Sunday, March 3, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ አገር ለመጎብኘት ከመጡ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር እየተወያዩ ነው]

 • ባደረጋችሁት ጉብኝት አገራችሁ ያለችበትን ትክክለኛ ገጽታ ለመመልከት እንደቻላችሁ እርግጠኛ ነኝ።
 • ልክ ነዎት ክቡር ሚኒስትር።
 • ታዲያ ጉብኝቱን እንዴት አገኛችሁት?
 • አንዳንድ ጉዳዮች በጥንቃቄ ከተያዙ አገራችን ተስፋ እንዳላት ተገንዝበናል።
 • እስኪ በጥንቃቄ መያዝ አለበት የምትሉትን አብራሩልኝ?
 • መንግሥት የጀመራቸው ተስፋ ሰጪ ነገሮች ቢኖሩም፣ በርካታ ግጭቶችና የማኅበረሰብ ጥያቄዎች ጥንቃቄና አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ ናቸው።
 • ለምሳሌ ብትጠቅሱልኝ?
 • ለምሳሌ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ አለው፣ ጥያቄውን ለምን አትመልሱም?
 • የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ የተለየ አይደለም።
 • እኛም የተለየ ነው አላልንም።
 • ታዲያ ምንድነው ያላችሁት?
 • ለምን ጥያቄውን አትመልሱም ነው ያልነው?
 • ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ ጋር አንድ ላይ ይመለሳል።
 • እሺ የአማራ ሕዝብ ጥያቄንስ ለምን አትመልሱም?
 • የአማራ ሕዝብ ጥያቄም ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ ጋር አብሮ ይመለሳል።
 • እሺ ሌላው ይቅር የትግራይ ሕዝብ ጥያቄን ለምን ቅድሚያ ሰጥታችሁ አትመልሱም?
 • የትግራይ ሕዝብ ጥያቄ ከሌላው የተለየ አይደለም።
 • እሺ ጥያቄውን ለምን አትመልሱም?
 • ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ ጋር አብሮ ይመለሳል።
 • እሺ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄን ለምን አትመልሱም?
 • ያው ነው።
 • ያው ነው ማለት ?
 • አንድ ላይ ይመለሳል ማለቴ ነው።
 • አንድ ላይ ማለት?
 • ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ ጋር አንድ ላይ ይመለሳል።

[ክቡር ሚኒስትሩ ከቢሮ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተመልሰው ልጃቸውን የሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ልጃቸውን በተመለከተ ከወላጅ ጋር ለመወያየት የፈለገበትን ምክንያት እንዲያስረዷቸው ባለቤታቸውን እየጠየቁ ነው]

 • ትምህርት ቤት ሄድሽ አይደል?
 • አዎ። 
 • እሺ ወላጅ የጠሩበት ምክንያት ምንድን ነው?
 • ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ጥያቄ እንዲመልሱ ተጠይቀው የእኛ ልጅ የሰጠው ምላሽ አስደንግጧቸው ነው።
 • ጥያቄው ምን ነበር?
 • ‹‹ስንዴ ለምን ለምን እንደሚጠቅም ግለጹ›› የሚል ጥያቄ ነበር የቀረበላቸው።
 • እሺ… ምን ብሎ መለሰ?
 • ሆሆ….
 • ምነው ?
 • ደግሜ ሳስበው እያሳቀኝ ነዋ!
 • ምን ብሎ ነው የመለሰው?
 • በመጀመሪያ… ስንዴ ለዳቦ ይጠቅማል አለ።
 • እሺ… ቀጥሎስ?
 • ለዶክመንተሪ!
 • ምን?
 • አይገርምህም!
 • የት ሰምቶ ነው።
 • እኔ ምን አውቄ።
 • እንዴት! ቤት አይደለም እንዴ የሚውለው?
 • ከቤት ውጪ የት ይውላል? ገና አንድ ፍሬ ልጅ አይደል እንዴ? 
 • ታዲያ ከየት አምጥቶት ነው?
 • ያው በቴሌቪዥን ስለ ስንዴ የሚቀርበውን ዝግጅት አይቶ ነው የሚሆነው።
 • ታዲያ ትምህርት ቤቱ ለምንድን ነው ወላጅ የጠራው?
 • የተቃዋሚ ፖለቲከኛ ልጅ መስሏቸው ነዋ!እንዴት?
 • እነሱማ መኖሪያ ቤት ውስጥ ልጅ ፊት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ይወራል ብለው አስበው ሊመክሩ ነበር ወላጅ የጠሩት። 
 • አንቺ ምን አልሻቸው ታዲያ?
 • አባቱ ሚኒስትር እንደሆነ ነገርኳቸው።
 • ምን አሉ?
 • እንደዚያ ከሆነ እንኳ ችግር የለውም አሉ።
 • ምን ማለታቸው ነው?
 • የሚኒስትር ልጅ ከሆነ ማለታቸው ነው፡፡
 • እና የሚኒስትር ልጅ ቢሆንስ!
 • ከሥራው ጋር የተገናኘ ነገር በቤት ውስጥ ይወራል ማለታቸው ነዋ!
 • የተትረፈረፈ የስንዴ ምርት ዳቦ ከመሆን ባለፈ ለማስተዋወቅም ይጠቅማል ሲባል ሊሰማ ይችላል ብለው ነዋ፡፡
 • እሱስ እውነት ነው ልክ ብለሻል፡፡
 • ግን…
 • ግን ምን?
 • ምርቱ ተትረፍርፏል የሚለው ያሳምናል?›
 • ለምን አያሳምንም?
 • በግልጽ የሚታይ ነው ብዬ ነው፡፡
 • ምኑ ነው በግልጽ የሚታየው?
 • የድርቅ ተጎጂዎች ብዛት ነዋ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...

ምርጫ ቦርድ ፓርላማው ያፀደቀለትን 304 ሚሊዮን ብር አለማግኘቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ሰኔ 2016 ዓ.ም. በአራት...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ ነው የሚደንቀው? የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ሕዝባዊ ውይይት ላይ ምን ጉዳዮች ተነሱ? በአስማት ነው የምንኖረው ሲሉ ቅሬታቸውን...

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...