Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበዲጂታል ክህሎት ሥልጠና ከአንድ ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ተጠቃሚ ሊሆኑ ነው

በዲጂታል ክህሎት ሥልጠና ከአንድ ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ተጠቃሚ ሊሆኑ ነው

ቀን:

በምሕረት ሞገስ

በብሔራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ውስጥ ከተካተቱ ትግበራዎች አንዱ በሆነውና ወጣቶችን በዲጂታል ክህሎት (ታለንት) አብቅቶ ተጠቃሚ ለማድረግ በሚያስችለው ፕሮጀክት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ወጣቶች እንደሚሠለጥኑ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2020 እስከ 2025 ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዕውን ለማድረግ ከጃይካ፣ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያና ከሱሚቶሞ ኮርፖሬሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረመው ሚኒስቴሩ፣ ከእነዚህ አካላት ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ 10,000፣ በሒደት ደግሞ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ወጣቶችን በዲጂታል ታለንት ዙሪያ እንደሚያሠለጥን ገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ ወጣቶችን በዲጂታል ታለንት ለማሠልጠን፣ ለማብቃትና ተጠቃሚ ለማድረግ ከጃይካ፣ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያና ከሱሚቶሞ ኮርፖሬሽን ጋር የመከሩ ሲሆን፣ ለዲጂታል ታለንት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራም መናገራቸውን ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አሥፍሯል፡፡

በጃይካ የዲኤክስ ላብ ኃላፊ ዩሺ ናጋኖ፣ በኢትዮጵያ በብሔራዊ ደረጃ 10,000 ዲጂታል ታለንት ያላቸው ወጣቶችን በአጭር ጊዜ በማብቃት፣ በቀጣይ የሚሊዮኖችን አቅም ለመፍጠር እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

ከሚኒስቴሩ ባገኘነው መረጃ መሠረት፣ ሥልጠናዎቹ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበሩና በ2025 ዲጂታል ዕቅድ ላይ የተቀመጡ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ የኢትዮጵያን 2025 ዲጂታል ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ፣ ሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም ከተቋማቱ ጋር ተፈራርሟል፡፡ በዕቅዱ ከተካተቱት ደግሞ፣ የወጣቶችን የዲጂታል ታለንት ማጠናከርና ማሳደግ ይገኝበታል፡፡

ሥልጠናውም ዲጂታል ክህሎት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ መሠረታዊ ሥልጠናዎች ማለትም ኮምፒዩተርና ስልክ መጠቀም እንዲችሉ፣ በአንድ ቴክኖሎጂ ዙሪያ መሠረታዊ ክህሎት እንዲኖራቸውና ቴክኖሎጂውን ጥቅም ላይ እንዲያውሉት፣ ከዚህ በፊት እየሠሩ ያሉበትን ቴክኖሎጂ ይበልጥ እንዲያሳድጉ ማስቻልና በጣም ከፍተኛና በዓለም ውስጥ ተፈላጊነት ባላቸው ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ክህሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው፡፡

በወጣት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ የሥልጠናው ተጠቃሚ የሚሆኑ ሲሆን፣ ከመጀመሩ በፊትም ወጣቶች የሥልጠናው ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ የሚቀርብ ይሆናል፡፡

ሥልጠናው ሠልጣኞችን ወደ ሥራ በማስገባትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግና በሥራ ውስጥ ያሉትንም እንደተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ አሠራራቸው የበለጠ የዘመነ እንዲሆን ያግዛል፡፡

በርካታ ዘርፎችን በሚዳስሰው ሥልጠና፣ ሠልጣኞች የሥራ ሐሳብ የሚያገኙበት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

መንግሥት ተግባራዊ እያረገ ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ የተለያዩ የፖሊሲና የስትራቴጂ መሣሪያዎችን እያስተዋወቀና ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡ ከእነዚህም ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መካከል እ.ኤ.አ. ከ2020 እስከ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው  ብሔራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ አንዱ ነው፡፡

የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ፣ በኢትዮጵያ ውጤታማና አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ ድህነትን ለመቅረፍ፣ ዕድገትን ለማስፋፋት፣ አዳዲስ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀምና የመወዳደር አቅምን ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡

ስትራቴጂው ከብሔራዊ ሶሺዮኢኮኖሚክና ዕድገት ዕቅዶች ከሆኑት ከብሔራዊ የ10 ዓመት የልማት ዕቅድናና የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያን መሠረት አድርጎ ከተባበሩት መንግሥታት ዘላቂ የልማት ግቦች፣ እንዲሁም ከተለያዩ የዓለም አቀፍ ኢኒሺየቲቮች ጋር የተጣጣመ ስለመሆኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...