኛውን፣ እንዲሁም በ1968 አሥረኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ማስተናገድ ችላለች፡፡

ሦስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ በአዲስ አበባ በአራት ቡድኖች መካከል ሲካሄድ፣ ስድስተኛው በአዲስ አበባ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስታዲየምና በአሥመራ ንግሥተ ሳባ ስታዲየም፣ አሥረኛው በአዲስ አበባና በድሬዳዋ በስምንት ስምንት ቡድኖች ተከናውኗል፡፡

ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን ማስተናገድ የሚችል ሰው ሠራሽ ሳር የተተከለለት የድሬዳዋ ስታዲየም | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አሥረኛው የአፍሪካ ዋንጫ በሁለት ምድብ ሲካሄድ በምድብ አንድ ኢትዮጵያ፣ ጊኒ፣ ግብፅና ዑጋንዳ፤ በምድብ ሁለት ሞሮኮ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳንና ዛየር ተደልድለዋል፡፡ ድሬዳዋ የምድብ ሁለቱን ጨዋታ 18,000 ተመልካች በሚይዘው ስታዲየም ማስተናገድ መቻሉ ይታወሳል፡፡

ከአገር ውስጥ በዘለለ የዓለም አቀፍ ውድድሮችን የማስተናገድ አቅም የነበረው  ስታዲየሙ፣ ለዘመናት በአገር ውስጥ ውድድሮች ተወስኖ ቆይቷል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ አገር አቀፍ ውድድሮችን ብቻ በማስተናገድ ተጠምዶ የሰነበተው ድሬዳዋ ስታዲየም፣ በተለይ በዝናብ ወቅት ማስተናገድ ተስኖት ሲቸገር መቆየቱና ውድድሩም መቋረጡ ይታወሳል፡፡

ከዚህም ባሻገር የአዲስ አበባና የባህር ዳር ስታዲየሞች ከደረጃ በታች መሆናቸው ተከትሎ በካፍ በመታገዳቸው፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በራሱ ሜዳ የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች በተለያዩ አገሮች ለማድረግ ተገዷል፡፡ 

በኢትዮጵያ የካፍና የፊፋን መሥፈርት ያሟሉ ስታዲየሞች አለመኖራቸውን የተረዳው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በስታዲየሙ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ የመጫወቻ ሜዳ ሳር ተከላ ለማከናወን እንቅስቃሴ ጀመረ፡፡

ለአገሪቱ በዓይነቱ ልዩ የሆነና የፊፋን መሥፈርት ያሟላ ሰው ሠራሽ ሳር ተከላ ለማከናወን ከተን ኢንጂነሪንግ ጋር በመሆን ጥናት በማድረግ ወደ ሥራ መገባቱን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር አስረድተዋል፡፡

የስታዲየሙ የሳር ተከላ ሒደት በአራት ወራት ይፈጸማል ቢባልም፣ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀው ግን በስድስት ወራት ውስጥ ነው፡፡

በፊፋ ዕውቅና ካገኘ ተቋም የሳር ግዥው ከመፈጸሙ አስቀድሞም የሰው ሠራሽ ሳሩ ርጥበትን መቋቋም የሚችል መሆኑና ከመሬት አሠራሩ ጋር የተጣጣመ እንደሆነ በማጣራት መረጋገጡ ተገልጿል፡፡

የድሬዳዋን ስታዲየም የሰው ሠራሽ ንጣፍ የሚያከናውነው የታን ኢንጂነሪንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ፉአድ ኢብራሂም ነው፡፡

በኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ ሳር ተከላ ጋር ተያይዞ ቅሬታዎች ሲነሱ ይስተዋላል፡፡ ቢሆንም የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ግን በድሬዳዋ የተተከለው ሰው ሠራሽ ሳር ደረጃውን የጠበቀ እንደሆነ ያስረዳል፡፡

‹‹የድሬዳዋ ስታዲየም የሰው ሠራሽ ሳር በኢትዮጵያ ካሉ የተለየና ደረጃውን የጠበቀ ነው፡፡ በዚህ ስታዲየም የተጠቀምናቸው ማቴሪያሎች በጥሩ ሁኔታ ስለተነጠፉና በፊፋ ዕውቅና ባገኙ ተቋማት የተገመገመ ነው፤›› በማለት፣ የታን ኢንጂነሪንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፉአድ አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የፊፋ ቴክኒካል ልዑክ የድሬዳዋ የሰው ሠራሽ የሜዳ ሳር ንጣፉን ግምገማ አድርጓል፡፡ መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገው ‹‹ስፖርት ላብ ዩኬ›› የተሰኘ የስፖርት ቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር ተቋም የድሬዳዋ ስታዲየምን ሰው ሠራሽ ሳርና ሜዳውን ገምግሟል፡፡

