Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልተመላሽዋ ንሥረ ፀሐይ የተባለችው ‹‹ኢትዮጵያ 1›› አውሮፕላን

ተመላሽዋ ንሥረ ፀሐይ የተባለችው ‹‹ኢትዮጵያ 1›› አውሮፕላን

ቀን:

‹‹በፋሺስቱ አምባገነን በቤኒቶ ሙሶሎኒ ትእዛዝ ከኢትዮጵያ በ1929 ዓ.ም. የተዘረፈውን እና በዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት ያልተመለሰውን የአክሱም ሐውልት መመለስ እየጠበቅን ሳለ፣ ምናልባት ሌላ ትኩረት የሚስብ የተዘረፈን የኢትዮጵያ አውሮፕላን እንዲመለስ ጥያቄ ለማቅረብ ጊዜ አለን።››

ተመላሽዋ ንሥረ ፀሐይ የተባለችው ‹‹ኢትዮጵያ 1›› አውሮፕላን | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ንሥረ ፀሐይ በ2016 ዓ.ም.
በሮም

ይህን ኃይለ ቃል ከሦስት አሠርታት በፊት አለፍ በሚል ጊዜ ያስተጋቡት የታሪክ ሊቁ ሪቻርድ ፓንክረስት (ፕሮፌሰር) ናቸው፡፡ Unreturned Loot, in Italy እና Tsehai: Aeroplane or Princess? በሚሉ ርዕሶች በፋሺስት ጣሊያን ወራሪዎች የተዘረፉ ቅርሶች ለኢትዮጵያ እንዲመለሱ ከኢትዮጵያውያን አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ይወተውቱ ነበር፡፡ ቀዳሚው ፍሬ ያፈራው የአክሱም ሐውልት በኢትዮጵያ ሚሌኒየም ክብረ በዓል ዋዜማ መመለሱ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በፋሺስት ጣሊያን ወረራ (1928-1933) ዋዜማ አዲስ አበባ ውስጥ የተመረተችውና ‹‹ኢትዮጵያ 1›› የተባለችውና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተወዳጅ ልጅ ልዕልት ፀሐይ ስምን በመውሰድ ወደ ‹‹ንሥረ ፀሐይ›› የተሸጋገረችው ትንሽ አውሮፕላን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ ዘጠኝ አሠርታት ያህል ጊዜ ወስዶባታል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ተመላሽዋ ንሥረ ፀሐይ የተባለችው ‹‹ኢትዮጵያ 1›› አውሮፕላን | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ንሥረ ፀሐይን በሰነድ በተረከቡበት
ወቅት

ባለፈው ሳምንት ለጣሊያን አፍሪካ ጉባዔ ወደ ሮም ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ አውሮፕላኗን ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጣሊያን መንግሥት በይፋ ተረክበዋል። ይህን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ‹‹ዛሬ ፀሐይ አውሮፕላንን ከጣሊያን መንግሥት በይፋ መረከባችንን የምናከብርበት ታሪካዊ ቀን በመሆኑ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ታላቅ የኩራት ቀን ነው፤›› ብለዋል።  ላለፈው አንድ ዓመት አውሮፕላኑን የመመለስ ሒደቱን ሲያግዙ በመቆየት ለውጤት ያበቁ የጣሊያን አቻቸውን ጂኦርጂያ ሜሎኔንም አመስግነዋል።

 ንሥረ ፀሐይ በጣሊያን አቪዬሽን ሙዚየም የነበረች ሲሆን፣ የተሠራችውም የአፄ ኃይለ ሥላሴ ፓይለት በነበረው ጀርመናዊ አብራሪ ሉድቪግ ዌበር ነበር፡፡ ዌበር በ1925 ዓም. ወደ አዲስ አበባ የመጣው የጁንከርስ የጀርመን ኩባንያ ተወካይ ሆኖ፣ የኢትዮጵያ አቪዬሽን እንዲቋቋም እንዲረዳ ተልዕኮ ተሰጥቶት እንደነበር ፓንክረስት ጽፈዋል።

