Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅ‹‹የመጀመሪያው እራት›› በነ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኪነ ቅርፅ

‹‹የመጀመሪያው እራት›› በነ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኪነ ቅርፅ

ቀን:

በለንደኑ የሮያል አካዴሚ ኦፍ አርትስ ቅጥር ግቢ ውስጥ  በጣም አስደናቂ ከሆኑት የኪነ ቅርፅ ሥራዎች አንዱ ሰሞኑን ተገልጧል። የባሃማው ከያኒ ታቫሬስ ስትራቻን  በጥቁሩ ዓለም ከጥንት እስከ ዛሬ ገናን የሆኑ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ጨምሮ የ13 በየዘርፉ ስመ ጥር የሆኑ ግለሰቦችን ምስል ነው የሠራው፡፡ እነዚህ ጥቁሮች ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ላበረከቱት አስተዋፅዖ የመታሰቢያ ሐውልት እንዲሆናቸው የቆመ ሐውልት መሆኑን ዘ አርትኒውስ ፔፐር ዘግቧል፡፡ ‹‹የመጀመሪያው እራት (ጋላክሲ ብላክ) 2023›› የሚል ጥቅል ርዕስ ያለው የመታሰቢያ ኪነ ቅርፁ በሮያል አካዴሚ በቅኝ ግዛት ጥናት ውስጥ ተካቷል። የባሃማው ከያኒ ታቫሬስ ስትራቻ ይህን ቅርፅ እንዲሠራ መነሻ የሆነው የ16ኛው ክፍለ ዘመን የሊዮናርዶ ዳቪንቺ  ‹‹የመጨረሻው እራት›› ሥራው ነው፡፡ በቅርፁ ላይ ከሚታዩት መካከል ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሌላ የ1930ዎቹ የወንጌል ዘማሪ ሲስተር ሮዛታ ታርፕ፤ ለአሜሪካ ኮንግረስ የተመረጠችው የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ሸርሊ ቺሾልም፣; በ1969 በኒውዮርክ በስቶንዋል አመፅ ውስጥ ቁልፍ ሰው የነበሩት የ19ኛው ክፍለ ዘመን  ሃሪየት ቱብማን እና ማርሻ ፒ. ጆንሰን፣ የጠፈር ተመራማሪው ሮበርት ላውረንስ ይገኙበታል።

‹‹የመጀመሪያው እራት›› በነ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኪነ ቅርፅ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር‹‹የመጀመሪያው እራት›› በነ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኪነ ቅርፅ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...