የሰው ሠራሽ ሜዳ ንጣፍ የፊፋን መሥፈርት አማልቶ ስለማጠናቀቁ ለማረጋገጥ የመጡት እንግሊዛውያኑ ኮሊን ሚችልና እቤን ጋሊሞር ናቸው፡፡

በግምገማው ወቅት ሜዳው የተጠቀመበት ልኬት፣ የመሬቱ ጥብቅነት ከተፈጥሮ ሳር ጋር ያለው መቀራረብ፣ ኳስን የማንጠርና የማሽከርከር አቅም፣ የሳሩ ቁመት፣ የራበሩ ምጣኔ እንዲሁም የመጫወቻ ጫማ መሬት ሲረግጥ ሰበቃው እንዴት ነው የሚለው ታይተዋል፡፡

ባለሙያዎቹ ሜዳው ከመሥፈርት አንፃር ገምግመው ሪፖርቱን ለፊፋ እንደሚልኩና የግምገማው ውጤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ይገለጻል ተብሏል፡፡

የሳር ተከላውን ደረጃ የገመገሙት ባለሙያ ሜዳው ማንኛውንም ዓለም አቀፍ ጨዋታ ማስተናገድ ይችላል፡፡ ሜዳውን በሚገባ መመርመራቸውን የገለጹት የስፖርት ላብ ዮኬ የምርምር ባለሙያው፣ ብሔራዊ ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ፣ የዓለም ዋንጫ፣ እንዲሁም ማንኛውንም ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን በሜዳው ማከናወን ይችልበታል በማለት አስረድተዋል፡፡

የድሬዳዋ ስታዲየም ሜዳ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ ከተወሰኑ የሻምፒዮንስ ሊግ ሜዳዎች ጋር ተመጣጣኝ እንደሆነ፣ ለጨዋታም ምቹ መሆኑንም ባለሙያው ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

ሆኖም ስታዲየሙ ሙሉ በሙሉ ዕድሳት ተደርጎለት የተጠናቀቀ ሳይሆን፣ በካፍም ሆነ በፊፋ በዝርዝር የተቀመጡ መሥፈርቶች ማሟላት ሲችል ዕውቅና የሚያገኝ ይሆናል፡፡

ከስታዲየም ሳር ተከላው ባሻገር የመልበሻ ክፍል፣ ቪአይፒ፣ የሚዲያ ክፍል፣ መፀዳጃ ክፍሎች ሲጠናቀቁ፣ ለ20,000 ተመልካች የሚሆኑ ወንበሮችም ተተክለዋል፡፡ ስታዲየሙ ሁለት አሳንሰሮች የተገጠሙለት ሲሆን፣ የተቀያሪ ተጫዋቾች የሚቀመጡበት ወንበር ከውጭ እየገባ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

ዕድሳቱ መጠናቀቁን ተከትሎ በሚኖረው የምረቃ መርሐ ግብር፣ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች የሚሳተፉበት ‹‹የከንቲባ ዋንጫ›› ጨዋታ በስታዲየሙ እንደሚከናወን ተጠቅሷል፡፡ በውድድሩ ከኢትዮጵያ ጋር የኬንያ፣ ጂቡቲና ሩዋንዳ  ብሔራዊ ቡድኖች እንደሚሳተፉ ማረጋገጫ መላካቸውም ተገልጿል፡፡

የከንቲባ ዋንጫ ጨዋታውም የስታዲየሙን ጥራትና ደረጃ ለመገምገም እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል በአዳማ እየተከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ቀጣይ ማረፊያ እስኪሆን አልታወቀም፡፡ 14ኛው ሳምንት ከየካቲት 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ቀጣይ ማረፊያው ይታወቃል፡፡ ቀጣዩ ማረፊያ ድሬዳዋ ወይስ ሐዋሳ የሚለው በቅርቡ ምላሽ ያገኛል፡፡

የድሬዳዋ ስታዲየም በአጭር ጊዜ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሰው ሠራሽ ሳር ተከላና ዕድሳት ማድረጉ፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኖች ተስፋ የሚሰጥ ተግባር መሆኑ ተጠቅሷል፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...