በመጣጥፉ እንደተገለጸው፣ ዌበር አውሮፕላኑን ዲዛይን ያደረገው ከአንድ ዓመት ወይም ከዚያ ቀደም ብሎ በፍሪቡርግ በተሠራው የጀርመን ሞዴል ላይ ነው። በአዲስ አበባ ከሦስት ባላነሱ አውሮፕላኖች ላይ የግንባታ ሥራውን የጀመረ ቢሆንም፣ በፋሺስት ወረራ ምክንያት አንዱ ብቻ ነው የተጠናቀቀው። አውሮፕላኑ ሞኖ አውሮፕላን ሲሆን፣ በሰባት ሲሊንደር ዋልተር ቬኑስ፣ 115 የፈረስ ጉልበት ሞተርና ሽዋርትዝ ፕሮፕለር እንደነበረው፣ የጭስ ማውጫው ከብረት፣ ክንፎቹ ላይ የንፋስ መከላከያ ፕላስቲክ ነበር።

እንደ ፓንክረስት ማብራሪያ ታሪካዊው አውሮፕላን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ የተቀባ ነበር፡፡ ከዚያም ከ‹‹ኢትዮጵያ 1›› የሚለው ስያሜዋን ንጉሠ ነገሥቱ በሚወዷት በሴት ልጃቸው ልዕልት ፀሐይ ስም ‹‹ንሥረ ፀሐይ›› ተብላለች፡፡

በ1928 ዓ.ም. የመጀመርያው መንፈቅ የመጀመሪያው በረራ የተደረገባት ንሥረ ፀሐይ፣ አገልግሎቷ አጭር ነበር። አውሮፕላኗ የበረረችው በአጠቃላይ ሠላሳ ሰዓታት ብቻ የሆነው፣ የወራሪዎቹ የፋሺስት ጣሊያን ሠራዊት ግስጋሴ ዌበር እና ሠራተኞቹ ከኢትዮጵያ እንዲወጡ በማስገደዱ ነበር።

ተመላሽዋ ንሥረ ፀሐይ የተባለችው ‹‹ኢትዮጵያ 1›› አውሮፕላን | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ከሦስት አሠርታት በፊት ከአክሱም ሐውልት በተጨማሪ ንሥረ
ፀሐይ መመለስ አለባት ሲሉ ሲሟገቱ የነበሩት ሪቻርድ ፓንክረስት

 

ሪቻርድ ፓንክረስት ምኞት

ከሠላሳ ዓመት በፊት ሪቻርድ ፓንክረስት እንዲህ ተመኙ፡፡ ‹‹ፀሐይ›› ወይም ‹‹ኢትዮጵያ 1›› የሚለው አውሮፕላን በሚመለስበት ጊዜ፣ በኢትዮጵያ አቪዬሽን ወይም በመሳሰሉት የወደፊቶቹ ሙዚየሞች ውስጥ መካተቱ በጣም አስፈላጊና ተስማሚ ይመስላል። ይህ የማይረሳ የቅድመ ጦርነት አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ አውሮፕላን ባይኖር ኢትዮጵያ ያለፈችበትን ራሷን የማዘመን ጉዞ ማስረጃ የለም ያሰኝ ነበር፡፡ የዚህ አውሮፕላን መኖር ከጦርነት በፊት ኢትዮጵያ ራሷን ለማዘመን ያደረገችውን ​​ጀግንነት የሚያሳይ ምስላዊ ማስረጃ ነው ይላሉ ፓንክረስት። አውሮፕላኑ በመንገዱ፣ በመቅደላ አምባ ከተሠራው የአፄ ቴዎድሮስ መድፍ -ሰባስቶፖል- ጋር ሊመሳሰል ይችላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...