Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና የኢትዮጵያን ተደማጭነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት ለማረጋገጥ እንደሚሠራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

 የኢትዮጵያን ተደማጭነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት ለማረጋገጥ እንደሚሠራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ቀን:

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እ.ኤ.አ. በ2024 ካስቀመጣቸው የውጭ ግንኙነት ሥራዎች መካከል፣ የኢትዮጵያን ተደማጭና ተፅዕኖ ፈጣሪነት ማረጋገጥ ትልቁ ሥራው መሆኑን አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ መለስ ዓለም (አምባሳደር) ጥር 30 ቀን 2026 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ‹‹በተቀረፀልንና በተቀመጠልን አጀንዳ መሳተፍ ብቻ ሳይሆን፣ ለአፍሪካም ሆነ ለዓለም የሚረዱና የሚጠቅሙ አጀንዳዎችን በመቅረፅ፣ ከኢትዮጵያ ሊወሰዱ የሚገቡ በጎ ልምዶችን እንዲገነዘቧቸውና እንዲረዷቸው እየሠራን ነው፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ዳቦን የማይፈጥር፣ እንጀራን የማይፈጥር ዲፕሎማሲ በቂ ዲፕሎማሲ አይደለም፤›› ያሉት ቃል አቀባዩ፣ የዲፕሎማሲ መጀመሪያና መጨረሻው ኢኮኖሚ መሆኑን ገልጸው፣ ለየትኛውም አገር የዲፕሎማሲ ሥራ መድረሻውም መጨረሻውም ብሔራዊ ጥቅም እንጂ ለፅድቅ የሚደረግ አይደለም ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አክለውም የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ ማዕከል የሚያደርገው ለኢኮኖሚ ልማት የሚሆን የፋይናንስ ድጋፍ ማሰባሰብ፣ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር እንዲኖር ማድረግ፣ የገበያ ትስስር መፍጠር፣ ኢንቨስትመንት መሳብና የቱሪስት መዳረሻዎችን ማስፋፋትና መሰል ጉዳዮች እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡ 

መለስ (አምባሳደር) ኢትዮጵያ በቅርቡ አባል በሆነችበት ብሪክስ በተሰኘው ቡድን በ2015 ዓ.ም. የተቋቋመውን የብሪክስ ልማት ባንክ አገሪቱ እንድትቀላቀል፣ አባል አገሮች ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎታቸውን መግለጻቸውን አስታውቀዋል፡፡ 

በዚህ ሳምንት ለሚካሄደው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ ማረጋገጫ ከሰጡ ከፍተኛ የአገርና የመንግሥት መሪዎች መካከል 24 ፕሬዚዳንቶች፣ አንድ ንጉሥ፣ አምስት ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ ሁለት ጠቅላይ ሚኒስትሮችና ሁለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉ ማሳወቃቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ መሪዎች ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት ይገልጻሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቆሙት ቃል አቀባዩ፣ በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ፣ የኢጋድ ዋና ጸሐፊ፣ የዓረብ ሊግ ዋና ጸሐፊና ሎሎችም ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው በሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የቀረበለትንና ለሦስት አሥርት ዓመታት በተለያዩ አገሮች ዲፕሎማት ሆነው በማገልገልና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ኢትዮጵያን በመወከል በሚያደርጉት ንግግር በብዙዎች ዘንድ ስማቸው የሚጠራውን የታዬ አጽቀ ሥላሴ (አምባሳደር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሹመት ማፅደቁ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...